Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 22:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በአ​ንቺ ውስጥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ኀፍ​ረተ ሥጋ ገለጡ፤ በአ​ን​ቺም ውስጥ አደፍ ያለ​ባ​ትን አዋ​ረዱ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 የአባታቸውን መኝታ የሚደፍሩ ሰዎች በውስጥሽ አሉ፤ በሥርዐቱ መሠረት ንጹሕ ባልሆኑበት በወር አበባቸው ጊዜ ሴቶችን በማስገደድ የሚደፍሩ በመካከልሽ ይገኛሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በአንቺ ውስጥ የአባቶቻቸውን ዕራቁትነት ገለጡ፥ በአንቺም ውስጥ አደፍ ያለባትን አዋረዱ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 አንዳንዶቹ ከእንጀራ እናታቸው ጋር በመተኛት የአባታቸውን አልጋ ይደፍራሉ፤ አንዳንዶቹ በወር አበባ ጊዜ ውስጥ ያሉትን ሴቶች በማስገደድ ግንኙነት ይፈጽማሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 በአንቺ ውስጥ የአባቶቻቸውን ኀፍረተ ሥጋ ገለጡ፥ በአንቺም ውስጥ አደፍ ያለባትን አዋረዱ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 22:10
14 交叉引用  

የያ​ዕ​ቆ​ብም ልጆች ዐሥራ ሁለት ናቸው፤


እንደ ውኃ የሚ​ዋ​ልል ነው፤ ኀይል የለ​ውም፤ ወደ አባቱ መኝታ ወጥ​ቶ​አ​ልና፤ ያን ጊዜ የወ​ጣ​በ​ትን አልጋ አር​ክ​ሶ​አ​ልና።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም በኵር የሮ​ቤል ልጆች እነ​ዚህ ናቸው። እርሱ የበ​ኵር ልጅ ነበረ፤ ነገር ግን ወደ አባቱ ምን​ጣፍ ስለ ወጣ አባቱ እስ​ራ​ኤል በረ​ከ​ቱን ለልጁ ለዮ​ሴፍ ሰጠ፤ ብኵ​ር​ናም አል​ተ​ቈ​ጠ​ረ​ለ​ትም።


በተ​ራ​ራም ላይ ባይ​በላ፥ ዐይ​ኖ​ቹ​ንም ወደ እስ​ራ​ኤል ቤት ጣዖ​ታት ባያ​ነሣ፥ የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ው​ንም ሚስት ባያ​ረ​ክስ፥ አደ​ፍም ወዳ​ለ​ባት ሴት ባይ​ቀ​ርብ፤


“እር​ስ​ዋም በግ​ዳ​ጅዋ ርኵ​ሰት ሳለች ኀፍ​ረተ ሥጋ​ዋን ትገ​ልጥ ዘንድ ሳት​ነጻ በግ​ዳ​ጅዋ ወደ አለች ሴት አት​ቅ​ረብ።


“ከእ​ና​ን​ተም ማንም ሰው ኀፍ​ረተ ሥጋ​ውን ይገ​ልጥ ዘንድ ወደ ሥጋ ዘመዱ ሁሉ አይ​ቅ​ረብ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ።


ማና​ቸ​ውም ሰው ከአ​ባቱ ሚስት ጋር ቢተኛ የአ​ባ​ቱን ኀፍ​ረተ ሥጋ ገል​ጦ​አል፤ ሁለ​ቱም ፈጽ​መው ይገ​ደሉ፤ በደ​ለ​ኞች ናቸው።


ማና​ቸ​ውም ሰው ከባለ ግዳጅ ሴት ጋር ቢተኛ ኀፍ​ረተ ሥጋ​ዋ​ንም ቢገ​ልጥ፥ ፈሳ​ሽ​ዋን ገል​ጦ​አ​ልና፥ እር​ስ​ዋም የደ​ም​ዋን ፈሳሽ ገል​ጣ​ለ​ችና ሁለቱ ከሕ​ዝ​ባ​ቸው መካ​ከል ተለ​ይ​ተው ይጥፉ።


የድ​ሆ​ችን ራስ ይቀ​ጠ​ቅ​ጣሉ፤ የት​ሑ​ታ​ን​ንም ፍርድ ያጣ​ም​ማሉ፤ የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም ስም ያረ​ክሱ ዘንድ አባ​ትና ልጁ ወደ አን​ዲት ሴት ይገ​ባሉ፤


በእ​ና​ንተ ላይ ዝሙት ይሰ​ማል፤ እን​ደ​ዚህ ያለው ዝሙ​ትም አረ​ማ​ው​ያን እንኳ የማ​ያ​ደ​ር​ጉት ነው፤ ያባ​ቱን ሚስት ያገባ አለና።


“ከእ​ን​ጀራ እናቱ ጋር የሚ​ተኛ የአ​ባ​ቱን ኀፍ​ረት ገል​ጦ​አ​ልና ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።


“ከአ​ማቱ ጋር የሚ​ተኛ ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ። ከዋ​ር​ሳው ጋር የሚ​ተኛ ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይሁን ይላሉ።


跟着我们:

广告


广告