Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 21:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ሰይፍ ወደ አሞን ልጆች ሀገር፥ ወደ ራባት፥ ወደ ይሁ​ዳም፥ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም፥ በመ​ካ​ከ​ልዋ ይገባ ዘንድ መን​ገ​ድን አድ​ርግ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 በአሞናውያን ከተማ በረባት ላይ ለሚመጣው ሰይፍ አንደኛውን መንገድ ምልክት አድርግ፤ በይሁዳና በተመሸገችው ከተማ በኢየሩሳሌም ላይ ለሚመጣውም ሰይፍ ሁለተኛውን መንገድ ምልክት አድርግ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ሰይፍ ወደ አሞን ልጆች ወደ ረባት፥ ወደ ይሁዳ፥ ወደ ተመሸገች ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመጣ መንገድን አድርግ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ለጦሩ ወደ አሞናውያን ከተማ ራባ በሚወስደው መንገድ ላይና እንዲሁም ወደ ተመሸገችው የይሁዳ ከተማ ወደ ኢየሩሳሌም በሚወስደው መንገድ ላይ የአቅጣጫ ምልክት አድርግ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ሰይፍ ወደ አሞን ልጆች አገር ወደ ረባት ወደ ይሁዳም ወደ ተመሸገች ወደ ኢየሩሳሌም ይመጣ ዘንድ መንገድን አድርግ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 21:20
13 交叉引用  

ኢዮ​አ​ብም የአ​ሞ​ንን ልጆች ከተማ ራባ​ትን ወጋ፤ የመ​ን​ግ​ሥ​ታ​ቸ​ው​ንም ከተማ ያዘ።


ዳዊ​ትም በአ​ን​ባ​ዪቱ ውስጥ ተቀ​መጠ፤ እር​ስ​ዋም የዳ​ዊት ከተማ ተባ​ለች። ከተ​ማ​ዋ​ንም ዙሪ​ያ​ዋን እስከ ዳር​ቻዋ ድረስ ቀጠ​ራት፤ ቤቱ​ንም ሠራ።


ዖዝ​ያ​ንም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በማ​ዕ​ዘኑ በርና በሸ​ለ​ቆው በር፥ ቅጥ​ሩም በዞ​ረ​በት ማዕ​ዘን አጠ​ገብ ግን​ቦ​ችን ሠርቶ መሸ​ጋ​ቸው።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ሰው​ነ​ቱን አጽ​ናና፤ የፈ​ረ​ሰ​ው​ንም ቅጥር ሁሉ ጠገነ፤ በላ​ዩም ግንብ ሠራ​በት፤ ከእ​ር​ሱም በስ​ተ​ውጭ ሌላ ቅጥር ሠራ፤ ወደ ዳዊ​ትም ከተማ የሚ​ያ​ወ​ጣ​ውን በር አጠ​ነ​ከረ፤ ብዙም መሣ​ሪ​ያና ጋሻ አዘ​ጋጀ።


“ዓለ​ምን ሁሉ የም​ት​ገዛ፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን የአ​ብ​ር​ሃ​ምና የይ​ስ​ሐቅ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም የጻ​ድ​ቃን ልጆ​ቻ​ቸ​ውም አም​ላክ ሆይ፥ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ከዓ​ለ​ሞ​ቻ​ቸው ጋር የፈ​ጠ​ርህ፥


የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ቤቶች ቈጠ​ራ​ችሁ፤ ቅጥ​ሩ​ንም ለማ​ጽ​ናት ቤቶ​ችን አፈ​ረ​ሳ​ችሁ።


ስለ​ዚህ እነሆ በአ​ሞን ልጆች ከተማ በራ​ባት ላይ የሰ​ልፍ ውካ​ታን የማ​ሰ​ማ​በት ዘመን ይመ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ለጥ​ፋ​ትም ትሆ​ና​ለች፥ መን​ደ​ሮ​ች​ዋም በእ​ሳት ይቃ​ጠ​ላሉ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም የወ​ረ​ሱ​ትን ይወ​ር​ሳል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ላሜድ። የም​ድር ነገ​ሥ​ታት፥ በዓ​ለ​ምም የሚ​ኖሩ ሁሉ፥ አስ​ጨ​ና​ቂና ጠላት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በር እን​ደ​ሚ​ገባ አላ​መ​ኑም።


የአ​ሞ​ንን ከተማ ለግ​መ​ሎች ማሰ​ማ​ሪያ፥ የአ​ሞ​ን​ንም ልጆች ለመ​ንጋ መመ​ሰ​ጊያ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


በራባ ቅጥር ላይ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ በጦ​ር​ነት ቀን በጩ​ኸት መሠ​ረ​ቶ​ች​ዋን ትበ​ላ​ለች፤ በፍ​ጻ​ሜ​ዋም ቀን ትና​ወ​ጣ​ለች።


ከራ​ፋ​ይ​ንም ወገን የባ​ሳን ንጉሥ ዐግ ብቻ​ውን ቀርቶ ነበር፤ እነሆ፥ አል​ጋው የብ​ረት አልጋ ነበረ፤ እርሱ በአ​ሞን ልጆች ሀገር ዳርቻ አለ፤ ርዝ​መቱ ዘጠኝ ክንድ ወር​ዱም አራት ክንድ በሰው ክንድ ልክ ነበረ።


跟着我们:

广告


广告