Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 26:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ጢሮስ ሆይ! እነሆ ከሰ​ሜን የነ​ገ​ሥ​ታት ንጉሥ የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርን ከፈ​ረ​ሶ​ችና ከሰ​ረ​ገ​ሎች፥ ከፈ​ረ​ሰ​ኞ​ችም፥ ከጉ​ባ​ኤና ከብዙ ሕዝ​ብም ጋር በአ​ንቺ ላይ አመ​ጣ​ለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ‘የነገሥታት ንጉሥ የሆነውን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን ከፈረሶችና ከሠረገሎች ጋራ፣ ከፈረሰኞችና ከታላቅ ሰራዊትም ጋራ ከሰሜን በጢሮስ ላይ አመጣለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ ከሰሜን የነገሥታት ንጉሥ የሆነውን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነዖርን ከፈረሶች፥ ከሰረገሎች፥ ከፈረሰኞች፥ ከጉባኤና ከብዙ ሕዝብ ጋር በጢሮስ ላይ አመጣለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በጢሮስ ላይ አደጋ እንዲጥል የነገሥታት ንጉሥ የሆነውን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን ከሰሜን በኩል አመጣባታለሁ፤ እርሱም ከታላቅ ሠራዊት ጋር በብዙ ፈረሶችና ሠረገሎች በፈረሰኞችም ታጅቦ ይመጣል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ ከሰሜን የነገሥታት ንጉሥ የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነዖርን ከፈረሶችና ከሰረገሎች ከፈረሰኞችም ከጉባኤና ከብዙ ሕዝብ ጋር በጢሮስ ላይ አመጣለሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 26:7
22 交叉引用  

“ከን​ጉሠ ነገ​ሥት ከአ​ር​ተ​ሰ​ስታ ለሰ​ማይ አም​ላክ ሕግ ጸሓፊ ለካ​ህኑ ለዕ​ዝራ፥ ሰላም ይሁን፤


“አንተ ብቻ​ህን አለቃ ነህን?” ቢሉ​ትም፥ የሔ​ማ​ትን መን​ደር ወሰ​ድሁ ይላል።


የጢ​ሮ​ስ​ንም ነገ​ሥ​ታት ሁሉ፥ የሲ​ዶ​ና​ንም ነገ​ሥ​ታት ሁሉ፥ በባ​ሕር ማዶ ያሉ የደ​ሴት ነገ​ሥ​ታ​ት​ንም፤


እነሆ ልኬ የሰ​ሜ​ንን ወገ​ኖች ሁሉ፤ ባሪ​ያ​ዬ​ንም የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርን እወ​ስ​ዳ​ለሁ፤ በዚ​ችም ምድ​ርና በሚ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ትም ሰዎች ላይ፥ በዙ​ሪ​ያ​ዋም ባሉ በእ​ነ​ዚህ አሕ​ዛብ ሁሉ ላይ አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ፈጽ​ሜም አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ለጥ​ፋ​ትና ለፉ​ጨት ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ዕፍ​ረት ባድማ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ።


እነሆ! እንደ ደመና ይወ​ጣል፤ ሰረ​ገ​ሎ​ቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ናቸው፤ ፈረ​ሶ​ቹም ከን​ስር ይልቅ ፈጣ​ኖች ናቸው። ተዋ​ር​ደ​ና​ልና ወዮ​ልን።


አን​በሳ ከጕ​ድ​ጓዱ ወጥ​ቶ​አል፤ አሕ​ዛ​ብ​ንም ሊያ​ጠ​ፋ​ቸው የሚ​ዘ​ርፍ ተነ​ሥ​ቶ​አል፤ ምድ​ር​ሽን ባድማ ያደ​ርግ ዘንድ፥ ከተ​ሞ​ች​ሽ​ንም ሰው እን​ዳ​ይ​ኖ​ር​ባ​ቸው ያፈ​ር​ሳ​ቸው ዘንድ ከስ​ፍ​ራው ወጥ​ቶ​አል።


በመ​ል​ካ​ምም ተና​ገ​ረው፤ ዙፋ​ኑ​ንም ከእ​ርሱ ጋር በባ​ቢ​ሎን ከነ​በ​ሩት ነገ​ሥ​ታት ዙፋን በላይ አደ​ረ​ገ​ለት።


ቀስ​ት​ንና ጦርን ይይ​ዛሉ፤ ጨካ​ኞች ናቸው፤ ምሕ​ረ​ትም አያ​ደ​ር​ጉም፤ ድም​ፃ​ቸው እንደ ባሕር ሞገድ ይተ​ም​ማል፤ በሰ​ረ​ገ​ላና በፈ​ረ​ሶ​ችም ላይ ይቀ​መ​ጣሉ፤ የጽ​ዮን ሴት ልጅ ሆይ! እንደ እሳት ያጠ​ፉ​ሻል።


ይኸ​ውም መን​ግ​ሥቱ እን​ድ​ቷ​ረ​ድና ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ከፍ እን​ዳ​ትል፥ ቃል ኪዳ​ኑን በመ​ጠ​በቅ ጸንታ እን​ድ​ት​ኖር ነው።


ስማ​ቸ​ውን ያስ​ጠሩ ሰዎች ሁሉ በመ​ን​ኰ​ራ​ኵ​ርና በሠ​ረ​ገላ፥ በአ​ሕ​ዛ​ብም ጉባኤ ይመ​ጡ​ብ​ሻል፤ ጋሻና አላ​ባሽ ጋሻ፥ ራስ ቍርም ይዘው በዙ​ሪ​ያሽ ጥበቃ ያደ​ር​ጋሉ፤ ፍር​ድ​ንም እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እንደ ፍር​ዳ​ቸ​ውም ይፈ​ር​ዱ​ብ​ሻል።


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጢሮስ ሆይ! እነሆ በአ​ንቺ ላይ ነኝ፤ ባሕ​ርም ሞገ​ድ​ዋን እን​ደ​ም​ታ​ወጣ እን​ዲሁ ብዙ አሕ​ዛ​ብን አወ​ጣ​ብ​ሻ​ለሁ።


ስለ​ዚህ እነሆ የሌላ ሀገር ሰዎ​ችን፥ የአ​ሕ​ዛብ ጨካ​ኞ​ችን አመ​ጣ​ብ​ሃ​ለሁ፤ ሰይ​ፋ​ቸ​ው​ንም በጥ​በ​ብህ ውበት ላይ ይመ​ዝ​ዛሉ፤ ክብ​ር​ህ​ንም ያረ​ክ​ሳሉ።


ስለ​ዚህ ለአ​ሕ​ዛብ አል​ፈው ይሰ​ጣሉ፤ እኔም አሁን እቀ​በ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ንጉ​ሥ​ንና አለ​ቆ​ች​ንም ይቀቡ ዘንድ ፈጽ​መው ያን​ሣሉ።


跟着我们:

广告


广告