Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 23:48 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

48 ሴቶ​ችም ሁሉ እንደ ኀጢ​አ​ታ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ሠሩ ይማሩ ዘንድ ሴሰ​ኝ​ነ​ትን ከም​ድር ላይ አጠ​ፋ​ለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

48 “ስለዚህ ሴቶች ሁሉ እንዲጠነቀቁና መጥፎ ፈለጋችሁን እንዳይከተሉ፣ ሴሰኛነትን ከምድሪቱ አጠፋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

48 ሴቶችም ሁሉ እንደ አመንዝራነታችሁ እንዳይሠሩ፥ እንዲጠነቀቁ አመንዝራነትን ከምድር ላይ አጠፋለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

48 እናንተ ሁለት እኅትማማቾች እንዳመነዘራችሁ ሁሉ ሴቶች ከእንግዲህ ወዲህ እንዳያመነዝሩ መቀጣጫ ይሆን ዘንድ ከምድሪቱ ሁሉ ላይ የሴሰኝነት ስድነት እንዲወገድ አደርጋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

48 ሴቶችም ሁሉ እንደ ሴሰኝነታችሁ እንዳይሠሩ ይማሩ ዘንድ ሴሰኝነትን ከምድር ላይ አጠፋለሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 23:48
15 交叉引用  

አቤቱ፥ አም​ላኬ ሆይ፥ ትእ​ዛ​ዝህ በም​ድር ላይ ብር​ሃን ነውና ነፍሴ በሌ​ሊት ወደ አንተ ትገ​ሠ​ግ​ሣ​ለች። በም​ድር የም​ት​ኖ​ሩም ጽድቅ መሥ​ራ​ትን ተማሩ።


ቤቶ​ች​ሽ​ንም በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ላሉ፤ በብ​ዙም ሴቶች ፊት ይበ​ቀ​ሉ​ሻል፤ ግል​ሙ​ት​ና​ሽ​ንም አስ​ተ​ው​ሻ​ለሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ ዋጋ አት​ሰ​ጪም።


ወደ አሕ​ዛ​ብም እበ​ት​ን​ሻ​ለሁ፤ በሀ​ገ​ሮ​ችም እዘ​ራ​ሻ​ለሁ፤ ከአ​ን​ቺም ርኵ​ሰ​ትሽ ይጠ​ፋል።


ሴሰ​ኝ​ነ​ት​ሽ​ንም፥ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ሽ​ውን ዝሙ​ት​ሽ​ንም ከአ​ንቺ አስ​ቀ​ራ​ለሁ፤ ዐይ​ን​ሽ​ንም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ወደ እነ​ርሱ አታ​ነ​ሺም፤ ግብ​ፅ​ንም ከዚያ ወዲያ አታ​ስ​ቢም።


ጉባ​ኤ​ውም በድ​ን​ጋይ ይወ​ግ​ሩ​አ​ቸ​ዋል፤ በሰ​ይ​ፋ​ቸ​ውም ይቈ​ር​ጡ​አ​ቸ​ዋል፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይገ​ድ​ላሉ፤ ቤቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ላሉ።


እን​ግ​ዲህ በደ​ላ​ችሁ በላ​ያ​ችሁ ላይ ይመ​ለ​ሳል፤ እና​ን​ተም የጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ኀጢ​አት ትሸ​ከ​ማ​ላ​ችሁ፤ እኔም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።”


ጥሩ ውኃ​ንም እረ​ጭ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ከር​ኵ​ሰ​ታ​ችሁ ሁሉ ትነ​ጻ​ላ​ችሁ፤ ከጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሁሉ አነ​ጻ​ች​ኋ​ለሁ።


በቍ​ጣ​ዬና በመ​ቅ​ሠ​ፍቴ በተ​በ​ቀ​ል​ሁሽ ጊዜ በዙ​ሪ​ያሽ በአሉ በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ትጨ​ነ​ቂ​ያ​ለሽ፤ ትደ​ነ​ግ​ጫ​ለ​ሽም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ።


በም​ት​ኖ​ሩ​ባ​ትም ስፍራ ሁሉ ከተ​ሞች ይፈ​ር​ሳሉ፥ የኮ​ረ​ብታ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችም ሁሉ ውድማ ይሆ​ናሉ፤ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቻ​ች​ሁም ይፈ​ር​ሳሉ፤ ባድ​ማም ይሆ​ናሉ፤ ጣዖ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ይሰ​በ​ራሉ፤ ያል​ቃ​ሉም፤ የፀ​ሐይ ምስ​ሎ​ቻ​ች​ሁም ይጠ​ፋሉ፤ ሥራ​ች​ሁም ይሻ​ራል።


ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፣ የሰማይን ወፎችና የባሕርን ዓሣዎች ማሰናከያንም ከኃጢአተኞች ጋር አጠፋለሁ፣ ሰውንም ከምድር ፊት እቈርጣለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።


እስ​ራ​ኤል ሁሉ ሰም​ተው ይፍሩ፤ እን​ዲህ ያለ ክፉ ሥራም እን​ደ​ገና በእ​ና​ንተ መካ​ከል አይ​ደ​ገም።


“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልት​ኖ​ር​ባት ከሰ​ጠህ ከተ​ሞች በአ​ን​ዲቱ ከተ​ማህ፦


ኀጢአትንም ያደርጉ ዘንድ ላሉት ምሳሌ አድርጎ ከተማዎችን ሰዶምንና ገሞራን አመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎና ገልብጦ ከፈረደባቸው፥


跟着我们:

广告


广告