Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 25:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ስለ​ዚህ እነሆ እጄን ዘር​ግ​ቼ​ብ​ሃ​ለሁ፤ ለአ​ሕ​ዛ​ብም አስ​በ​ዘ​ብ​ዝ​ሃ​ለሁ፤ ከአ​ሕ​ዛ​ብም ለይች እቈ​ር​ጥ​ሃ​ለሁ፤ ከሀ​ገ​ሮ​ችም እደ​መ​ስ​ስ​ሃ​ለሁ፤ አጠ​ፋ​ሃ​ለ​ሁም፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ለህ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ክንዴን በእናንተ ላይ አነሣለሁ፤ በአሕዛብ እንድትበዘበዙ አደርጋለሁ፤ ከሕዝቦች መካከል አውጥቼ፣ ከአገሮችም ለይቼ አጠፋችኋለሁ፤ እደመስሳችኋለሁም። በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ስለዚህ እነሆ እጄን በአንተ ላይ ዘርግቻለሁ፥ እንዲበዘብዙህ ለሕዝቦች እሰጥሃለሁ፥ ከሕዝቦች እቆርጥሃለሁ፥ ከአገሮችም እደመስስሃለሁ፤ አጠፋሃለሁም፥ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃለህ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ይህንንም በማድረጋችሁ ኀይሌን እገልጥላችኋለሁ፤ በምርኮኛነት ለሕዝቦች አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ ዳግመኛ በሕዝብነት የማትታወቁ እስክትሆኑ ድረስ ጨርሼ አጠፋችኋለሁ፤ ከዚያ በኋላ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ስለዚህ፥ እነሆ፥ እጄን ዘርግቼብሃለህ፥ ለአሕዛብም አስበዘብዝሃለሁ፥ ከአሕዛብም ለይቼ እቈርጥሃለሁ፥ ከአገሮችም አጠፋሃለሁ እፈጅህማለሁ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃለህ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 25:7
14 交叉引用  

አን​በጣ እን​ደ​ሚ​ሰ​በ​ሰብ ትን​ሹም ትል​ቁም ምር​ኮ​አ​ችሁ እን​ዲሁ ይሰ​በ​ሰ​ብ​ላ​ች​ኋል።


ስለ​ዚህ እነሆ በአ​ሞን ልጆች ከተማ በራ​ባት ላይ የሰ​ልፍ ውካ​ታን የማ​ሰ​ማ​በት ዘመን ይመ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ለጥ​ፋ​ትም ትሆ​ና​ለች፥ መን​ደ​ሮ​ች​ዋም በእ​ሳት ይቃ​ጠ​ላሉ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም የወ​ረ​ሱ​ትን ይወ​ር​ሳል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ኖን። በእጄ ስለ​ተ​ታቱ ኀጢ​አ​ቶች ተጋ፤ በአ​ን​ገቴ ላይ ወጥ​ተ​ዋል፤ ጕል​በቴ ደከመ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልቋ​ቋ​መው በማ​ል​ች​ለው መከራ እጅ ሰጥ​ቶ​ኛ​ልና።


ነቢ​ዩም ቢታ​ለል፥ ቃል​ንም ቢና​ገር፥ ያን ነቢይ ያታ​ለ​ልሁ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፥ እጄ​ንም በእ​ርሱ ላይ እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ ከሕ​ዝ​ቤም ከእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል አጠ​ፋ​ዋ​ለሁ።


ቍጣ​ዬ​ንም አፈ​ስ​ስ​ብ​ሃ​ለሁ፤ በመ​ዓ​ቴም እሳት አና​ፋ​ብ​ሃ​ለሁ፤ ማጥ​ፋ​ት​ንም ለሚ​ያ​ውቁ ለጨ​ካ​ኞች ሰዎች እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።


ለእ​ሳት ማገዶ ትሆ​ና​ለህ፤ ደም​ህም በም​ድር መካ​ከል ይፈ​ስ​ሳል፤ ደግ​ሞም አት​ታ​ሰ​ብም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና።”


የአ​ሞን ልጆች በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ እን​ዳ​ይ​ታ​ሰቡ የአ​ሞ​ንን ልጆች ለም​ሥ​ራቅ ልጆች ርስት አድ​ርጌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እጄን በኤ​ዶ​ም​ያስ ላይ እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ዘንድ ሰው​ንና እን​ስ​ሳን አጠ​ፋ​ለሁ፤ ባድ​ማም አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ ከቴ​ማ​ንና ከድ​ዳ​ንም ያመ​ለጡ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ።


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ እጄን በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ላይ እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ መኳ​ን​ን​ቱ​ንም እቈ​ር​ጣ​ለሁ፤ የባ​ሕ​ሩ​ንም ዳር ቅሬታ አጠ​ፋ​ለሁ።


በባ​ሕር ውስጥ የመ​ረብ ማስጫ ትሆ​ና​ለች፤ እኔ ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ብዝ​በዛ ትሆ​ና​ለች።


እን​ዲ​ህም በለው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የሴ​ይር ተራራ ሆይ! እነሆ በአ​ንተ ላይ ነኝ፤ እጄን እዘ​ረ​ጋ​ብ​ሃ​ለሁ፤ ባድ​ማና ውድ​ማም አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ።


እጄ​ንም እዘ​ረ​ጋ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በሚ​ኖ​ሩ​በ​ትም ስፍራ ሁሉ ምድ​ሪ​ቱን ከዴ​ብ​ላታ ምድረ በዳ ይልቅ ውድ​ማና በረሃ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”


እጄንም በይሁዳ ላይ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ሁሉ ላይ እዘረጋለሁ፣ ከዚህም ስፍራ የበኣልን ቅሬታና የጣዖታቱን ካህናት ስም አጠፋለሁ፣


跟着我们:

广告


广告