Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 27:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በባ​ሕር መግ​ቢያ የም​ት​ኖር፥ በብ​ዙም ደሴ​ቶች ላይ ከሚ​ኖሩ አሕ​ዛብ ጋር ንግ​ድን የም​ታ​ደ​ርግ ጢሮ​ስን እን​ዲህ በላት፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጢሮስ ሆይ! አንቺ፦ በው​በት ፍጹም ነኝ ብለ​ሻል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በባሕር መግቢያ ላይ ለምትገኘውና በብዙ ጠረፎች ከሚኖሩ ሕዝቦች ጋራ ለምትነግደው ለጢሮስ እንዲህ በላት፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ጢሮስ ሆይ፤ “ፍጹም ውብ ነኝ” ብለሻል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በባሕር መግቢያ ለምትኖረውና፥ በብዙ ደሴቶች ላይ ከሚኖሩ ሕዝቦች ጋር ለምትነግደው ጢሮስ እንዲህ በላት፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጢሮስ ሆይ፥ አንቺ፦ “በውበት ፍጹም ነኝ” ብለሻል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ወደ ባሕር መግቢያ በሚወስደው መንገድ ላይ ተቀምጣ ከተለያዩ የጠረፍ ከተሞች ለሚመጡ ነጋዴዎች አገናኝ ለሆነችው ለጢሮስ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ንገራት፦ ‘ጢሮስ ሆይ! በፍጹም ውብ ነኝ ብለሻል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በባሕር መግቢያ የምትኖር በብዙም ደሴቶች ላይ ከሚኖሩ አሕዛብ ጋር ንግድን የምታደርግ ጢሮስንም እንዲህ በላት፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጢሮስ ሆይ፥ አንቺ፦ በውበት ፍጹም ነኝ ብለሻል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 27:3
15 交叉引用  

ከበ​ደሌ ፈጽሞ እጠ​በኝ፥ ከኀ​ጢ​አ​ቴም አን​ጻኝ፤


ከኀ​ይል ወደ ኀይ​ልም ይሄ​ዳል፥ የአ​ማ​ል​ክት አም​ላክ በጽ​ዮን ይታ​ያል።


ነገ​ሥ​ታ​ቱን ያበ​ሳ​ጨ​ቻ​ቸው የባ​ሕር ሰዎች እጃ​ቸው ትደ​ክ​ማ​ለች፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የከ​ነ​ዓ​ንን ኀይል ያጠፉ ዘንድ አዘዘ።


“ነገር ግን በው​በ​ትሽ ታም​ነ​ሻል፤ በስ​ም​ሽም አመ​ን​ዝ​ረ​ሻል፤ ምን​ዝ​ር​ና​ሽ​ንም ከመ​ን​ገድ አላፊ ሁሉ ጋር አበ​ዛሽ።


ገን​ዘ​ብ​ሽን ይበ​ረ​ብ​ራሉ፤ መን​ጋ​ሽ​ንም ይዘ​ር​ፋሉ፤ አም​ባ​ሽ​ንም ይን​ዳሉ፤ የተ​ወ​ደዱ ቤቶ​ች​ሽ​ንም ያፈ​ር​ሳሉ፤ እን​ጨ​ቶ​ች​ሽ​ንና ድን​ጋ​ይ​ሽን፥ መሬ​ት​ሽ​ንም በባ​ሕሩ ጥልቅ ውስጥ ይጥ​ሉ​ታል።


በአ​ን​ቺም ላይ ሙሾ ያሞ​ሻሉ፤ እን​ዲ​ህም ይሉ​ሻል፦ በባ​ሕር የተ​ቀ​መ​ጥሽ፥ በባ​ሕ​ርም ውስጥ የጸ​ናሽ፥ ከሚ​ቀ​መ​ጡ​ብ​ሽም ጋር በዙ​ሪ​ያሽ የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ ያስ​ፈ​ራሽ፥ የከ​በ​ርሽ ከተማ ሆይ! እን​ዴት ጠፋሽ!


ዳር​ቻሽ በባ​ሕር ውስጥ ነው፤ ልጆ​ች​ሽም ውበ​ት​ሽን ፈጽ​መ​ዋል።


አሕዛብ ሁሉ ከዝሙትዋ ቍጣ ወይን ጠጅ የተነሣ ወድቀዋልና፤ የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ፤ የምድርም ነጋዴዎች ከቅምጥልነትዋ ኀይል የተነሣ ባለጠጋዎች ሆኑ፤” ብሎ ጮኸ።


跟着我们:

广告


广告