Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 21:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ስለ​ዚህ አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ወገ​ብ​ህን በማ​ጕ​በጥ አል​ቅስ፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ምርር ብለህ አል​ቅስ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 “ስለዚህ የሰው ልጅ ሆይ፤ አቃስት! በተሰበረ ልብና በመረረ ሐዘን አቃስት፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 አንተም የሰው ልጅ ሆይ አልቅስ፥ ወገብህን በማጉበጥና በምሬት በፊታቸው አልቅስ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 “ስለዚህ በእነርሱ ፊት በተሰበረ ልብና በመረረ ሐዘን ቃትት! የሰው ልጅ ሆይ! ቃትት!”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ስለዚህም፥ አንተ የሰው ልጅ ሆይ፥ አልቅስ፥ ወገብህን በማጕበጥ በፊታቸው ምርር ብለህ አልቅስ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 21:6
21 交叉引用  

ስለ​ዚህ ልቤ ስለ ሞዓብ እንደ መሰ​ንቆ ትጮ​ኻ​ለች። አጥ​ን​ቶ​ችም እንደ ተመ​ረገ ግድ​ግዳ ይሆ​ናሉ።


ስለ​ዚ​ህም ወገቤ ሕማም ተሞላ፤ እን​ደ​ም​ት​ወ​ልድ ሴትም ምጥ ያዘኝ፤ ከሕ​ማሜ የተ​ነሣ አል​ሰ​ማም፤ ከድ​ን​ጋ​ጤም የተ​ነሣ አላ​ይም።


ስለ​ዚህ፥ “ተዉኝ እኔ መራራ ልቅሶ አለ​ቅ​ሳ​ለሁ፤ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ጥፋ​ትም ታጽ​ና​ኑኝ ዘንድ አት​ድ​ከሙ፥” አልሁ።


“ገም​ቦ​ው​ንም ከአ​ንተ ጋር በሚ​ሄዱ ሰዎች ፊት ትሰ​ብ​ራ​ለህ፤


ጠይቁ፤ ወንድ ይወ​ልድ እንደ ሆነ ተመ​ል​ከቱ፤ ስለ ምን ሰው ሁሉ እንደ ወላድ እጁን በወ​ገቡ ላይ አድ​ርጎ፥ ፊቱም ሁሉ ወደ ጥቍ​ረት ተለ​ውጦ አየሁ?


አን​ጀቴ! አን​ጀቴ! ልቤ በጣም ታም​ሞ​አል፤ ነፍ​ሴም አእ​ም​ሮ​ዋን አጥ​ታ​ለች፤ በው​ስ​ጤም ልቤ ታው​ኮ​ብ​ኛል፤ ነፍ​ሴም የመ​ለ​ከ​ትን ድም​ፅና የሰ​ል​ፍን ውካታ ሰም​ታ​ለ​ችና ዝም እል ዘንድ አል​ች​ልም።


የሰው ልጅ ሆይ! በሕ​ዝቤ ላይ ነውና፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አለ​ቆች ሁሉ ላይ ነውና ጩኽ፤ ዋይም በል፤ እነ​ርሱ ከሕ​ዝቤ ጋር ለሰ​ይፍ ተሰ​ጥ​ተ​ዋል፤ ስለ​ዚህ እጅ​ህን ጽፋ።


ሥጋ ለባ​ሹም ሁሉ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰይ​ፌን ከሰ​ገ​ባው እንደ መዘ​ዝሁ ያው​ቃል፤ እር​ሱም ደግሞ አይ​መ​ለ​ስም።


እነ​ር​ሱም፦ ስለ ምን ታለ​ቅ​ሳ​ለህ? ቢሉህ አንተ እን​ዲህ በላ​ቸው፦ ስለ​ሚ​መ​ጣው ወሬ ነው፤ ልብም ሁሉ ይቀ​ል​ጣል፤ እጆ​ችም ሁሉ ይዝ​ላሉ፤ ሥጋና መን​ፈስ ሁሉ ይደ​ክ​ማል፤ ከጕ​ል​በ​ትም እዥ ይፈ​ስ​ሳል፤ እነሆ ይመ​ጣል፤ ይፈ​ጸ​ማ​ልም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“የሰው ልጅ ሆይ! ስለ ግብፅ ኀይል ዋይ በል፤ እር​ስ​ዋ​ንና የብ​ር​ቱ​ዎ​ቹን አሕ​ዛብ ሴቶች ልጆች ወደ ጕድ​ጓድ ከሚ​ወ​ርዱ ጋር ወደ ታች​ኛው ምድር ጣላ​ቸው።


የም​ት​ጽ​ፍ​ባ​ቸ​ውም በት​ሮች በፊ​ታ​ቸው በእ​ጅህ ውስጥ ይሆ​ናሉ።


የገ​ብስ እን​ጎ​ቻ​ንም ትበ​ላ​ለህ፤ በሰው ኵስም ታበ​ስ​ለ​ዋ​ለህ፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ታዳ​ፍ​ነ​ዋ​ለህ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ጅህ አጨ​ብ​ጭብ፤ በእ​ግ​ር​ህም አሸ​ብ​ሽብ፤ ስለ እስ​ራ​ኤል ቤት ርኵ​ሰት ሁሉ ወዮ ወዮ በል፤ በረ​ኀ​ብና በጦር፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም ይጠ​ፋሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “በከ​ተ​ማ​ዪቱ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መካ​ከል እለፍ፥ በመ​ካ​ከ​ል​ዋም ስለ ተሠ​ራው ኀጢ​አት ሁሉ በሚ​ያ​ለ​ቅ​ሱና በሚ​ተ​ክዙ ሰዎች ግን​ባር ላይ ምል​ክት ጻፍ አለው።


ባዶና ባድማ ምድረ በዳም ሆናለች፣ ልብ ቀልጦአል፥ ጕልበቶችም ተብረክርከዋል፣ በወገብም ሁሉ ሕማም አለ፥ የሰዎችም ሁሉ ፊት ጠቍሮአል።


እኔ ሰምቻለሁ፥ ልቤም ደነገጠብኝ፣ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፣ መንቀጥቀጥ ወደ አጥንቶቼ ውስጥ ገባ፣ በስፍራዬ ሆኜ ተናወጥሁ፣ በሚያስጨንቁን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ።


跟着我们:

广告


广告