Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 3:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ተነ​ሥ​ተ​ህም ወደ ተማ​ረኩ ወደ ወገ​ንህ ልጆች ሂድ፤ እነ​ር​ሱም ቢሰሙ ወይም ቢፈሩ፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል ብለህ ንገ​ራ​ቸው” አለኝ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ተነሥተህም በምርኮ ወዳሉት ወገኖችህ ሄደህ ተናገራቸው፤ ቢሰሙህም ባይሰሙህም፣ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል’ በላቸው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ተነሥተህም ወደ ተማረኩት፥ ወደ ሕዝብህ ልጆች ሂድ፥ እነርሱም ቢሰሙ ወይም ባይሰሙ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ንገራቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 በምርኮ ወደሚገኙት የአገርህ ሕዝብ ሄደህ ቢሰሙህም ባይሰሙህም እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምላቸውን ሁሉ ንገራቸው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ተነሥተህም ወደ ተማረኩ ወደ ወገንህ ልጆች ሂድ፥ እነርሱም ቢሰሙ ወይም ባይሰሙ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ንገራቸው አለኝ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 3:11
20 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን ተና​ገ​ረው እን​ዲ​ህም አለው፥ “ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ኻ​ቸው ሕዝ​ብህ በድ​ለ​ዋ​ልና ሂድ፤ ፈጥ​ነህ ውረድ።


ስለ​ዚህ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ባቢ​ሎን የሰ​ደ​ድ​ኋ​ችሁ ምር​ኮ​ኞች ሁሉ ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።”


እነ​ርሱ ፊታ​ቸው የከፋ፥ ልባ​ቸው የደ​ነ​ደነ ልጆች ናቸው። እኔ ወደ እነ​ርሱ እል​ክ​ሃ​ለሁ፤ አን​ተም፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል በላ​ቸው።


“እነ​ርሱ ዐመ​ፀኛ ቤት ናቸ​ውና ቢሰሙ ወይም ቢፈሩ አንተ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ነቢይ እንደ ሆንህ ያው​ቃሉ።


እነ​ርሱ ዐመ​ፀኛ ቤት ስለ​ሆኑ ቢሰሙ ወይም ቢደ​ነ​ግጡ ቃሌን ትነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ።


“ስለ​ዚህ የሰው ልጅ ሆይ! ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በዚ​ህም ደግሞ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ በአ​ደ​ረ​ጉት ዐመፅ አስ​ቈ​ጡኝ።


እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! የነ​ገ​ር​ሁ​ህን ቃሌን ሁሉ በል​ብህ ጠብ​ቀው፤ በጆ​ሮ​ህም ስማው።


መን​ፈ​ስም ወደ ላይ ወሰ​ደኝ፤ በኋ​ላ​ዬም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ከቦ​ታው ይባ​ረክ” የሚል የታ​ላቅ ንው​ጽ​ው​ጽታ ድምፅ ሰማሁ።


በቴ​ል​አ​ቢ​ብም ወደ አሉ፥ በኮ​ቦ​ርም ወንዝ አጠ​ገብ ወደ ተቀ​መጡ ምር​ኮ​ኞች መጣሁ፤ በተ​ቀ​መ​ጡ​በ​ትም ቦታ ተቀ​መ​ጥሁ፤ በዚ​ያም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው እየ​ተ​መ​ላ​ለ​ስሁ ሰባት ቀን ተቀ​መ​ጥሁ።


ነገር ግን በተ​ና​ገ​ር​ሁህ ጊዜ አፍ​ህን እከ​ፍ​ታ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ዐመ​ፀኛ ቤት ናቸ​ውና አንተ፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የሚ​ሰማ ይስማ፤ እንቢ የሚ​ልም እንቢ ይበል” ትላ​ቸ​ዋ​ለህ።


አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! የሕ​ዝ​ብ​ህን ልጆች እን​ዲህ በላ​ቸው፦ በበ​ደ​ለ​በት ቀን የጻ​ድቅ ጽድቁ አያ​ድ​ነ​ውም፤ ኀጢ​አ​ተ​ኛም ከኀ​ጢ​አቱ በተ​መ​ለ​ሰ​በት ቀን በኀ​ጢ​አቱ አይ​ሰ​ና​ከ​ልም፤ ጻድ​ቁም ኀጢ​አት በሠ​ራ​በት ቀን በጽ​ድቁ በሕ​ይ​ወት አይ​ኖ​ርም።


“የሕ​ዝ​ብህ ልጆች፦ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ገድ የቀና አይ​ደ​ለም ይላሉ፤ ነገር ግን የእ​ነ​ርሱ መን​ገድ የቀና አይ​ደ​ለም።


“የሰው ልጅ ሆይ! ለሕ​ዝ​ብህ ልጆች ተና​ገር እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ጦርን በም​ድር ላይ በአ​መ​ጣሁ ጊዜ፥ የም​ድር ሕዝብ ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አንድ ሰውን ወስ​ደው ለራ​ሳ​ቸው ጕበኛ ቢያ​ደ​ርጉ፥


“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! የሕ​ዝ​ብህ ልጆች በቅ​ጥር አጠ​ገ​ብና በቤት ደጆች ውስጥ ስለ አንተ ይና​ገ​ራሉ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም አንዱ ከአ​ንዱ ጋር፦ እን​ሂ​ድና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ለ​ውን ቃል እን​ስማ ይላሉ።


የሕ​ዝ​ብ​ህም ልጆች፦ ይህ የም​ታ​ደ​ር​ገው ነገር ምን ማለት እንደ ሆነ አት​ነ​ግ​ረ​ን​ምን? ብለው በተ​ና​ገ​ሩህ ጊዜ፥ አንተ፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፦ ተነ​ሥ​ተህ ከዚህ ፈጥ​ነህ ውረድ፤ ከግ​ብፅ ያወ​ጣ​ሃ​ቸው ሕዝ​ብህ በድ​ለ​ዋ​ልና፤ ፈጥ​ነው ካዘ​ዝ​ኋ​ቸው መን​ገድ ፈቀቅ ብለ​ዋ​ልና፥ ቀልጦ የተ​ሠራ ምስ​ልም ለራ​ሳ​ቸው አድ​ር​ገ​ዋ​ልና።


跟着我们:

广告


广告