Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 26:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 የባ​ሕ​ርም አለ​ቆች ሁሉ ከዙ​ፋ​ኖ​ቻ​ቸው ይወ​ር​ዳሉ፤ ዘው​ዳ​ቸ​ውን ከራ​ሳ​ቸው ያወ​ር​ዳሉ፤ ወርቀ ዘቦ ልብ​ሳ​ቸ​ውን ያወ​ል​ቃሉ፤ በመ​ሬ​ትም ላይ ተቀ​ም​ጠው ይደ​ነ​ግ​ጣሉ፤ ሞታ​ቸ​ው​ንም ይፈ​ራሉ፤ ስለ አን​ቺም ያለ​ቅ​ሳሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 የባሕር ጠረፍ መሳፍንት ሁሉ ከዙፋኖቻቸው ይወርዳሉ፤ መጐናጸፊያቸውን ይጥላሉ፤ ወርቀ ዘቦ ልብሳቸውን ያወልቃሉ። ፍርሀት ተከናንበው በመሬት ላይ በመቀመጥ ባለማቋረጥ፣ እየተንቀጠቀጡ በአንቺ ላይ በደረሰው ነገር ይሸበራሉ፤’

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 በዚያን ጊዜ የባሕር አለቆች ሁሉ ከዙፋኖቻቸው ይወርዳሉ፤ መጐናጸፊያቸውን ያስቀምጣሉ፥ ወርቀዘቦ ልብሳቸውንም ያወልቃሉ፤ መንቀጥቀጥን ይለብሳሉ፥ በመሬት ላይ ይቀመጣሉ፥ ሁልጊዜም ይንቀጠቀጣሉ፥ በአንቺም ይደነቃሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 በባሕር አጠገብ ያሉ አገሮች ነገሥታት ሁሉ ከዙፋናቸው ይወርዳሉ፤ መጐናጸፊያቸውንና በእጅ ሥራ ጥልፍ ያጌጠ ልብሳቸውን አውልቀው በፍርሃት እየተንቀጠቀጡ መሬት ላይ ይቀመጣሉ፤ በአንቺ ላይ የደረሰውን አሠቃቂ ሁኔታ እያሰቡ በብርቱ ይሸበራሉ፤ በአንቺም ሁኔታ ይደነግጣሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 የባሕርም አለቆች ሁሉ ከዙፋኖቻቸው ይወርዳሉ፥ መጐናጸፊያቸውን ያወጣሉ ወርቀዘቦ ልብሳቸውንም ያወልቃሉ፥ መንቀጥቀጥን ለብሰው በመሬት ላይ ይቀመጣሉ፥ ሁልጊዜም ይንቀጠቀጣሉ በአንቺም ይደነቃሉ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 26:16
32 交叉引用  

ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ኀፍ​ረ​ትን ይለ​ብ​ሳሉ፤ የኀ​ጢ​ኣ​ተ​ኞ​ችም ቤት ይጠ​ፋል።”


ያን ጊዜ የኤ​ዶም አለ​ቆች ሸሹ፤ የሞ​ዓ​ብ​ንም አለ​ቆች መን​ቀ​ጠ​ቀጥ ያዛ​ቸው፤ በከ​ነ​ዓን የሚ​ኖሩ ሁሉ ቀለጡ።


የጌ​ጦ​ች​ሽም ሣጥ​ኖች ያለ​ቅ​ሳሉ፤ ይዋ​ረ​ዳ​ሉም፤ ብቻ​ሽ​ንም ትቀ​ሪ​ያ​ለሽ፤ ከም​ድ​ርም ጋር ትቀ​ላ​ቀ​ያ​ለሽ።”


አሕ​ዛብ አይ​ተው ፈሩ። የም​ድ​ርም ዳር​ቾች ቀረቡ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ቀረቡ፤ መጡም።


አንቺ ድን​ግል የባ​ቢ​ሎን ልጅ ሆይ፥ ውረጂ፤ በት​ቢ​ያም ላይ ተቀ​መጪ፤ የከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሴት ልጅ ሆይ፥ ከዚህ በኋላ ለስ​ላ​ሳና ቅም​ጥል አት​ባ​ዪ​ምና ያለ ዙፋን በመ​ሬት ላይ ተቀ​መጪ።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ትቢ​ያን አራ​ግፊ፤ ተነሺ፥ ተቀ​መጪ፤ ምር​ኮ​ኛ​ዪቱ የጽ​ዮን ልጅ ሆይ፥ የአ​ን​ገ​ት​ሽን እስ​ራት ፍቺ።


እን​ዴት ተለ​ወ​ጠች! ከእ​ፍ​ረ​ትም የተ​ነሣ ሞአብ ጀር​ባ​ዋን እን​ዴት መለ​ሰች! ሞአ​ብም በዙ​ሪ​ያዋ ላሉት ሁሉ መሳ​ቂ​ያና መሳ​ለ​ቂያ ትሆ​ና​ለች።


ዮድ። የጽ​ዮን ሴት ልጅ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ዝም ብለው በመ​ሬት ላይ ተቀ​ም​ጠ​ዋል፤ ትቢ​ያን በራ​ሳ​ቸው ላይ ነሰ​ነሱ፤ ማቅም ታጠቁ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መሳ​ፍ​ን​ቱ​ንና ደና​ግ​ሉን ወደ ምድር አወ​ረ​ዷ​ቸው።


ወርቀ ዘቦም አለ​በ​ስ​ሁሽ፤ ጥቁር ጫማም አደ​ረ​ግ​ሁ​ልሽ፤ በጥሩ በፍታ አስ​ታ​ጠ​ቅ​ሁሽ፤ በሐ​ርም ከደ​ን​ሁሽ።


ለሞት እሰ​ጥ​ሻ​ለሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም አት​ኖ​ሪም፤ ይፈ​ል​ጉ​ሻል፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም አያ​ገ​ኙ​ሽም፤ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”


በው​በ​ትህ ምክ​ን​ያት ልብህ ኰር​ቶ​አል፤ ከክ​ብ​ርህ የተ​ነሣ ጥበ​ብ​ህን አረ​ከ​ስህ፤ በም​ድር ላይ ጣል​ሁህ፤ ያዩ​ህም፥ ይዘ​ብ​ቱ​ብ​ህም ዘንድ በነ​ገ​ሥ​ታት ፊት አሳ​ልፌ ሰጠ​ሁህ።


“ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ወደ ሲኦል በወ​ረ​ደ​በት ቀን ልቅ​ሶን አስ​ለ​ቀ​ስሁ፤ ቀላ​ዩ​ንም ስለ እርሱ ሸፈ​ን​ሁት፤ ፈሳ​ሾ​ች​ንም ከለ​ከ​ልሁ፤ ታላ​ላ​ቆ​ችም ውኆች ተከ​ለ​ከሉ፤ ሊባ​ኖ​ስ​ንም ስለ እርሱ አሳ​ዘ​ን​ሁት። የዱ​ርም ዛፎች ሁሉ ስለ እርሱ ዛሉ።


ብዙ አሕ​ዛ​ብን አስ​ደ​ን​ቅ​ብ​ሃ​ለሁ፤ ሰይ​ፌም በፊ​ታ​ቸው በተ​ወ​ረ​ወ​ረች ጊዜ ንጉ​ሦ​ቻ​ቸው እጅግ አድ​ር​ገው ይፈ​ራሉ፤ በወ​ደ​ቅ​ህ​ባ​ትም ቀን እያ​ን​ዳ​ንዱ ስለ ነፍሱ በየ​ጊ​ዜው ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣል።”


ንጉ​ሡም ያለ​ቅ​ሳል፥ አለ​ቃም ውር​ደ​ትን ይለ​ብ​ሳል፤ የም​ድ​ርም ሕዝብ እጅ ትሰ​ላ​ለች፤ እንደ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውም መጠን አደ​ር​ግ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በፍ​ር​ዳ​ቸ​ውም መጠን እፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”


አሁን በቅ​ርብ መዓ​ቴን አፈ​ስ​ስ​ብ​ሻ​ለሁ፤ ቍጣ​ዬ​ንም እፈ​ጽ​ም​ብ​ሻ​ለሁ፤ እን​ደ​መ​ን​ገ​ድ​ሽም መጠን እፈ​ር​ድ​ብ​ሻ​ለሁ፤ ጕስ​ቍ​ል​ና​ሽ​ንም ሁሉ አመ​ጣ​ብ​ሻ​ለሁ።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እከ​ተ​ለው ዘንድ እሄ​ዳ​ለሁ፤ እርሱ ያድ​ነ​ና​ልና፤ እር​ሱም እንደ አን​በሳ ያገ​ሣል፤ የውኃ ልጆ​ችም ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።


ወሬ​ውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፤ እር​ሱም ከዙ​ፋኑ ተነ​ሥቶ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ውን አወ​ለቀ፤ ማቅም ለበሰ፤ በአ​መ​ድም ላይ ተቀ​መጠ።


የመንግሥታትንም ዙፋን እገለብጣለሁ፥ የአሕዛብንም መንግሥታት ኃይል አጠፋለሁ፣ ሰረገሎችንና የሚቀመጡባቸውንም እገለብጣለሁ፣ ፈረሶችና ፈረሰኞቻቸውም እያንዳንዳቸው በወንድማቸው ሰይፍ ይወድቃሉ።


እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ልበሱ፤ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል።


ከእርስዋም ጋር የሴሰኑና የተቀማጠሉ የምድር ነገሥታት የመቃጠልዋን ጢስ ሲያዩ ስለ እርስዋ እየጮሁ እያሉ ያለቅሳሉ፤


跟着我们:

广告


广告