ሕዝቅኤል 25:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እጄን በኤዶምያስ ላይ እዘረጋለሁ፤ ከእርስዋም ዘንድ ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፤ ባድማም አደርጋታለሁ፤ ከቴማንና ከድዳንም ያመለጡ በሰይፍ ይወድቃሉ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም13 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ክንዴን በኤዶም ላይ አነሣለሁ፤ ሰዎቹንና እንስሶቻቸውን እገድላለሁ፤ ባድማ አደርጋታለሁ፤ ከቴማንም ጀምሮ እስከ ድዳን ድረስ በሰይፍ ይወድቃሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በኤዶምያስ ላይ እጄን እዘረጋለሁ፥ ከእርሷም ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፤ ባድማ አደርጋታለሁ፤ ከቴማን ጀምሮ እስከ ድዳን ድረስ በሰይፍ ይወድቃሉ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 ስለዚህ አሁን ኤዶምን እንደምቀጣና በዚያም ያሉትን ሰዎችና እንስሶች በሙሉ እንደማጠፋ አሳውቃለሁ፤ ከቴማን ከተማ እስከ ደዳን ከተማ ድረስ ባድማ እንዲሆን አደርጋለሁ፤ ሕዝቡም በጦርነት ያልቃሉ፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እጄን በኤዶምያስ ላይ እዘረጋለሁ ከእርስዋም ዘንድ ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፥ ከቴማንም ጀምሮ ባድማ አደርጋታለሁ፥ እስከ ድዳንም ድረስ በሰይፍ ይወድቃሉ። 参见章节 |