Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 30:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 የባ​ቢ​ሎ​ን​ንም ንጉሥ ክንድ አበ​ረ​ታ​ለሁ፤ ሰይ​ፌ​ንም በእጁ እሰ​ጣ​ለሁ፤ ግብ​ፅ​ንም ይወ​ጋ​በ​ታል፥ ምር​ኮ​ዋ​ንም ይማ​ር​ካል፤ ሰለ​ባ​ዋ​ንም ይሰ​ል​ባል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 የባቢሎንን ንጉሥ ክንድ አበረታለሁ፤ ሰይፌንም አስይዘዋለሁ፤ የፈርዖንን ክንድ ግን እሰብራለሁ፤ እርሱም በፊቱ ክፉኛ እንደ ቈሰለ ሰው ያቃስታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 የባቢሎንን ንጉሥ ክንድ አበረታለሁ ሰይፌንም በእጁ አኖራለሁ፤ የፈርዖንንም ክንድ እሰብራለሁ፥ እሱም በፊቱ ክፉኛ እንደቆሰለ ሰው ያቃስታል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 በዚህም ዐይነት የባቢሎንን ንጉሥ ኀይል በማጠንከር የእኔን ሰይፍ በእጁ አስይዘዋለሁ። የግብጽን ንጉሥ ኀይል ግን እሰብራለሁ፤ እርሱም ለሞት የሚያደርስ ቊስል እንደ ደረሰበት ሰው በጠላቱ ፊት ይቃትታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 የባቢሎንንም ንጉሥ ክንድ አበረታለሁ ሰይፌንም በእጁ እሰጣለሁ፥ የፈርዖንን ክንድ ግን እሰብራለሁ፥ ተወግቶም በሚሞተው እንጕርጕሮ በፊቱ ያንጐራጕራል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 30:24
21 交叉引用  

እነ​ር​ሱም ሁሉ ሥራው እን​ዳ​ይ​ፈ​ጸም፥ “እጃ​ቸው ይደ​ክ​ማል” ብለው አስ​ፈ​ራ​ሩን፤ ስለ​ዚ​ህም እጆ​ችን አበ​ረ​ታሁ።


ድሆ​ችን ከከ​ተ​ማ​ውና ከገዛ ቤቶ​ቻ​ቸው አባ​ረ​ሩ​አ​ቸው የሕ​ፃ​ና​ት​ንም ነፍስ እጅግ አስ​ጮሁ፤


አም​ላኬ ንጉሤ ሆይ፥ ከፍ ከፍ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ፥ ስም​ህ​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ዓለም አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ማ​ያት አን​ጐ​ደ​ጐደ፥ ልዑ​ልም ቃሉን ሰጠ።


“በውኑ መጥ​ረ​ቢያ በሚ​ቈ​ር​ጥ​በት ሰው ላይ ይነ​ሣ​ልን? ወይስ መጋዝ በሚ​ስ​በው ሰው ላይ ይጓ​ደ​ዳ​ልን? ይህም ዘንግ በሚ​መ​ቱ​በት ላይ እንደ መነ​ሣት፥ በት​ርም ዕን​ጨት አይ​ደ​ለ​ሁም እንደ ማለት ነው።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ለቀ​ባ​ሁት፥ አሕ​ዛ​ብ​ንም በፊቱ አስ​ገዛ ዘንድ የነ​ገ​ሥ​ታ​ት​ንም ኀይል እጥል ዘንድ፥ በሮ​ቹም እን​ዳ​ይ​ዘጉ መዝ​ጊ​ያ​ዎ​ቹን በፊቱ እከ​ፍት ዘንድ፥ ቀኝ እጁን ለያ​ዝ​ሁት ለቂ​ሮስ እን​ዲህ ይላል፦


እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ነኝ፤ ከእ​ኔም በቀር ሌላ አም​ላክ የለም፤ አጸ​ና​ሁህ፤ አንተ ግን አላ​ወ​ቅ​ኸ​ኝም።


ስለ​ዚህ እነሆ የተ​ቀ​ረ​ጹ​ትን ምስ​ሎ​ች​ዋን የም​በ​ቀ​ል​በት ዘመን ይመ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በም​ድ​ር​ዋም ሁሉ የተ​ገ​ደ​ሉት ይወ​ድ​ቃሉ።


“ስለ ጢሮስ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሾተ​ላ​ቸ​ውን በመ​ካ​ከ​ልሽ በመ​ዘዙ ጊዜ ከው​ድ​ቀ​ትሽ፥ ከቈ​ሰ​ሉ​ትም ጩኸት የተ​ነሣ፤ ደሴ​ቶች የሚ​ነ​ዋ​ወጡ አይ​ደ​ለ​ምን?


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ የግ​ብ​ፅን ምድር ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ለና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ ብዛ​ቷ​ንም ይወ​ስ​ዳል፤ ምር​ኮ​ዋ​ንም ይማ​ር​ካል፤ ብዝ​በ​ዛ​ዋ​ንም ይበ​ዘ​ብ​ዛል፤ ይህም ለሠ​ራ​ዊቱ ደመ​ወዝ ይሆ​ናል።


“ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የግ​ብ​ፅን ብዛት በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ አጠ​ፋ​ለሁ።


እር​ሱና ሕዝቡ የአ​ሕ​ዛ​ብም ኀያ​ላን ምድ​ሪ​ቱን ለማ​ጥ​ፋት ይላ​ካሉ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ን​ንም በሰ​ይፍ ይወ​ጉ​አ​ቸ​ዋል፤ ምድ​ሪ​ቱም በሙ​ታን ትሞ​ላ​ለች።


“የሰው ልጅ ሆይ! የግ​ብ​ፅን ንጉሥ የፈ​ር​ዖ​ንን ክንድ ሰብ​ሬ​አ​ለሁ፥ እነ​ሆም ይድን ዘንድ መድ​ኃ​ኒት ቀብ​ተው አያ​ደ​ር​ቁ​ትም፤ ሰይ​ፉ​ንም ለመ​ያዝ ኀይ​ልን ያገኝ ዘንድ አል​ታ​ሰ​ረም።


የባ​ቢ​ሎ​ን​ንም ንጉሥ ክንድ አጸ​ና​ለሁ፤ የፈ​ር​ዖ​ንም ክንድ ይወ​ድ​ቃል፤ ሰይ​ፌ​ንም በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ እጅ በሰ​ጠሁ ጊዜ፥ እር​ሱም በግ​ብፅ ምድር ላይ በዘ​ረ​ጋው ጊዜ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።


እናንተም ኢትዮጵያውያን ደግሞ፥ በሰይፌ ትገደላላችሁ።


跟着我们:

广告


广告