ሕዝቅኤል 29:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ የግብፅን ምድር ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እሰጠዋለሁ፤ ብዛቷንም ይወስዳል፤ ምርኮዋንም ይማርካል፤ ብዝበዛዋንም ይበዘብዛል፤ ይህም ለሠራዊቱ ደመወዝ ይሆናል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም19 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ግብጽን ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እሰጣለሁ፤ ሀብቷን ሁሉ ያግዛል፤ ለሰራዊቱም ደመወዝ ይሆን ዘንድ ምድሪቱን ይበዘብዛል፤ ይመዘብራልም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ የግብጽን ምድር ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እሰጠዋለሁ፤ ብዛትዋን ያነሳል፥ ምርኮዋን ይማርካል፥ ብዝበዛዋንም ይበዘብዛል፤ ይህም ለሠራዊቱ ደመወዝ ይሆናል። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 ስለዚህ እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምለው ይህ ነው፦ ‘የግብጽን ምድር ለንጉሥ ናቡከደነፆር አሳልፌ እሰጠዋለሁ፤ እርሱም ለሠራዊቱ እንደ ደመወዝ ይሆንለት ዘንድ በዘረፋና በብዝበዛ የሚያገኘውን ሀብት ሁሉ ይዞ ይሄዳል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የግብጽን ምድር ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እሰጠዋለሁ፥ ብዛትዋንም ይወስዳል ምርኮዋንም ይማርካል ብዝበዛዋንም ይበዘብዛል፥ ይህም ለሠራዊቱ ደመወዝ ይሆናል። 参见章节 |