Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 3:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ደግሞ ጻድቁ ከጽ​ድቁ ተመ​ልሶ ኀጢ​አት በሠራ ጊዜ እኔ በፊቱ ዕን​ቅ​ፋት ባደ​ርግ፥ እርሱ ይሞ​ታል፤ አን​ተም አል​ነ​ገ​ር​ኸ​ው​ምና በኀ​ጢ​አቱ ይሞ​ታል፤ ያደ​ረ​ጋ​ትም የጽ​ድቅ ነገር አት​ታ​ሰ​ብ​ለ​ትም፤ ደሙን ግን ከእ​ጅህ እፈ​ል​ጋ​ለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 “ጻድቁ ሰው ደግሞ ከጽድቁ ተመልሶ ኀጢአት ቢሠራ፣ እኔም መሰናክል በፊቱ ባስቀምጥ እርሱ ይሞታል፤ አንተ አላስጠነቀቅኸውምና በኀጢአቱ ይሞታል፤ ያደረገውም ጽድቅ አይታሰብለትም፤ አንተንም ስለ ደሙ በኀላፊነት እጠይቅሃለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ጻድቁ ደግሞ ከጽድቁ ተመልሶ ኃጢአት ከሠራ፥ እኔም በፊቱ ዕንቅፋትን አደርጋለሁ፥ እርሱም ይሞታል፤ አንተም አላስጠነቀቅኸውምና በኃጢአቱ ይሞታል፥ የጽድቁም ሥራ አይታሰብለትም፥ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 “በደግነቱ የታወቀ ጻድቅ ሰው ክፉ ሥራ መሥራት ቢጀምርና እኔም በችግር ላይ እንዲወድቅ ባደርገው፥ አንተ ካላስጠነቀቅኸው በቀር በኃጢአቱ ይሞታል፤ ከዚያ በፊት የፈጸመው መልካም ሥራ ሁሉ አይታሰብለትም፤ ስለ እርሱ ሞት አንተን በኀላፊነት እጠይቅሃለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ደግሞ ጻድቁ ከጽድቁ ተመልሶ ኃጢአት በሠራ ጊዜ እኔ በፊቱም ዕንቅፋትን ሳደርግ፥ እርሱ ይሞታል፥ አንተም አላስጠነቀቅኸውምና በኃጢአቱ ይሞታል ያደረጋትም ጽድቅ ነገር አትታሰብለትም፥ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 3:20
41 交叉引用  

ኢዮ​አ​ስም በካ​ህኑ በኢ​ዮ​አዳ ዘመን ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገ​ርን አደ​ረገ።


ስለ​ዚ​ህም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በን​ጉሡ በአ​ሜ​ስ​ያስ ላይ መጣ፤ እን​ዲ​ህም ሲል ነቢ​ይን ላከ​በት፥ “ሕዝ​ባ​ቸ​ውን ከአ​ንተ እጅ ያላ​ዳ​ኑ​ትን የአ​ሕ​ዛ​ብን አማ​ል​ክት ስለ​ምን ፈለ​ግ​ሃ​ቸው?”


በል​ቅሶ የሚ​ዘሩ በደ​ስታ ይሰ​በ​ስ​ባሉ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመን፥ መል​ካ​ም​ንም አድ​ርግ፥ በም​ድ​ርም ያሳ​ድ​ር​ሃል፥ በሀ​ብ​ት​ዋም ያሰ​ማ​ር​ሃል።


ሁላ​ችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነ​ናል፤ ጽድ​ቃ​ች​ንም ሁሉ እንደ መር​ገም ጨርቅ ነው፤ በኀ​ጢ​አ​ታ​ችን ምክ​ን​ያት እንደ ቅጠል ረግ​ፈ​ናል፤ እን​ዲ​ሁም ነፋስ ጠራ​ርጎ ወስ​ዶ​ናል።


ብታ​ም​ን​በት ይቀ​ድ​ስ​ሃል፤ እንደ ድን​ጋይ ዕን​ቅ​ፋ​ትም አያ​ደ​ና​ቅ​ፍ​ህም፤ እን​ደ​ሚ​ያ​ድጥ ዓለ​ትም አይ​ሆ​ን​ብ​ህም፤ ሁለቱ የያ​ዕ​ቆብ ቤቶች ግን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በወ​ጥ​መ​ድና በአ​ሽ​ክላ ተይ​ዘው ይኖ​ራሉ።


ነገር ግን ተመ​ል​ሳ​ችሁ ስሜን አስ​ነ​ቀ​ፋ​ችሁ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ች​ሁም በፈ​ቃ​ዳ​ቸው እን​ዲ​ሄዱ አር​ነት ያወ​ጣ​ች​ኋ​ቸ​ውን ወን​ድና ሴት ባሪ​ያ​ዎ​ቻ​ች​ሁን፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ባሪ​ያ​ዎች እን​ዲ​ሆ​ኑ​ላ​ችሁ መለ​ሳ​ች​ኋ​ቸው።”


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በዚህ ሕዝብ ላይ ደዌን አሳ​ድ​ራ​ለሁ፤ አባ​ቶ​ችና ልጆ​ችም በአ​ን​ድ​ነት ይታ​መ​ማሉ፤ ጎረ​ቤ​ትና ባል​ን​ጀ​ራም ይጠ​ፋሉ።


“የሰው ልጅ ሆይ! እነ​ዚህ ሰዎች በል​ባ​ቸው ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አኑ​ረ​ዋል፤ የበ​ደ​ላ​ቸ​ው​ንም መቅ​ሠ​ፍት በፊ​ታ​ቸው አቁ​መ​ዋል፤ እኔስ ለእ​ነ​ርሱ መልስ ልመ​ል​ስ​ላ​ቸ​ውን?


ጻድቁ ግን ከጽ​ድቁ ቢመ​ለስ፥ ኀጢ​አ​ት​ንም ቢሠራ፥ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውም እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ር​ገው ርኵ​ሰት ሁሉ ቢያ​ደ​ርግ፥ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራ​ልን? የሠ​ራው ጽድቅ ሁሉ አይ​ታ​ሰ​ብ​ለ​ትም፤ በአ​ደ​ረ​ገው ዐመ​ፅና በሠ​ራት ኀጢ​አት በዚ​ያች ይሞ​ታል።


ጻድቁ ከጽ​ድቁ ቢመ​ለስ፥ ኀጢ​አ​ት​ንም በሠራ ጊዜ፥ በዚያ ቢሞት፥ እርሱ በአ​ደ​ረ​ገው በደል ይሞ​ታል።


እኔ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን፥ “በእ​ር​ግጥ ትሞ​ታ​ለህ ባል​ሁት ጊዜ አን​ተም ባት​ነ​ግ​ረው፥ ነፍ​ሱም እን​ድ​ት​ድን ከክፉ መን​ገዱ ይመ​ለስ ዘንድ ለኀ​ጢ​አ​ተ​ኛው ባት​ነ​ግ​ረው፥ ያ ኀጢ​አ​ተኛ በኀ​ጢ​አቱ ይሞ​ታል፤ ደሙን ግን ከእ​ጅህ እፈ​ል​ጋ​ለሁ።


ጻድቅ ከጽ​ድቁ ተመ​ልሶ ኀጢ​አ​ትን ቢሠራ ይሞ​ት​በ​ታል።


ጕበ​ኛው ግን ጦር ሲመጣ ቢያይ፥ መለ​ከ​ቱ​ንም ባይ​ነፋ፥ ሕዝ​ቡ​ንም ባያ​ስ​ጠ​ነ​ቅቅ፥ ጦርም መጥቶ አንድ ሰው ከእ​ነ​ርሱ ቢወ​ስድ፥ እርሱ በኀ​ጢ​አቱ ተወ​ስ​ዶ​አል፤ ደሙን ግን ከጕ​በ​ኛው እጅ እፈ​ል​ጋ​ለሁ።


ብራ​ቸ​ውን በጎ​ዳ​ና​ዎቹ ላይ ይጥ​ላሉ፤ ወር​ቃ​ቸ​ውም ይረ​ክ​ሳል፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዓት ቀን ብራ​ቸ​ውና ወር​ቃ​ቸው አያ​ድ​ና​ቸ​ውም። እርሱ የኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው እን​ቅ​ፋት ሆኖ​አ​ልና ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን አያ​ጠ​ግ​ቡም፤ ሆዳ​ቸ​ው​ንም አይ​ሞ​ሉም።


“ወን​ድ​ም​ህን አት​በ​ድ​ለው፤ በል​ብ​ህም አት​ጥ​ላው፤ በእ​ርሱ ምክ​ን​ያት ኀጢ​አት እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ብህ ባል​ን​ጀ​ራ​ህን የም​ት​ነ​ቅ​ፍ​በ​ትን ንገ​ረው፤ ገሥ​ጸ​ውም።


እግዚአብሔርንም ከመከተል የተመለሱትን፥ እግዚአብሔርንም ያልፈለጉትንና ያልጠየቁትን አጠፋለሁ።


“ወንድምህም ቢበድልህ፥ ሄደህ አንተና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ ውቀሰው። ቢሰማህ፥ ወንድምህን ገንዘብ አደረግኸው፤


ስም​ዖ​ንም ባረ​ካ​ቸው፤ እና​ቱን ማር​ያ​ም​ንም እን​ዲህ አላት፤ “እነሆ፥ ይህ ሕፃን ከእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል ለብ​ዙ​ዎች ለመ​ው​ደ​ቃ​ቸ​ውና ለመ​ነ​ሣ​ታ​ቸው፥ ለሚ​ቃ​ወ​ሙ​ትም ምል​ክት ይሆን ዘንድ የተ​ሠ​የመ ነው፤


በመ​ል​ካም ምድር የወ​ደ​ቀው ግን ቃሉን በበ​ጎና በን​ጹሕ ልብ የሚ​ሰ​ሙና የሚ​ጠ​ብ​ቁት፥ ታግ​ሠ​ውና ጨክ​ነ​ውም የሚ​ያ​ፈሩ ናቸው።


ዳዊ​ትም እን​ዲህ ብሎ​አል፥ “ማዕ​ዳ​ቸው በፊ​ታ​ቸው ወጥ​መ​ድና አሽ​ክላ፥ መሰ​ና​ከ​ያና ፍዳም ትሁ​ን​ባ​ቸው።


እኛ ግን የተ​ሰ​ቀ​ለ​ውን ክር​ስ​ቶ​ስን እን​ሰ​ብ​ካ​ለን፤ ይህም ለአ​ይ​ሁድ ማሰ​ና​ከያ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ስን​ፍና ነው።


አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በፍ​ጹም ልባ​ችሁ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ሳ​ችሁ ትወ​ድ​ዱት እን​ደ​ሆን ያውቅ ዘንድ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊፈ​ት​ና​ችሁ ነውና የዚ​ያን ነቢይ ቃል ወይም ያን ሕልም አላሚ አት​ስሙ።


ጻድቅ በእ​ም​ነት ይድ​ናል፤ ወደ​ኋላ ቢመ​ለስ ግን ልቡ​ናዬ በእ​ርሱ ደስ አይ​ላ​ትም።”


ለመ​ም​ህ​ሮ​ቻ​ችሁ ታዘዙ፤ ተገ​ዙ​ላ​ቸ​ውም፤ ስለ እና​ንተ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ምላሽ የሚ​ሰጡ እንደ መሆ​ና​ቸው፥ ይህን ሳያ​ዝኑ ደስ ብሎ​አ​ቸው ያደ​ር​ጉት ዘንድ ስለ ነፍ​ሳ​ችሁ ይተ​ጋ​ሉና።


የማሰናከያም ዓለት ሆነ፤” የማያምኑ ስለ ሆኑ በቃሉ ይሰናከሉበታልና፤ ለዚህ ደግሞ የተመደቡ ናቸው።


ከእኛ ዘንድ ወጡ፥ ዳሩ ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ከእኛ ጋር ጸንተው በኖሩ ነበር፤ ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ ይገለጡ ዘንድ ወጡ።


跟着我们:

广告


广告