Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 23:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 እነ​ር​ሱም የባ​ቢ​ሎን ልጆች፥ ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም ሁሉ፥ ፋቁድ፥ ሱሔ፥ ቆዓ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር አሦ​ራ​ው​ያን ሁሉ፥ መልከ መል​ካ​ሞች ጐበ​ዛ​ዝት፥ መሳ​ፍ​ን​ትና መኳ​ን​ንት ሁሉ፥ መሳ​ፍ​ን​ትና አማ​ካ​ሪ​ዎች ሁሉ፥ በሦ​ስት ወገን በፈ​ረስ ላይ የተ​ቀ​መጡ ናቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 እነርሱም ባቢሎናውያንና ከለዳውያን ሁሉ፣ የፋቁድ፣ የሱሔና የቆዓ ሰዎች፣ ከእነርሱም ጋራ አሦራውያን ሁሉ ናቸው። እነዚህም መልከ ቀና ጐበዛዝት ሲሆኑ፣ ሁላቸውም በፈረስ ላይ የተቀመጡ ገዦችና አዛዦች፣ የሠረገላ አዛዦችና ከፍተኛ ባለሥልጣኖች ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 እነርሱም የባቢሎን ልጆች፥ ከለዳውያን ሁሉ ፋቁድ፥ ሾዓ፥ ቆዓ፥ ከእነርሱም ጋር የአሦር ልጆች ሁሉ፥ ሁሉም መልከ መልካም ወጣቶች፥ ገዢዎች፥ ባለ ሥልጣናት፥ መኰንኖችና የተጠሩ፥ ሁሉም ፈረስ የሚጋልቡ ናቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ባቢሎናውያንንና ከለዳውያንን ሁሉ አመጣለሁ፤ የፈቆድን፥ የሾዐንና የቆዐንን ወንዶች እንዲሁም አሦራውያንን ሁሉ አመጣለሁ፤ ወጣትነት ያላቸው፥ መልከ ቀና የሆኑ መሳፍንትና የጦር መኰንኖች፥ ታላላቅ ባለሥልጣኖችና ከፍተኛ ማዕርግ ያላቸው እነዚህ ሁሉ በፈረስ ተቀምጠው ይመጣሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 እነርሱም የባቢሎን ሰዎች ከለዳውያንም ሁሉ ፋቁድ፥ ሱሔ፥ ቆዓ፥ ከእነርሱም ጋር አሦራውያን ሁሉ፥ መልከ መልካሞች ጐበዛዝት፥ አለቆችና ሹማምቶች ሁሉ፥ መሳፍንቶችና አማካሪዎች ሁሉ፥ በፈረስ ላይ የተቀመጡ ናቸው።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 23:23
16 交叉引用  

የሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ወንዝ ስም ጤግ​ሮስ ነው፤ እር​ሱም በአ​ሶር ላይ የሚ​ሄድ ነው። አራ​ተ​ኛ​ውም ወንዝ ኤፍ​ራ​ጥስ ነው።


ይስ​ማ​ኤ​ልም የኖ​ረ​በት የዕ​ድ​ሜው ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው ፤ ሸም​ግሎ ሞተ፤ ወደ ወገ​ኖ​ቹም ተጨ​መረ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንን አደጋ ጣዮች፥ የሶ​ር​ያ​ው​ያ​ን​ንም አደጋ ጣዮች፥ የሞ​ዓ​ባ​ው​ያ​ን​ንም አደጋ ጣዮች፥ የአ​ሞ​ን​ንም ልጆች አደጋ ጣዮች ሰደ​ደ​በት፤ በባ​ሪ​ያ​ዎቹ በነ​ቢ​ያት ቃል እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ያጠ​ፉት ዘንድ በይ​ሁዳ ላይ ሰደ​ዳ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደስ አሰ​ኝ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም አም​ላክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ለመ​ሥ​ራት እጃ​ቸ​ውን ያጸና ዘንድ የአ​ሦ​ርን ንጉሥ ልብ ወደ እነ​ርሱ መል​ሶ​አ​ልና የቂ​ጣ​ውን በዓል ሰባት ቀን በደ​ስታ አደ​ረጉ።


እር​ሱም ገና ይህን ሲና​ገር ሦስ​ተ​ኛው መል​እ​ክ​ተኛ መጥቶ ለኢ​ዮብ እን​ዲህ አለው፥ “ፈረ​ሰ​ኞች በሦ​ስት ረድፍ ከብ​በው ግመ​ሎ​ችን ማር​ከው ወሰዱ፥ ብላ​ቴ​ኖ​ች​ህ​ንም በሰ​ይፍ ስለት ገደሉ፤ እኔም ብቻ​ዬን አም​ልጬ እነ​ግ​ርህ ዘንድ መጣሁ።”


እነሆ፥ የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንን ሀገር አሦ​ራ​ው​ያን አጥ​ፍ​ተ​ዋ​ታ​ልና፤ ግን​ብ​ዋም ወድ​ቆ​አል፤


“በላ​ይ​ዋና በሚ​ኖ​ሩ​ባት ላይ በም​ሬት ውጡ፤ ሰይፍ ሆይ! ተበ​ቀዪ፥ ፍጻ​ሜ​ያ​ቸ​ው​ንም አጥፊ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ያዘ​ዝ​ሁ​ሽ​ንም ሁሉ አድ​ርጊ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦


የሚ​ቀ​ር​ቡ​አ​ትን መሳ​ፍ​ን​ቱ​ንና መኳ​ን​ን​ቱን ጌጠኛ ልብስ የለ​በ​ሱ​ትን፥ በፈ​ረ​ሶች ላይ የሚ​ቀ​መ​ጡ​ትን ፈረ​ሰ​ኞች፥ ሁሉ​ንም መልከ መል​ካ​ሞ​ችን ጐበ​ዛ​ዝት አሦ​ራ​ው​ያ​ንን በፍ​ቅር ተከ​ተ​ለ​ቻ​ቸው።


ዳግ​መ​ኛም ዝሙ​ቷን አበ​ዛች፤ በግ​ንብ ላይ የተ​ሣሉ የከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሰዎች ሥዕ​ል​ንም አየሁ።


ስለ​ዚህ ሐሊባ ሆይ! ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ነፍ​ስሽ ከእ​ነ​ርሱ የተ​ለ​የች ወዳ​ጆ​ች​ሽን አስ​ነ​ሣ​ብ​ሻ​ለሁ፤ በዙ​ሪ​ያ​ሽም በአ​ንቺ ላይ አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።


እነ​ር​ሱም ሰማ​ያዊ ሐር የለ​በሱ መሳ​ፍ​ን​ትና መኳ​ን​ንት፥ መልከ መል​ካ​ሞች ጐበ​ዛ​ዝት፥ በፈ​ረስ ላይ የሚ​ቀ​መጡ የተ​መ​ረጡ ፈረ​ሰ​ኞች ነበሩ።


ከዚ​ህም በኋላ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሀገር ወጥቶ በካ​ራን ተቀ​መጠ፤ ከዚ​ያም አባቱ ከሞተ በኋላ፥ ዛሬ እና​ንተ ወደ አላ​ች​ሁ​ባት ወደ​ዚች ሀገር አመ​ጣው።


跟着我们:

广告


广告