ሕዝቅኤል 23:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 በጥቍር ቀለም የተሣሉ የከለዳውያንን መልክ አየሁ፤ በወገባቸው ዝናር የታጠቁ ናቸው፤ በራሳቸውም ላይ ጥልፍ ሰበን የጠመጠሙ ናቸው፤ ፊታቸውም ሦስት ወገን ነው፤ ሁሉም በትውልድ ሀገራቸው የሚኖሩ የባቢሎን ሰዎችን ከለዳውያንን ይመስላሉ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም15 እነርሱም ወገባቸውን በቀበቶ የታጠቁና በራሳቸው ላይ ተንጠልጣይ ያለው ጥምጥም የጠመጠሙ ነበሩ፤ ሁሉም የከለዳውያን ተወላጆችና የባቢሎን ሠረገላ አዛዦች ይመስሉ ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 በወገባቸው ዝናር የታጠቁ፥ በራሳቸውም ላይ መጠምጠሚያ ያንጠለጠሉ፥ ሁሉም የተወለዱባት አገር የከለዳ የሆነች የባቢሎን ልጆች የሆኑትን ባለሥልጣኖችን ይመስሉ ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 በወገባቸው ዝናር የታጠቁ ራሳቸውንም በቀለማዊ መጠምጠሚያ የጠመጠሙ ነበሩ፥ ሁሉም ከተወለዱባት አገር የሆኑትን የከለዳውያንን ልጆች መስለው መሳፍንትን ይመስሉ ነበር። 参见章节 |