ሕዝቅኤል 26:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 እርሱ በምድረ በዳ ያሉ ሴቶች ልጆችሽን በሰይፍ ይገድላቸዋል፤ ጠባቂዎችንም በአንቺ ላይ ያስቀምጣል፤ በዙሪያሽም ግንብ ይሠራል፤ የጦር መሣሪያም ይዘው ይከቡሻል፤ በጦራቸውም ይወጉሻል፤ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም8 እርሱ መኻል አገር ያሉ ሰፈሮችሽን በሰይፍ ያወድማቸዋል፤ በዙሪያሽ ካብ ይክባል፤ እስከ ቅጥሮችሽ ጫፍ ድረስ ዐፈር ይደለድልብሻል፤ ጋሻውንም በአንቺ ላይ ያነሣል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 በሜዳ ያሉትን ሴቶችን ልጆችሽን በሰይፍ ይገድላቸዋል፤ በአንቺ ላይ ምሽግ ይሠራል፥ ደለልም በአንቺ ላይ ይደለድላል፥ በአንቺም ላይ ጋሻ ያነሣል። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 በዋናይቱ ምድር ባሉት መንደሮች ነዋሪ የሆኑ ሕዝብ ሁሉ በጦርነት ያልቃሉ፤ እናንተን የሚከላከልበት ምሽግ ይሠራል። ጠላትም እስከ ቅጽሮችሽ ጫፍ ዐፈር ይደለድላል፤ በጋሻም ብዛት እየተከላከለ ያጠቃችኋል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 በሜዳ ያሉትን ሴቶችን ልጆችሽን በሰይፍ ይገድላቸዋል፥ አምባም ይሠራብሻል አፈርንም ይደለድልብሻል ጋሻም ያነሣብሻል። 参见章节 |