Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 3:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 በዚ​ያም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእኔ ላይ ነበ​ረች፤ እር​ሱም፥ “ተነ​ሥ​ተህ ወደ ሜዳ ሂድ፤ በዚ​ያም እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ” አለኝ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 የእግዚአብሔር እጅ በላዬ ነበረ፤ እርሱም፣ “ተነሥተህ ወደ ረባዳው ስፍራ ሂድ፤ በዚያ እናገርሃለሁ” አለኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 በዚያም የጌታ እጅ በእኔ ላይ ነበረች፥ እርሱም እንዲህ አለኝ፦ ተነሥ፥ ወደ ሜዳ ውጣ፥ በዚያም ከአንተ ጋር እነጋገራለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር ኀይል በእኔ ላይ ነበረ፤ “ተነሥተህ ወደ ሸለቆ ሂድ፤ በዚያም አነጋግርሃለሁ” አለኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 በዚያም የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ላይ ነበረች፥ እርሱም፦ ተነሥተህ ወደ ቈላው ሂድ በዚያም እናገርሃለሁ አለኝ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 3:22
6 交叉引用  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሀገር በኮ​ቦር ወንዝ ላይ ወደ ቡዝ ልጅ ወደ ካህኑ ወደ ሕዝ​ቅ​ኤል መጣ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ በዚያ በእኔ ላይ ሆነች፤


መን​ፈ​ስም አን​ሥቶ ወሰ​ደኝ፤ እኔም በም​ሬ​ትና በመ​ን​ፈሴ ሙቀት ሄድሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ በላዬ በር​ትታ ነበር።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ በላዬ ነበረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በመ​ን​ፈሱ አወ​ጣኝ፤ አጥ​ን​ቶ​ችም በሞ​ሉ​በት ሸለቆ መካ​ከል አኖ​ረኝ።


በተ​ማ​ረ​ክን በሃያ አም​ስ​ተ​ኛው ዓመት በዓ​መቱ መጀ​መ​ሪያ ከወሩ በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን፥ ከተ​ማ​ዪቱ ከተ​መ​ታች በኋላ በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ዓመት፥ በዚ​ያው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእኔ ላይ ነበረ፤ እር​ሱም ወደ​ዚያ ወሰ​ደኝ።


እነ​ሆም ቀድሞ በሜዳ እንደ አየ​ሁት ራእይ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ክብር በዚያ ነበረ።


እር​ሱም እየ​ፈ​ራና እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀጠ፥ “አቤቱ፥ ምን እን​ዳ​ደ​ርግ ትሻ​ለህ?” አለው፤ ጌታም፥ “ተነ​ሣና ወደ ከተማ ግባ፤ በዚ​ያም ልታ​ደ​ር​ገው የሚ​ገ​ባ​ህን ይነ​ግ​ሩ​ሃል” አለው።


跟着我们:

广告


广告