ሕዝቅኤል 23:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 ቅንአቴንም በአንቺ ላይ አደርጋለሁ፤ በመዓትም ያደርጉብሻል፤ አፍንጫሽንና ጆሮሽንም ከአንቺ ይቈርጣሉ፤ ከአንቺም የቀረ በሰይፍ ይወድቃል፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችሽንም ማርከው ይወስዳሉ፤ ከአንቺም የቀሩትን እሳት ትበላቸዋለች። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም25 የቅናት ቍጣዬን በአንቺ ላይ አመጣለሁ፤ እነርሱም በአንቺ ላይ በቍጣ ይወጣሉ፤ አፍንጫሽንና ጆሮሽን ይቈርጣሉ፤ ከአንቺ ወገን የተረፉትም በሰይፍ ይወድቃሉ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችሽን ይወስዱብሻል፤ የተረፉትንም እሳት ይበላቸዋል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 በቁጣ እንዲቀርቡሽ ቅናቴን በአንቺ ላይ አደርጋለሁ፥ አፍንጫሽንና ጆሮሽን ይቆርጣሉ፤ ቀሪሽም በሰይፍ ይወድቃል፤ ወንዶችንና ሴቶች ልጆችሽን ይወስዳሉ፥ ከአንቺም የቀረው በእሳት ይበላል። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 እኔ በአንቺ ስለ ተቈጣሁ፤ እነርሱም በቊጣቸው በአንቺ ላይ የፈለጉትን እንዲያደርጉ እፈቅድላቸዋለሁ፤ አፍንጫሽንና ጆሮዎችሽን ይቈርጣሉ፤ ከአንችም የቀሩትን በሰይፍ ይገደላሉ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችሽን ከአንቺ ነጥቀው ይወስዳሉ፤ ከአንቺም የቀሩትን በእሳት ያቃጥሉአቸዋል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 ቅንዓቴንም በአንቺ ላይ አደርጋለሁ በመዓትም ያደርጉብሻል፥ አፍንጫሽንና ጆሮሽንም ከአንቺ ይቈርጣሉ፥ ከአንቺም የቀረ በሰይፍ ይወድቃል፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችሽንም ማርከው ይወስዳሉ፥ ከአንቺም የቀረውን እሳት ትበላቸዋለች። 参见章节 |