Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 25:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ በእ​ጆ​ችህ አጨ​ብ​ጭ​በ​ሃ​ልና፥ በእ​ግ​ሮ​ች​ህም አሸ​ብ​ሽ​በ​ሃ​ልና፥ ሰው​ነ​ት​ህም በእ​ስ​ራ​ኤል ምድር ላይ ደስ ብሎ​አ​ታ​ልና፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ በልባችሁ ክፋት ሁሉ፣ በእስራኤል ውድቀት ላይ በመደሰት በእጃችሁ አጨብጭባችኋልና፤ በመዝለልም ጨፍራችኋልና

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በእስራኤል ምድር ላይ በውስጥሽ ባለው ንቀት ሁሉ ደስ ብሎሽ በእጅሽ አጨብጭበሻልና፥ በእግርሽም አሸብሽበሻልና፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 “ልዑል እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ በእጃችሁ በማጨብጨብና በእግራችሁም በመርገጥ የእስራኤልንም ምድር በንቀት ተመልክታችኋት ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በእጅህ አጨብጭበሃልና፥ በእግርህም አሸብሽበሃልና፥ በእስራኤልም ምድር ላይ በነፍስህ ንቀት ሁሉ ደስ ብሎሃልና

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 25:6
17 交叉引用  

በእ​ር​ሱም እጁን ያጨ​በ​ጭ​ብ​በ​ታል፤ ከስ​ፍ​ራ​ውም በፉ​ጨት ጎትቶ ያወ​ጣ​ዋል።


በኀ​ጢ​አ​ቶ​ችህ ላይ እን​ዳ​ት​ጨ​ምር፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ብዙ መና​ገር በደል ይሆ​ን​ብ​ሃል።”


ጠላትህ ቢወድቅ ደስ አይበልህ፥ በመሰናከሉም አትታበይ።


እስ​ራ​ኤል ለአ​ንተ መሳ​ቂያ አል​ሆ​ነ​ምን? ወይስ በሌ​ቦች መካ​ከል ተገ​ኝ​ቶ​አ​ልን? ስለ እርሱ በተ​ና​ገ​ርህ ጊዜ ራስ​ህን ትነ​ቀ​ን​ቃ​ለህ።


ዛይ። ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ቀድሞ ወድዳ በሠ​ራ​ችው ሥራ ሁሉ የመ​ከ​ራ​ዋን ወራት አሰ​በች፤ ሕዝ​ብዋ በአ​ስ​ጨ​ና​ቂ​ዎች እጅ በወ​ደቀ ጊዜ፥ የሚ​ረ​ዳ​ትም በሌ​ላት ጊዜ፥ አስ​ጨ​ና​ቂ​ዎች አዩ​አት፤ በመ​ፍ​ረ​ስ​ዋም ሳቁ።


ሳም​ኬት። መን​ገድ ዐላ​ፊ​ዎች ሁሉ እጃ​ቸ​ውን ያጨ​በ​ጭ​ቡ​ብ​ሻል፦ “በውኑ የም​ድር ሁሉ ደስታ፥ አክ​ሊ​ልና ክብር የሚ​ሉ​አት ከተማ ይህች ናትን?” እያሉ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሴት ልጅ ላይ ያፍ​ዋ​ጫሉ፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም ይነ​ቀ​ን​ቃሉ።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን በቀ​ልን አድ​ር​ገ​ዋ​ልና፥ በቀ​ላ​ቸ​ው​ንም አጽ​ን​ተ​ዋ​ልና፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይጠፉ ዘንድ ነፍ​ሳ​ቸው ደስ ይላ​ታ​ልና፤


ለአ​ሞ​ንም ልጆች እን​ዲህ በል፦ የጌ​ታን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ መቅ​ደሴ በረ​ከሰ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ምድር ባድማ በሆ​ነች ጊዜ፥ የይ​ሁ​ዳም ቤት በተ​ማ​ረኩ ጊዜ ስለ እነ​ርሱ ደስ ብሎ​ሃ​ልና፤


የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ርስት ባድማ ስለ ሆነ በላዩ ደስ እን​ዳ​ለህ፥ እን​ዲሁ አደ​ር​ግ​ብ​ሃ​ለሁ፤ የሴ​ይር ተራራ ሆይ! አን​ተና መላው ኤዶ​ም​ያስ ባድማ ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ለህ።”


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ያሳ​ድ​ዱ​አ​ትና ይበ​ዘ​ብ​ዙ​አት ዘንድ በል​ባ​ቸው ሁሉ ደስ​ታና በነ​ፍ​ሳ​ቸው ንቀት ምድ​ሬን ርስት አድ​ር​ገው ለራ​ሳ​ቸው በሰጡ በቀ​ሩት አሕ​ዛ​ብና በኤ​ዶ​ም​ያስ ሁሉ ላይ በቅ​ን​አቴ እሳት ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ጅህ አጨ​ብ​ጭብ፤ በእ​ግ​ር​ህም አሸ​ብ​ሽብ፤ ስለ እስ​ራ​ኤል ቤት ርኵ​ሰት ሁሉ ወዮ ወዮ በል፤ በረ​ኀ​ብና በጦር፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም ይጠ​ፋሉ።


በጠ​ላት ቀን ወን​ድ​ም​ህን ዝቅ አድ​ር​ገህ ትመ​ለ​ከ​ተው ዘንድ፥ በጥ​ፋ​ታ​ቸ​ውም ቀን በይ​ሁዳ ልጆች ላይ ደስ ይልህ ዘንድ፥ በጭ​ን​ቀ​ታ​ቸ​ውም ቀን በት​ዕ​ቢት ትና​ገር ዘንድ ባል​ተ​ገ​ባህ ነበር።


ስብራትህ አይፈወስም፥ ቁስልህም ክፉ ነው፣ ወሬህንም የሚሰሙ ሁሉ እጃቸውን በአንተ ላይ ያጨበጭባሉ፣ ክፋትህ ሁልጊዜ ያላለፈችበት ሰው ማን ነውና?


በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ አላግጠዋልና፥ እየታበዩም ተናግረዋልና ይህ ስለ ትዕቢታቸው ያገኛቸዋል።


ተዘልላ የተቀመጠች፥ በልብዋም፦ እኔ ነኝ፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለም ያለች ደስተኛይቱ ከተማ ይህች ናት፣ አራዊት የሚመሰጉባት ባድማ እንዴት ሆነች! በእርስዋ በኩል የሚያልፈው ሁሉ እጁን እያወዛወዘ ያፍዋጫል።


በሕዝቤም ላይ ያላገጡባትን፥ በድንበራቸውም ላይ እየታበዩ የተናገሩባትን የሞዓብን ማላገጥና የአሞንን ልጆች ስድብ ሰምቻለሁ።


跟着我们:

广告


广告