Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 28:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 በበ​ደ​ልህ ብዛት፥ በን​ግ​ድ​ህም ኀጢ​አት መቅ​ደ​ስ​ህን አረ​ከ​ስህ፤ ስለ​ዚህ እሳ​ትን ከው​ስ​ጥህ አው​ጥ​ቻ​ለሁ፤ እር​ስ​ዋም በል​ታ​ሃ​ለች፤ በሚ​ያ​ዩ​ህም ሁሉ ፊት በም​ድር ላይ አመድ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 በኀጢአትህና በተጭበረበረው ንግድህ ብዛት፣ መቅደስህን አረከስህ። ስለዚህ እሳት ከአንተ እንዲወጣ አደረግሁ፤ እርሱም በላህ፤ በሚመለከቱህ ሁሉ ፊት፣ በምድር ላይ ዐመድ አደረግሁህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 በበደልህ ብዛት በንግድህም ኃጢአት መቅደስህን አረከሰህ፤ ስለዚህ እሳትን ከውስጥህ አውጥቻለሁ እርሷም በልታሃለች፥ በሚያዩህም ሁሉ ፊት በምድር ላይ አመድ አድርጌሃለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 በመግዛትና በመሸጥ ከፈጸምከው በደል የተነሣ የአምልኮ ስፍራዎችህ ሁሉ ረከሱ፤ ስለዚህ በከተማይቱ የሰደድ እሳት እንዲነሣ አድርጌ በሙሉ አቃጠልኳት፤ አሁን ወደ አንተ የሚመለከቱ ሁሉ ዐመድ ብቻ መሆንክን ያያሉ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 በበደልህ ብዛት በንግድህም ኃጢአት መቅደስህን አረከሰህ፥ ስለዚህ እሳትን ከውስጥህ አውጥቻለሁ እርስዋም በልታሃለች፥ በሚያዩህም ሁሉ ፊት በምድር ላይ አመድ አድርጌሃለሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 28:18
17 交叉引用  

ምድ​ርም ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሳት ሰውም ሁሉ በሰ​ይፉ ይፈ​ረ​ድ​ባ​ቸ​ዋል፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተቀ​ሥ​ፈው የሞ​ቱት ይበ​ዛሉ።


ከተ​ፈ​ጠ​ር​ህ​በት ቀን ጀም​ረህ በደል እስ​ከ​ሚ​ገ​ኝ​ብህ ድረስ በመ​ን​ገ​ድህ ፍጹም ነበ​ርህ።


በን​ግ​ድ​ህም ብዛት ግፍ በው​ስ​ጥህ ተሞላ፤ ኀጢ​አ​ት​ንም ሠራህ፤ ስለ​ዚህ እንደ ርኩስ ነገር ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራራ ጣል​ሁህ፤ የም​ት​ጋ​ርድ ኪሩብ ሆይ! ከእ​ሳት ድን​ጋ​ዮች መካ​ከል አጠ​ፋ​ሁህ።


“አንተ የሰው ልጅ ሆይ! የጢ​ሮ​ስን አለቃ እን​ዲህ በለው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ልብህ ኰር​ት​ዋል፥ አንተ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በባ​ሕር መካ​ከል እን​ዲ​ቀ​መጥ እኔም ተቀ​ም​ጫ​ለሁ ብለ​ሃ​ልና፤ አንተ ሰው ስት​ሆን ልብ​ህን እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልብ ብታ​ደ​ር​ግም አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ህም።


ከእ​ነ​ር​ሱም ደግሞ ወስ​ደህ በእ​ሳት ውስጥ ትጥ​ላ​ለህ፤ በእ​ሳ​ትም ታቃ​ጥ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ከእ​ር​ስ​ዋም እሳት ይወ​ጣል፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ቤት ሁሉ እን​ዲህ ትላ​ቸ​ዋ​ለህ።”


በራባ ቅጥር ላይ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ በጦ​ር​ነት ቀን በጩ​ኸት መሠ​ረ​ቶ​ች​ዋን ትበ​ላ​ለች፤ በፍ​ጻ​ሜ​ዋም ቀን ትና​ወ​ጣ​ለች።


በሞ​ዓብ ላይ እሳ​ትን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ የከ​ተ​ሞ​ች​ዋ​ንም መሠ​ረ​ቶች ትበ​ላ​ለች፤ ሞዓ​ብም በድ​ካ​ምና በው​ካታ፥ በመ​ለ​ከ​ትም ድምፅ ይሞ​ታል፤


በይ​ሁዳ ላይ እሳ​ትን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም መሠ​ረ​ቶች ትበ​ላ​ለች።”


እነሆ፥ ጌታ ይገፍፋታል፥ በባሕርም ላይ ያለውን ብርታትዋን ይመታል፣ እርስዋም በእሳት ትበላለች።


በምሠራበት ቀን በደለኞች ከእግራችሁ ጫማ በታች አመድ ይሆናሉና እናንተ ትረግጡአቸዋላችሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል?


ኀጢአትንም ያደርጉ ዘንድ ላሉት ምሳሌ አድርጎ ከተማዎችን ሰዶምንና ገሞራን አመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎና ገልብጦ ከፈረደባቸው፥


ስለዚህ በአንድ ቀን ሞትና ሐዘን ራብም የሆኑ መቅሰፍቶችዋ ይመጣሉ፤ በእሳትም ትቃጠላለች፤ የሚፈርድባት እግዚአብሔር ብርቱ ነውና።”


ዶግም ዛፎ​ቹን፦ በእ​ው​ነት እኔን በእ​ና​ንተ ላይ ካነ​ገ​ሣ​ች​ሁኝ እሳት ከዶግ ወጥቶ የሊ​ባ​ኖ​ስን ዝግባ ካል​በ​ላው ከጥ​ላዬ በታች ታርፉ ዘንድ ኑ አለ​ቻ​ቸው።


እን​ዲህ ባይ​ሆን ግን ከአ​ቤ​ሜ​ሌክ እሳት ትውጣ፤ የሰ​ቂ​ማ​ንም ሰዎች፥ የመ​ሐ​ሎ​ን​ንም ቤት ትብላ፤ ያም ባይ​ሆን ከሰ​ቂማ ሰዎች ከመ​ሐ​ሎ​ንም ቤት እሳት ትውጣ፤ አቤ​ሜ​ሌ​ክ​ንም ትብ​ላው።”


跟着我们:

广告


广告