Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 23:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 እነ​ር​ሱም በጥል ያደ​ር​ጉ​ብ​ሻል፤ የደ​ከ​ም​ሽ​በ​ት​ንም ሁሉ ይወ​ስ​ዳሉ፤ ዕራ​ቁ​ት​ሽ​ንና ዕር​ቃ​ን​ሽን አድ​ር​ገ​ውም ይተ​ዉ​ሻል፤ የግ​ል​ሙ​ት​ና​ሽ​ንም ነውር፥ ሴሰ​ኝ​ነ​ት​ሽ​ንና ግል​ሙ​ት​ና​ሽ​ንም ሁሉ ይገ​ል​ጣሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 እነርሱም በጥላቻ ይቀርቡሻል፤ የለፋሽበትንም ሁሉ ይቀሙሻል፤ ከማሕፀን እንደ ወጣሽ ዕርቃንሽን ያስቀሩሻል፤ የሴሰኝነትሽ ኀፍረት ይገለጣል። ብልግናሽና ገደብ የለሽ ርኩሰትሽ፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 እነርሱም በጥል ይቀርቡሻል፥ የድካምሽን ፍሬ ሁሉ ይወስዳሉ፥ ዕራቁትሽንና ዕርቃንሽን አድርገውም ይተዉሻል፥ የዝሙትሽ ዕራቁትነት፥ ሴሰኝነትሽና ግልሙትናሽ ይገለጣል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29-30 አንቺን ከመጥላታቸው የተነሣ የደከምሽበትን ሁሉ ይወስዱብሻል፤ እርቃንሽንም አስቀርተው እንደ አመንዝራ ሴት ኀፍረተ ሥጋሽ እንዲጋለጥ ያደርጋሉ፤ የተቃጠለ ፍትወትሽና ዘማዊነትሽ፥ ይህ ሁሉ እንዲደርስብሽ አድርጎአል፤ ለሕዝቦች ሁሉ የፍትወት መጠቀሚያ ዘማዊት ሆነሽ በጣዖቶቻቸው ራስሽን አረከስሽ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 እነርሱም በጥል ያደርጉብሻል፥ የደከምሽበትንም ሁሉ ይወስዳሉ፥ ዕራቁትሽንና ዕርቃንሽን አድርገውም ይተዉሻል፥ የግልሙትናሽም ነውር፥ ሴሰኝነትሽና ግልሙትናሽም ሁሉ ይገለጣል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 23:29
11 交叉引用  

ከዚ​ያም በኋላ አም​ኖን ፈጽሞ ጠላት፤ አስ​ቀ​ድሞ ከአ​ፈ​ቀ​ራት ፍቅር ይልቅ በኋላ የጠ​ላት ጥል በለጠ። አም​ኖ​ንም፥ “ተነ​ሥ​ተሽ ሂጂ” አላት።


ስለ​ዚ​ህም የል​ብ​ስ​ሽን ዘርፍ በስ​ተ​ኋ​ላሽ ወደ ፊትሽ እገ​ል​ጣ​ለሁ እፍ​ረ​ት​ሽም ይታ​ያል።


ሔት። ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እጅግ ኀጢ​አት ሠር​ታ​ለች፤ ስለ​ዚህ ረክ​ሳ​ለች፤ በተ​ጨ​ነ​ቀ​ች​በት ቦታ ያከ​ብ​ሩ​አት የነ​በሩ ሁሉ ውር​ደ​ቷን አይ​ተ​ዋ​ልና አቃ​ለ​ሉ​አት፤ እር​ስ​ዋም እየ​ጮ​ኸች ታለ​ቅ​ሳ​ለች፤ ወደ ኋላ​ዋም ዘወር አለች።


በእ​ጃ​ቸ​ውም አሳ​ልፌ እሰ​ጥ​ሻ​ለሁ፤ የም​ን​ዝ​ር​ና​ሽ​ንም ስፍራ ያፈ​ር​ሳሉ፤ ከፍ ያለ​ው​ንም ቦታ​ሽን ይገ​ለ​ብ​ጣሉ፤ ልብ​ስ​ሽ​ንም ይገ​ፉ​ሻል፤ የክ​ብ​ር​ሽ​ንም ጌጥ ይወ​ስ​ዳሉ፤ ዕራ​ቁ​ት​ሽ​ንም ይተ​ዉ​ሻል፤ ቷረ​ጃ​ለ​ሽም።


በው​ስ​ጥሽ ደምን ያፈ​ስሱ ዘንድ ሌቦች ሰዎች በአ​ንቺ ውስጥ ነበሩ፤ በአ​ንቺ ውስጥ በተ​ራ​ሮች ላይ በሉ፤ በመ​ካ​ከ​ል​ሽም የማ​ይ​ገባ ነገ​ርን አደ​ረጉ።


ዝሙ​ቷ​ንም ገለ​ጠች፤ ኀፍ​ረተ ሥጋ​ዋ​ንም ገለ​ጠች፤ ነፍ​ሴም ከእ​ኅቷ እንደ ተለ​የች እን​ዲሁ ነፍሴ ከእ​ር​ስዋ ተለ​የች።


በሻፊር የምትቀመጪ ሆይ፥ በዕራቁትነትሽና በእፍረት እለፊ፥ በጸዓናን የምትቀመጠው አልወጣችም፥ የቤትኤጼል ልቅሶ ከእናንተ ዘንድ መኖሪያውን ይወስዳል።


跟着我们:

广告


广告