Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 28:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ቸነ​ፈ​ር​ንም በአ​ንቺ ላይ፥ ደም​ንም በጎ​ዳ​ናሽ ላይ እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ ከዙ​ሪ​ያ​ሽም በላ​ይሽ ባለ ሰይፍ የተ​ወጉ በመ​ካ​ከ​ልሽ ይወ​ድ​ቃሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 በርሷ ላይ መቅሠፍት አመጣለሁ፤ በመንገዶቿ ላይ ደም እንዲፈስስ አደርጋለሁ፤ ከየአቅጣጫው በሚመጣ ሰይፍ፣ የታረዱት በውስጧ ይወድቃሉ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ቸነፈርንም በእርሷ ላይ፥ ደምንም በጎዳናዋ እሰድዳለሁ፤ ከዙሪያዋ በላይዋ ባለ ሰይፍ የተወጉ በመካከልዋ ይወድቃሉ፤ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 መቅሠፍቴን በእናንተ ላይ አመጣለሁ፤ በየመንገዱም ደም እንዲፈስስ አደርጋለሁ፤ በየአቅጣጫው በሚነሣባችሁ ጦርነት ምክንያት በመካከላችሁ ሰዎች ይገደላሉ፤ ሕዝቦችም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ቸነፈርንም በእርስዋ ላይ፥ ደምንም በጎዳናዋ እሰድዳለሁ፥ ከዙሪያዋ በላይዋ ባለ ሰይፍ የተወጉ በመካከልዋ ይወድቃሉ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 28:23
13 交叉引用  

እነ​ር​ሱም፦ ወዴት እን​ሂድ ቢሉህ፥ አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ለሞት የሆነ ወደ ሞት፥ ለሰ​ይ​ፍም የሆነ ወደ ሰይፍ፥ ለራ​ብም የሆነ ወደ ራብ፥ ለም​ር​ኮም የሆነ ወደ ምርኮ ትላ​ቸ​ዋ​ለህ።


ስለ​ዚህ እነሆ የተ​ቀ​ረ​ጹ​ትን ምስ​ሎ​ች​ዋን የም​በ​ቀ​ል​በት ዘመን ይመ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በም​ድ​ር​ዋም ሁሉ የተ​ገ​ደ​ሉት ይወ​ድ​ቃሉ።


ስለ​ዚህ አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ትን​ቢት ተና​ገር፤ እጅ​ህን በእ​ጅህ ላይ አጨ​ብ​ጭብ፤ የተ​ገ​ደሉ ሰዎች ሰይፍ ሦስት ጊዜ ይደ​ጋ​ግም፤ ይኸ​ውም የታ​ላቅ ግድያ ሰይፍ ነው፤ ያስ​ደ​ነ​ግ​ጣ​ቸ​ዋ​ልም።


ፊትህ ወደ አቀ​ናው ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ሂድ።


በሞ​አ​ብም ላይ በቀ​ልን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”


በመ​ዓት መቅ​ሠ​ፍ​ትም ታላቅ በቀል አደ​ር​ግ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በቀ​ሌ​ንም በላ​ያ​ቸው በአ​ደ​ረ​ግሁ ጊዜ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”


ስለ​ዚህ እነሆ እጄን ዘር​ግ​ቼ​ብ​ሃ​ለሁ፤ ለአ​ሕ​ዛ​ብም አስ​በ​ዘ​ብ​ዝ​ሃ​ለሁ፤ ከአ​ሕ​ዛ​ብም ለይች እቈ​ር​ጥ​ሃ​ለሁ፤ ከሀ​ገ​ሮ​ችም እደ​መ​ስ​ስ​ሃ​ለሁ፤ አጠ​ፋ​ሃ​ለ​ሁም፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ለህ።”


በሜዳ ያሉ​ትም ሴቶች ልጆ​ችዋ በሰ​ይፍ ይገ​ደ​ላሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።


ሰይፍ በግ​ብፅ ላይ ይመ​ጣል፤ ሁከ​ትም በኢ​ት​ዮ​ጵያ ይሆ​ናል፤ የተ​ገ​ደ​ሉ​ትም በግ​ብፅ ውስጥ ይወ​ድ​ቃሉ፤ ብዛ​ቷ​ንም ይወ​ስ​ዳሉ፤ መሠ​ረ​ቷም ይፈ​ር​ሳል።


ከአ​ል​ተ​ገ​ረ​ዙና ወደ ጕድ​ጓድ ከሚ​ወ​ርዱ ጋር ተኝ​ተ​ዋል፤ የሰ​ሜን አለ​ቆች ሁሉ፥ ሲዶ​ና​ው​ያ​ንም ሁሉ ከተ​ገ​ደ​ሉት ጋር ወር​ደው በዚያ አሉ፤ በኀ​ይ​ላ​ቸ​ውም ያስ​ፈሩ በነ​በ​ረው ፍር​ሀት አፍ​ረ​ዋል፤ በሰ​ይ​ፍም ከተ​ገ​ደ​ሉት ጋር ያል​ተ​ገ​ረ​ዙት ተኝ​ተ​ዋል፤ ወደ ጕድ​ጓ​ድም ከሚ​ወ​ር​ዱት ጋር ቅጣ​ታ​ቸ​ውን ተሸ​ክ​መ​ዋል።


በቸ​ነ​ፈ​ርና በደም እፈ​ር​ድ​በ​ታ​ለሁ፤ ዶፍም፥ የበ​ረ​ዶም ድን​ጋይ፥ እሳ​ትና ድኝም በእ​ር​ሱና በጭ​ፍ​ሮቹ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር በአሉ በብዙ ሕዝብ ላይ አዘ​ን​ባ​ለሁ።


ከአ​ን​ቺም ሢሶው በቸ​ነ​ፈር ይሞ​ታል፤ በመ​ካ​ከ​ል​ሽም በራብ ያል​ቃል፤ ሢሶ​ውም በዙ​ሪ​ያሽ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃል፤ ሢሶ​ው​ንም ወደ ነፋ​ሳት ሁሉ እበ​ት​ና​ለሁ፤ በኋ​ላ​ቸ​ውም ሰይ​ፍን እመ​ዝ​ዛ​ለሁ።


ራብ​ንና ክፉ​ዎ​ችን አራ​ዊት እሰ​ድ​ድ​ብ​ሻ​ለሁ፤ እቀ​ሥ​ፍ​ሻ​ለሁ፤ ልጆ​ች​ሽ​ንም ያጠ​ፋሉ ቸነ​ፈ​ርና ደምም በአ​ንቺ ላይ ይመ​ጡ​ብ​ሻል፤ ሰይ​ፍ​ንም አመ​ጣ​ብ​ሻ​ለሁ፤ ይከ​ቡ​ሻ​ልም። እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ።”


跟着我们:

广告


广告