Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 23:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ስማ​ቸ​ውን ያስ​ጠሩ ሰዎች ሁሉ በመ​ን​ኰ​ራ​ኵ​ርና በሠ​ረ​ገላ፥ በአ​ሕ​ዛ​ብም ጉባኤ ይመ​ጡ​ብ​ሻል፤ ጋሻና አላ​ባሽ ጋሻ፥ ራስ ቍርም ይዘው በዙ​ሪ​ያሽ ጥበቃ ያደ​ር​ጋሉ፤ ፍር​ድ​ንም እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እንደ ፍር​ዳ​ቸ​ውም ይፈ​ር​ዱ​ብ​ሻል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 እነርሱም የጦር መሣሪያ፣ ሠረገላና ጋሪ በመያዝ ብዙ ሕዝብ ሆነው ይመጡብሻል፤ ትላልቅና መለስተኛ ጋሻ በማንገብና የራስ ቍር በመድፋት በየአቅጣጫው ይሰለፉብሻል፤ እኔም ለፍርድ በእጃቸው አሳልፌ እሰጥሻለሁ፤ በሕጋቸውም መሠረት ይቀጡሻል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 መሣሪያ፥ ሠረገላና መንኰራኵር ይዘው፥ ብዙ ሕዝብ ሆነው በአንቺ ላይ ይመጣሉ፤ ጋሻና አላባሽ ጋሻ ራስ ቁርም ይዘው በዙሪያሽ ይዘጋጁብሻል፥ ፍርድንም እሰጣቸዋለሁ፥ እንደ ፍርዳቸውም ይፈርዱብሻል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 እነርሱም በብዙ ሠረገላና ስንቅ በተጫኑ ጋሪዎች የተጠናከረ ታላቅ ሠራዊት መርተው በማምጣት በሁሉም አቅጣጫ አደጋ ይጥሉብሻል፤ በጋሻና በራስ ቊር እየተከላከሉ ይከቡሻል፤ እኔም ለእነርሱ ፍርድ አሳልፌ እሰጥሻለሁ፤ እነርሱም በራሳቸው ሕግ መሠረት ይቀጡሻል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 በመሣሪያና በሰረገላ በመንኰራኵርም በአሕዛብም ጉባኤ ይመጡብሻል፥ ጋሻና አላባሽ ጋሻ ራስ ቍርም ይዘው በዙሪያሽ ይዘጋጁብሻል፥ ፍርድንም እሰጣቸዋለሁ፥ እንደ ፍርዳቸውም ይፈርዱብሻል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 23:24
12 交叉引用  

ዳዊ​ትም ጋድን፥ “በሁ​ሉም እጅግ ተጨ​ን​ቄ​አ​ለሁ፤ በሰው እጅ ከም​ወ​ድቅ ይልቅ ምሕ​ረቱ ብዙ ነውና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ መው​ደቅ ይሻ​ለ​ኛል” አለው።


ከኀ​ይ​ለ​ኞች ፈረ​ሶች ከኮ​ቴ​ያ​ቸው መጠ​ብ​ጠብ ድምፅ፥ ከሰ​ረ​ገ​ሎ​ቹም መሽ​ከ​ር​ከር፥ ከመ​ን​ኰ​ራ​ኵ​ሮ​ቹም መት​መም የተ​ነሣ አባ​ቶች በእ​ጃ​ቸው ድካም ምክ​ን​ያት ወደ ልጆ​ቻ​ቸው አይ​መ​ለ​ሱም።


የሴ​ዴ​ቅ​ያ​ስ​ንም ዐይ​ኖች አወጣ፤ የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ በሰ​ን​ሰ​ለት አሰ​ረው፤ ወደ ባቢ​ሎ​ንም ወሰ​ደው፤ እስ​ኪ​ሞ​ትም ድረስ በግ​ዞት ቤት አኖ​ረው።


ንጉ​ሡ​ንም ይዘው የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ወዳ​ለ​ባት በኤ​ማት ምድር ወዳ​ለ​ችው ወደ ዴብ​ላታ አመ​ጡት፤ እር​ሱም ፍር​ድን በእ​ርሱ ላይ ተና​ገረ።


በአ​መ​ን​ዝ​ሮ​ችና በደም አፍ​ሳ​ሾች በቀል እበ​ቀ​ል​ሻ​ለሁ፤ በመ​ዓ​ትና በቅ​ን​አት ደምም አስ​ቀ​ም​ጥ​ሻ​ለሁ።


እርሱ በፊ​ታ​ቸው ምዋ​ር​ትን ያም​ዋ​ር​ታል፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ዐስቦ ሰባት ሱባዔ ይቈ​ጥ​ር​ባ​ቸ​ዋል።


ሴቶቹ አመ​ን​ዝ​ሮች ናቸ​ውና፥ በእ​ጃ​ቸ​ውም ደም አለና ጻድ​ቃን ሰዎች በአ​መ​ን​ዝ​ሮ​ቹና በደም አፍ​ሳ​ሾቹ ሴቶች ላይ በሚ​ፈ​ረ​ደው ፍርድ ይፈ​ር​ዱ​ባ​ቸ​ዋል።”


ከፈ​ረ​ሶ​ቹም ብዛት የተ​ነሣ በት​ቢያ ይሸ​ፍ​ን​ሻል፤ ከሠ​ረ​ገላ መን​ኰ​ራ​ኵ​ርና ከፈ​ረ​ሶቹ ድምፅ የተ​ነ​ሣም ቅጥ​ሮ​ች​ሽን ያፈ​ር​ሳል፤ ወን​በዴ መሣ​ሪ​ያ​ውን ይዞ ወደ ምድረ በዳ ቦታ እን​ዲ​ገባ በሮ​ች​ሽን ይገ​ቡ​ባ​ቸ​ዋል።


“ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ጢሮስ ሆይ! እነሆ ከሰ​ሜን የነ​ገ​ሥ​ታት ንጉሥ የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርን ከፈ​ረ​ሶ​ችና ከሰ​ረ​ገ​ሎች፥ ከፈ​ረ​ሰ​ኞ​ችም፥ ከጉ​ባ​ኤና ከብዙ ሕዝ​ብም ጋር በአ​ንቺ ላይ አመ​ጣ​ለሁ።


跟着我们:

广告


广告