Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 21:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ሥጋ ለባ​ሹም ሁሉ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰይ​ፌን ከሰ​ገ​ባው እንደ መዘ​ዝሁ ያው​ቃል፤ እር​ሱም ደግሞ አይ​መ​ለ​ስም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ሰይፌን ከሰገባው የመዘዝሁት እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ሕዝቡ ሁሉ ያውቃል፤ እርሱም ወደ ሰገባው አይመለስም።’

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እኔ ጌታ ሰይፌን ከሰገባው እንደ መዘዝሁ ሥጋ ለባሽ ሁሉ ያውቃል፤ እርሱም ደግሞ ወደ ሰገባው አይመለስም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እኔ እግዚአብሔር ሰይፌን እንደ መዘዝኩና መልሼም ወደ አፎቱ እንደማልከተው ሰው ሁሉ ያውቃል።’

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ሥጋ ለባሹም ሁሉ እኔ እግዚአብሔር ሰይፌን ከሰገባው እንደ መዘዝሁ ያውቃል፥ እርሱም ደግሞ አይመለስም።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 21:5
14 交叉引用  

ቃሌ ከአፌ በጽ​ድቅ ወጥ​ታ​ለች፤ አት​መ​ለ​ስ​ምም፤ ጕል​በት ሁሉ ለእኔ ይን​በ​ረ​ከ​ካል፤ ምላ​ስም ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይም​ላል ብዬ በራሴ ምያ​ለሁ።”


ከአፌ የሚ​ወጣ ቃሌ እን​ዲሁ ነው፤ የም​ሻ​ውን እስ​ኪ​ያ​ደ​ርግ ድረስ ወደ እኔ በከ​ንቱ አይ​መ​ለ​ስም፤ መን​ገ​ዴ​ንና ትእ​ዛ​ዜን አከ​ና​ው​ና​ለሁ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ የል​ቡን ዐሳብ ሠርቶ እስ​ኪ​ፈ​ጽም ድረስ አይ​መ​ለ​ስም፤ በኋ​ለ​ኛ​ውም ዘመን ያው​ቁ​ታል።


አን​ተም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ከም​ሰ​ድ​ደው ሰይፍ የተ​ነሣ ጠጡ፤ ስከ​ሩም፤ ተፍ​ገ​ም​ገሙ፤ ውደ​ቁም፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ አት​ነ​ሡም በላ​ቸው።


“የሰው ልጅ ሆይ! ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ምሳሌ መስ​ለህ ንገር፤ እን​ዲ​ህም በል፦


እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ነ​ደ​ድ​ሁት ሥጋ ለባሽ ሁሉ ያያል፥ እር​ሱም አይ​ጠ​ፋም።


ወደ ሰገ​ባ​ውም መል​ሰው፤ በተ​ፈ​ጠ​ር​ህ​ባት ስፍራ አት​ደር፤ በተ​ወ​ለ​ድ​ህ​ባ​ትም ምድር እፈ​ር​ድ​ብ​ሃ​ለሁ።


ስለ​ዚህ አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ወገ​ብ​ህን በማ​ጕ​በጥ አል​ቅስ፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ምርር ብለህ አል​ቅስ።


በእግዚአብሔር ላይ የምታስቡት ምንድር ነው? እርሱ ፈጽሞ ያጠፋል፥ መከራም ሁለተኛ አይነሣም።


እጄን ወደ ሰማይ እዘ​ረ​ጋ​ለ​ሁና፥ በቀኜ እም​ላ​ለሁ፦ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም እኔ ሕያው ነኝ እላ​ለሁ።


በዚ​ያም ቀን በቤቱ ላይ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን ሁሉ በዔሊ ላይ አጸ​ና​ለሁ፤ እኔም ጀምሬ እፈ​ጽ​ም​በ​ታ​ለሁ።


跟着我们:

广告


广告