ሕዝቅኤል 23:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)40 ከሩቅ ሀገርም ወደመጡ ሰዎች መልእክተኞችን ላኩ፤ እነርሱም በደረሱ ጊዜ ይታጠባሉ፤ ዐይኖቻቸውንም ይኳላሉ፤ ያጌጣሉም። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም40 “ከዚህም በላይ ወንዶች ከሩቅ እንዲመጡላቸው መልእክተኛ ላኩ፤ እነርሱም መጡ። አንቺም ገላሽን ታጥበሽ፣ ዐይንሽን ተኵለሽና በጌጣጌጥ ተውበሽ ጠበቅሻቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)40 ደግሞም መልእክተኛ ወደ ተላከባቸው፥ ከሩቅም ወደሚመጡ ሰዎች ልከዋል፥ እነሆም መጡ፤ ታጠብሽላቸው ዓይንሽን ተኳልሽ፥ ጌጥም አደረግሽ፤ 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም40 “ወንዶችን ከሩቅ አገር ጋብዘው እንዲያመጡላቸው ደጋግመው መልእክተኞችን ላኩ፤ የፈለጓቸውም ወንዶች መጡላቸው፤ ሁለቱ እኅትማማቾች ገላቸውን ታጠቡ፤ ዐይናቸውን ተኳሉ፤ ጌጣጌጦቻቸውንም አደረጉ፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)40 ደግሞ መልእክተኛ ወደ ተላከባቸው ከሩቅም ወደሚመጡ ሰዎች ልካችኋል፥ እነሆም መጡ፥ አንቺም ታጠብሽላቸው ዓይኖችሽንም ተኳልሽ ጌጥም አጌጥሽ፥ 参见章节 |