Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 23:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ስለ​ዚህ ሐሊባ ሆይ! ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ነፍ​ስሽ ከእ​ነ​ርሱ የተ​ለ​የች ወዳ​ጆ​ች​ሽን አስ​ነ​ሣ​ብ​ሻ​ለሁ፤ በዙ​ሪ​ያ​ሽም በአ​ንቺ ላይ አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 “ስለዚህ፣ ኦሖሊባ ሆይ፤ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ጠልተሻቸው ከእነርሱ ዘወር ያልሽውን ውሽሞችሽን በአንቺ ላይ አስነሣለሁ፤ እነርሱንም ከየአቅጣጫው አመጣብሻለሁ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ስለዚህ ኦሆሊባ ሆይ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ነፍስሽ ከእነርሱ የተለየቻቸው ወዳጆችሽን አስነሣብሻለሁ፥ እነርሱንም ከየአቅጣጫው በአንቺ ላይ አመጣቸዋለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 “አሁንም ኦሆሊባ ሆይ! እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምልሽ ይህ ነው፤ እነዚያን ወዳጆችሽን ተጸይፈሻቸዋል፤ ነገር ግን እነርሱ በአንቺ እንዲነሡ አደርጋለሁ፤ እንዲከቡሽም ወደዚህ አመጣቸዋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ስለዚህ፥ ኦሖሊባ ሆይ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ነፍስሽ ከእነርሱ የተለየች ውሽሞችሽን አስነሣብሻለሁ፥ በዙሪያሽም በአንቺ ላይ አመጣቸዋለሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 23:22
11 交叉引用  

ስለ​ዚህ እነሆ እኔ ከአ​ንቺ ጋር አንድ የሆኑ ውሽ​ሞ​ች​ሽን በአ​ንቺ ላይ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የም​ት​ወ​ጃ​ቸ​ው​ንም ከም​ት​ጠ​ያ​ቸው ጋር በአ​ንቺ ላይ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ይከ​ቡ​ሻል፤ በእ​ነ​ር​ሱም ዘንድ ጕስ​ቍ​ል​ና​ሽን እገ​ል​ጥ​ብ​ሻ​ለሁ፤ ሁሉም ኀፍ​ረ​ት​ሽን ያዩ​ብ​ሻል።


ጡትሽ በአ​ጐ​ጠ​ጐጠ ጊዜ በማ​ደ​ሪ​ያሽ በግ​ብፅ ሀገር የሠ​ራ​ሽ​ውን የወ​ጣ​ት​ነ​ት​ሽን ኀጢ​አት አሰ​ብሽ።”


እነ​ር​ሱም የባ​ቢ​ሎን ልጆች፥ ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም ሁሉ፥ ፋቁድ፥ ሱሔ፥ ቆዓ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር አሦ​ራ​ው​ያን ሁሉ፥ መልከ መል​ካ​ሞች ጐበ​ዛ​ዝት፥ መሳ​ፍ​ን​ትና መኳ​ን​ንት ሁሉ፥ መሳ​ፍ​ን​ትና አማ​ካ​ሪ​ዎች ሁሉ፥ በሦ​ስት ወገን በፈ​ረስ ላይ የተ​ቀ​መጡ ናቸው።


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በጠ​ላ​ሻ​ቸው እጅ፥ ነፍ​ስ​ሽም በተ​ለ​የ​ቻ​ቸው እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጥ​ሻ​ለሁ፤


ስለ​ዚህ በፍ​ቅር በተ​ከ​ተ​ለ​ቻ​ቸው በወ​ዳ​ጆ​ችዋ በአ​ሦ​ራ​ው​ያን እጆች አሳ​ልፌ ሰጠ​ኋት።


ያየሃቸውም ዐሥር ቀንዶችና አውሬው ጋለሞታይቱን ይጣላሉ፤ ባዶዋንና ራቁትዋንም ያደርጓታል፤ ሥጋዋንም ይበላሉ፤ በእሳትም ያቃጥሉአታል።


跟着我们:

广告


广告