Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 28:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 በን​ግ​ድ​ህም ብዛት ግፍ በው​ስ​ጥህ ተሞላ፤ ኀጢ​አ​ት​ንም ሠራህ፤ ስለ​ዚህ እንደ ርኩስ ነገር ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራራ ጣል​ሁህ፤ የም​ት​ጋ​ርድ ኪሩብ ሆይ! ከእ​ሳት ድን​ጋ​ዮች መካ​ከል አጠ​ፋ​ሁህ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ንግድህ ስለ ደረጀ፣ በዐመፅ ተሞላህ፣ ኀጢአትም ሠራህ፤ ስለዚህ ከእግዚአብሔር ተራራ በውርደት አሳደድሁህ፤ ጠባቂ ኪሩብ ሆይ፤ ከእሳት ድንጋዮች መካከል አስወጣሁህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 በንግድህ ብዛት ግፍ በውስጥህ ተሞላ ኃጢአትንም ሠራህ፤ ስለዚህ እንደ ርኩስ ነገር ከእግዚአብሔር ተራራ ጣልሁህ፤ የምትጋርድ ኪሩብ ሆይ፥ ከእሳት ድንጋዮች መካከል አጠፋሁህ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 በመግዛትና በመሸጥ ተግባር ትጣደፍ ነበር፤ ይህም ሁሉ ወደ ግፍ ሥራና ወደ ኃጢአት መራህ፤ በዚህም ምክንያት የተቀደሰውን ተራራዬን ለቀህ እንድትወጣ አስገደድኩህ፤ ከነዚያ ከሚያብረቀርቁ የከበሩ ድንጋዮች መካከል ጠባቂው ኪሩብ እያባረረ አስወጣህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 በንግድህ ብዛት ግፍ በውስጥህ ተሞላ ኃጢአትንም ሠራህ፥ ስለዚህ እንደ ርኩስ ነገር ከእግዚአብሔር ተራራ ጣልሁህ፥ የምትጋርድ ኪሩብ ሆይ፥ ከእሳት ድንጋዮች መካከል አጠፋሁህ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 28:16
23 交叉引用  

አዳ​ም​ንም አስ​ወ​ጣው፤ ደስታ በሚ​ገ​ኝ​ባት በገ​ነት አን​ጻ​ርም አኖ​ረው፤ ወደ ሕይ​ወት ዛፍ የሚ​ወ​ስ​ደ​ው​ንም መን​ገድ ለመ​ጠ​በቅ የም​ት​ገ​ለ​ባ​በጥ የነ​በ​ል​ባል ሰይ​ፍን በእ​ጃ​ቸው የያዙ ኪሩ​ቤ​ልን አዘ​ዛ​ቸው።


ምድ​ርም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተበ​ላ​ሸች፤ ምድ​ርም ግፍን ተመ​ላች።


ከአ​ዛ​ዥ​ነት ሥራ​ህና ከሥ​ል​ጣ​ንህ ትሻ​ራ​ለህ።


የክ​ቡ​ራ​ንን ትዕ​ቢት ይሽር ዘንድ፥ የም​ድ​ር​ንም ክቡ​ራን ሁሉ ያዋ​ርድ ዘንድ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወስ​ኖ​ታል።


አንተ ልት​ጋ​ርድ የተ​ቀ​ባህ ኪሩብ ነበ​ርህ፤ በተ​ቀ​ደ​ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራራ ላይ አኖ​ር​ሁህ፤ በእ​ሳት ድን​ጋ​ዮች መካ​ከል ተመ​ላ​ለ​ስህ።


እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ይህን አይ​ተ​ሃ​ልን? በዚህ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ይህን ኀጢ​አት ያደ​ርጉ ዘንድ ለይ​ሁዳ ቤት ጥቂት ነገር ነውን? ምድ​ሪ​ቱን በኀ​ጢ​አት ሞል​ተ​ዋ​ታል፤ ያስ​ቈ​ጡ​ኝም ዘንድ ተመ​ል​ሰ​ዋል፤ እነ​ሆም ቅር​ን​ጫ​ፉን አስ​ረ​ዝ​መ​ዋል። ይዘ​ባ​በ​ታ​ሉም።


ስለ​ዚህ ወደ አም​ላ​ክህ ተመ​ለስ፤ ምሕ​ረ​ት​ንና ፍር​ድን ጠብቅ፤ ዘወ​ት​ርም ወደ አም​ላ​ክህ ቅረብ።


በፋ​ርስ ሀገ​ሮ​ችና በግ​ብፅ ሀገ​ሮች ዐው​ጁና፥ “በሰ​ማ​ርያ ተራ​ሮች ላይ ተሰ​ብ​ሰቡ፤ በው​ስ​ጥ​ዋም የሆ​ነ​ውን ታላ​ቁን ተአ​ምር፥ በመ​ካ​ካ​ል​ዋም ያለ​ውን ግፍ ተመ​ል​ከቱ” በሉ።


በተ​ሰ​ነ​ጠ​ቀም ዓለት ውስጥ እን​ደ​ሚ​ኖር- ማደ​ሪ​ያ​ው​ንም ከፍ ከፍ እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ርግ፥ በል​ቡም፦ ወደ ምድር የሚ​ያ​ወ​ር​ደኝ ማን ነው? እን​ደ​ሚል፥ የል​ብህ ትዕ​ቢት እጅግ አኵ​ር​ቶ​ሃል።


በዚህ ዕረፍት የላችሁምና ተነሥታችሁ ሂዱ፥ በርኵሰት ምክንያት ክፉ ጥፋት ታጠፋችኋለች።


በእርሻው ላይ ይመኛሉ፥ በግዴታም ይይዙታል፥ በቤቶችም ላይ ይመኛሉ፥ ይወስዱአቸውማል፥ ሰውንና ቤቱን፥ ሰውንና ርስቱንም ይነጥቃሉ።


ባለ ጠጎችዋን ግፍ ሞልቶባቸዋል፥ በእርስዋም የሚኖሩ በሐሰት ተናግረዋል፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ተንኰለኛ ነው።


የሰውንም ደም ስላፈሰስህ፥ በምድሪቱና በከተማይቱም በእርስዋም በሚኖሩ ሁሉ ላይ ስላደረግኸው ግፍ፥ በሊባኖስ ላይ የሠራኸው ግፍ ይከድንሃል፣ የአራዊትም አደጋ ያስፈራራሃል።


የሰውን ደም ስላፈሰስህ፥ በምድሪቱና በከተማይቱም በእርስዋም በሚኖሩ ሁሉ ላይ ስላደረግኸው ግፍ፥ አንተ ብዙዎችን አሕዛብን በዝብዘሃልና ከአሕዛብ የቀሩት ሁሉ ይበዘብዙሃል።


በዚያም ቀን በመድረኩ ላይ የሚዘልሉትን፥ የጌታቸውን ቤት ዓመፃንና ሽንገላን የሚሞሉትን እቀጣለሁ።


ርግብ ሻጮ​ች​ንም፥ “ይህን ከዚህ አውጡ፤ የአ​ባ​ቴን ቤት የን​ግድ ቤት አታ​ድ​ርጉ” አላ​ቸው።


ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ፤ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።


跟着我们:

广告


广告