Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 31:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 “የሰው ልጅ ሆይ! የግ​ብ​ፅን ንጉሥ ፈር​ዖ​ን​ንና ሕዝ​ቡን እን​ዲህ በላ​ቸው፦ በታ​ላ​ቅ​ነ​ትህ ማንን ትመ​ስ​ላ​ለህ?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 “የሰው ልጅ ሆይ፤ ለግብጽ ንጉሥ ለፈርዖንና ስፍር ቍጥር ለሌለው ሕዝቡ እንዲህ በል፤ “ ‘በክብር ከአንተ ጋራ ማን ሊወዳደር ይችላል?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 የሰው ልጅ ሆይ የግብጽን ንጉሥ ፈርዖንንና ብዛቱን እንዲህ በላቸው፦ በታላቅነትህ ማንን ትመስላለህ?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 “የሰው ልጅ ሆይ! ለግብጽ ንጉሥና ብዛት ላለው ሕዝቡ እንዲህ ብለህ ንገር፥ ‘በታላቅነት ከማን ጋር ትመሳሰላለህ?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 የሰው ልጅ ሆይ፥ የግብጽን ንጉሥ ፈርዖንንና የሕዝቡን ብዛት እንዲህ በላቸው፦ በታላቅነትህ ማንን መስለሃል?

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 31:2
9 交叉引用  

አንተ ግን ወገ​ብ​ህን ታጠቅ፤ ተነ​ሥም፤ ያዘ​ዝ​ሁ​ህ​ንም ሁሉ ንገ​ራ​ቸው፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ አት​ፍራ። በፊ​ታ​ቸ​ውም አት​ደ​ን​ግጥ አድ​ንህ ዘንድ እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“በእ​ና​ትህ ሆድ ሳል​ሠ​ራህ አው​ቄ​ሃ​ለሁ፤ ከማ​ኅ​ፀ​ንም ሳት​ወጣ ቀድ​ሼ​ሃ​ለሁ፥ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ነቢይ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ።”


እንደ ገና በአ​ሕ​ዛብ ላይ ከፍ ከፍ እን​ዳ​ይሉ ትንሽ መን​ግ​ሥት ይሆ​ናሉ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም ላይ እን​ዳ​ይ​በዙ አሳ​ን​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ የግ​ብ​ፅን ምድር ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ለና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ ብዛ​ቷ​ንም ይወ​ስ​ዳል፤ ምር​ኮ​ዋ​ንም ይማ​ር​ካል፤ ብዝ​በ​ዛ​ዋ​ንም ይበ​ዘ​ብ​ዛል፤ ይህም ለሠ​ራ​ዊቱ ደመ​ወዝ ይሆ​ናል።


“ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የግ​ብ​ፅን ብዛት በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ አጠ​ፋ​ለሁ።


“በክ​ብ​ርና በታ​ላ​ቅ​ነት በዔ​ድን ዛፎች መካ​ከል ማንን ትመ​ስ​ላ​ለህ? ነገር ግን ከዔ​ድን ዛፎች ጋር ወደ ታች​ኛው ምድር ያወ​ር​ዱ​ሃል፤ በሰ​ይ​ፍም በተ​ገ​ደ​ሉት ባል​ተ​ገ​ረ​ዙት መካ​ከል ትተ​ኛ​ለህ። ይህም ፈር​ዖ​ንና የሕ​ዝቡ ብዛት ሁሉ ነው፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“በብዙ ወገኖችና በአሕዛብም በቋንቋዎችም በነገሥታትም ላይ እንደ ገና ትንቢት ትናገር ዘንድ ይገባሃል፤” ተባልሁ።


跟着我们:

广告


广告