Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 28:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 “አንተ የሰው ልጅ ሆይ! የጢ​ሮ​ስን አለቃ እን​ዲህ በለው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ልብህ ኰር​ት​ዋል፥ አንተ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በባ​ሕር መካ​ከል እን​ዲ​ቀ​መጥ እኔም ተቀ​ም​ጫ​ለሁ ብለ​ሃ​ልና፤ አንተ ሰው ስት​ሆን ልብ​ህን እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልብ ብታ​ደ​ር​ግም አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ህም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 “የሰው ልጅ ሆይ፤ ለጢሮስ ገዥ እንዲህ በለው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ልብህ በትዕቢት ተወጥሮ፣ “እኔ አምላክ ነኝ፤ በአምላክ ዙፋን ላይ፣ በባሕሮችም ልብ ተቀምጫለሁ” አልህ። ምንም እንኳ እንደ አምላክ ጠቢብ ነኝ ብለህ ብታስብም፣ አንተ ሰው እንጂ አምላክ አይደለህም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 የሰው ልጅ ሆይ፥ የጢሮስን ገዥ እንዲህ በለው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልብህ ኰርቶአል አንተም እንዲህ ብለሃል፦ እኔ አምላክ ነኝ፥ በእግዚአብሔር ወንበር በባሕር ልብ ተቀምጫለሁ፤ ነገር ግን ልብህን እንደ እግዚአብሔር ልብ ብታደርግም አንተ ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 “የሰው ልጅ ሆይ! ልዑል እግዚአብሔር ለጢሮስ ንጉሥ እንዲህ ይላል ብለህ ንገረው፦ ‘ልብህ ስለ ታበየ እኔ አምላክ ነኝ በባሕሩ መካከል በአማልክት ዙፋን ላይ እቀመጣለሁ ብለሃል። ምንም እንኳ አንተ በሐሳብህ አምላክ ነኝ ብትል ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 የሰው ልጅ ሆይ፥ የጢሮስን ገዥ እንዲህ በለው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልብህ ኰርቶአል አንተም፦ እኔ አምላክ ነኝ፥ በእግዚአብሔር ወንበር በባሕር መካከል ተቀምጫለሁ ብለሃል፥ ነገር ግን ልብህን እንደ እግዚአብሔር ልብ ብታደርግም አንተ ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 28:2
40 交叉引用  

ከእ​ር​ስዋ በበ​ላ​ችሁ ቀን፥ ዐይ​ኖ​ቻ​ችሁ እን​ዲ​ከ​ፈቱ፥ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ደ​ም​ት​ሆኑ፥ መል​ካ​ም​ንና ክፉን እን​ደ​ም​ታ​ውቁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ​ሚ​ያ​ውቅ ነው እንጂ።”


ነገር ግን በበ​ረታ ጊዜ ለጥ​ፋት ልቡ ታበየ፤ አም​ላ​ኩ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በደለ፤ በዕ​ጣን መሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ ያጥን ዘንድ ወደ መቅ​ደስ ገባ።


አቤቱ፥ የሕግ መም​ህ​ርን በላ​ያ​ቸው ላይ ሹም፤ አሕ​ዛ​ብም ሰዎች እንደ ሆኑ ይወቁ።


ከጥል በፊት ስድብ ይቀድማል፥ ከመውደቅም በፊት ክፋትን ማወቅ።


ከመውደቅ በፊት የሰው ልቡ ከፍ ከፍ ይላል፥ ሳይከብርም ይዋረዳል።


የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን በት​ዕ​ቢ​ተ​ኛ​ውና በኵ​ራ​ተ​ኛው ሁሉ ላይ ከፍ ባለ​ውም ላይ ይሆ​ናል፤ እነ​ር​ሱም ይዋ​ረ​ዳሉ፤


በጢ​ሮስ ላይ ይህን የመ​ከረ ማን ነው? እር​ስዋ ከሁሉ የም​ት​ሻ​ልና የም​ት​በ​ልጥ አይ​ደ​ለ​ች​ምን? ነጋ​ዴ​ዎ​ችዋ የከ​በሩ የም​ድር አለ​ቆች ናቸው።


ግብ​ፃ​ው​ያን ሰዎች እንጂ አም​ላክ አይ​ደ​ሉም፤ ፈረ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም ሥጋ እንጂ መን​ፈስ አይ​ደ​ሉም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ነ​ርሱ ላይ እጁን በዘ​ረጋ ጊዜ፥ ረጂው ይሰ​ና​ከ​ላል፤ ተረ​ጂ​ውም ይወ​ድ​ቃል፤ ሁሉም በአ​ንድ ላይ ይጠ​ፋሉ።


አሁ​ንም አንቺ ቅም​ጥል ተዘ​ል​ለሽ የም​ት​ቀ​መጪ፥ በል​ብ​ሽም፥ “እኔ ነኝ ከእ​ኔም በቀር ሌላ የለም፤ መበ​ለ​ትም ሆኜ አል​ኖ​ርም፤ የወ​ላድ መካ​ን​ነ​ት​ንም አላ​ው​ቅም” የም​ትዪ፥ ይህን ስሚ፤


እነሆ የእ​ኅ​ትሽ የሰ​ዶም ኀጢ​አት ይህ ነበረ፤ ትዕ​ቢት፥ እን​ጀ​ራን መጥ​ገብ፥ መዝ​ለ​ልና ሥራን መፍ​ታት፥ ይህ ሁሉ በእ​ር​ስ​ዋና በል​ጆ​ችዋ ነበር፤ የች​ግ​ረ​ኛ​ው​ንና የድ​ሀ​ው​ንም እጅ አላ​ጸ​ና​ችም።


በአ​ን​ቺም ላይ ሙሾ ያሞ​ሻሉ፤ እን​ዲ​ህም ይሉ​ሻል፦ በባ​ሕር የተ​ቀ​መ​ጥሽ፥ በባ​ሕ​ርም ውስጥ የጸ​ናሽ፥ ከሚ​ቀ​መ​ጡ​ብ​ሽም ጋር በዙ​ሪ​ያሽ የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ ያስ​ፈ​ራሽ፥ የከ​በ​ርሽ ከተማ ሆይ! እን​ዴት ጠፋሽ!


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦


በው​በ​ትህ ምክ​ን​ያት ልብህ ኰር​ቶ​አል፤ ከክ​ብ​ርህ የተ​ነሣ ጥበ​ብ​ህን አረ​ከ​ስህ፤ በም​ድር ላይ ጣል​ሁህ፤ ያዩ​ህም፥ ይዘ​ብ​ቱ​ብ​ህም ዘንድ በነ​ገ​ሥ​ታት ፊት አሳ​ልፌ ሰጠ​ሁህ።


አንተ ሰው ስት​ሆን ለሚ​ገ​ድ​ሉህ ሰዎች፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ ትላ​ቸ​ዋ​ለ​ህን? ሰው ነህ እንጂ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ህም።


እን​ዲ​ህም በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በወ​ን​ዞች መካ​ከል የሚ​ተኛ፥ ወንዙ የእኔ ነው፤ ለራ​ሴም ሠር​ቼ​ዋ​ለሁ የሚል ታላቅ ዘንዶ የግ​ብፅ ንጉሥ ፈር​ዖን ሆይ! እነሆ በአ​ንተ ላይ ነኝ።


የግ​ብ​ፅም ምድር ባድ​ማና ውድማ ትሆ​ና​ለች፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ፤ አንተ፦ ወንዙ የእኔ ነው፤ የሠ​ራ​ሁ​ትም እኔ ነኝ ብለ​ሃ​ልና።


“ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ቁመ​ትህ ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና፥ ራስ​ህም በደ​መ​ናት መካ​ከል ደር​ሶ​አ​ልና፤ ትዕ​ቢ​ቱ​ንም አየሁ፤


እነሆ፥ ነፍሱ ኰርታለች፥ በውስጡም ቅን አይደለችም፣ ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል።


ተዘልላ የተቀመጠች፥ በልብዋም፦ እኔ ነኝ፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለም ያለች ደስተኛይቱ ከተማ ይህች ናት፣ አራዊት የሚመሰጉባት ባድማ እንዴት ሆነች! በእርስዋ በኩል የሚያልፈው ሁሉ እጁን እያወዛወዘ ያፍዋጫል።


ደግሞም በዳርቻዋ ባለችው በሐማት ላይ፥ እጅግ ጠቢበኞች በሆኑ በጢሮስና በሲዶና ላይ ነው።


በኋላ ያ አን​ተ​ንም እር​ሱ​ንም የጠራ መጥቶ፦ ይህን ቦታ ለእ​ርሱ ተው​ለት ይል​ሃ​ልና፤ ያን​ጊ​ዜም አፍ​ረህ ትመ​ለ​ሳ​ለህ፤ ወደ ዝቅ​ተኛ ቦታም ትወ​ር​ዳ​ለህ።


ከግ​ብፅ ምድር ከባ​ር​ነት ቤት ያወ​ጣ​ህን፥


“እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤” ብሎ አዋጅ እየነገረ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እስኪቀመጥ ድረስ፥ አምላክ ከተባለው ሁሉ፥ ሰዎችም ከሚያመልኩት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርገው ተቃዋሚ እርሱ ነው።


በትዕቢት ተነፍቶ በዲያቢሎስ ፍርድ እንዳይወድቅ፥ አዲስ ክርስቲያን አይሁን።


እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ልበሱ፤ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል።


በመንፈስም ወደ በረሓ ወሰደኝ፤ የስድብም ስሞች በሞሉበት፥ ሰባት ራሶችና ዐሥር ቀንዶችም ባሉበት በቀይ አውሬ ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ አየሁ።


ራስዋን እንደ አከበረችና እንደ ተቀማጠለች ልክ ሥቃይና ሐዘን ስጡአት። በልብዋ ‘ንግሥት ሆኜ እቀመጣለሁ፤ ባልቴትም አልሆንም፤ ሐዘንም ከቶ አላይም፤’ ስላለች፥


跟着我们:

广告


广告