Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 20:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እነ​ርሱ ግን ዐመ​ፁ​ብኝ፤ ይሰ​ሙ​ኝም ዘንድ አል​ወ​ደ​ዱም፤ ሁሉም እያ​ን​ዳ​ንዱ ርኵ​ሰ​ቱን ከፊቱ አላ​ስ​ወ​ገ​ደም፤ የግ​ብ​ጽ​ንም ጣዖ​ታት አል​ተ​ወም፤ በዚ​ህም ጊዜ በግ​ብፅ ምድር መካ​ከል ቍጣ​ዬን እፈ​ጽ​ም​ባ​ቸው ዘንድ መዓ​ቴን አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ አልሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “ ‘እነርሱ ግን በእኔ ላይ ዐመፁ፤ ሊሰሙኝም አልፈለጉም፤ ዐይኖቻቸውን ያሳረፉባቸውን ርኩስ ምስሎች አላስወገዱም፤ የግብጽንም ጣዖታት አልተዉም። እኔም በዚያው በግብጽ ምድር መዓቴን በላያቸው ላፈስስ፣ ቍጣዬንም ላወርድባቸው ወስኜ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እነርሱ ግን ዐመፁብኝ ይሰሙኝም ዘንድ አልወደዱም፥ ሁሉም እያንዳንዱ የዓይኑን ርኩሰት አልጣለም የግብጽንም ጣዖታት አልተወም፤ በዚህም ጊዜ፦ በግብጽ ምድር መካከል ቁጣዬን እፈጽምባቸው ዘንድ መዓቴን አፈስስባቸዋለሁ አልሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ነገር ግን እነርሱ ዐመፀኞች ሆኑ እንጂ እኔን ለማዳመጥ ፈቃደኞች አልሆኑም፤ ዐይኖቻቸው ያተኰሩባቸውን አጸያፊ ምስሎች አላስወገዱም፤ የግብጽንም ጣዖት ማምለክ አልተዉም፤ ስለዚህ በግብጽ በነበሩበት ጊዜ ቊጣዬን ላወርድባቸው አስቤ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እነርሱ ግን ዐመፁብኝ ይሰሙኝም ዘንድ አልወደዱም፥ ሁሉም እያንዳንዱ የዓይኑን ርኵሰት አልጣለም የግብጽንም ጣዖታት አልተወም፥ በዚህም ጊዜ፦ በግብጽ ምድር መካከል ቍጣዬን እፈጽምባቸው ዘንድ መዓቴን አፈስስባቸዋለሁ አልሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 20:8
24 交叉引用  

“ነገር ግን ተመ​ል​ሰው ዐመ​ፁ​ብህ፤ ሕግ​ህ​ንም ወደ ኋላ​ቸው ጣሉት፤ ወደ አን​ተም ይመ​ለሱ ዘንድ የመ​ሰ​ከ​ሩ​ባ​ቸ​ውን ነቢ​ያ​ት​ህን ገደሉ፤ እጅ​ግም አስ​ቈ​ጡህ።


በመ​ር​ከ​ቦች ወደ ባሕር የሚ​ወ​ርዱ፥ በብዙ ውኃ ሥራ​ቸ​ውን የሚ​ሠሩ፥


የቀ​ደ​መ​ውን በደ​ላ​ች​ንን አታ​ስ​ብ​ብን፥ አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ትህ በቶሎ ያግ​ኘን፥ እጅግ ተቸ​ግ​ረ​ና​ልና።


ሕዝ​ቡም ሙሴ ከተ​ራ​ራው ሳይ​ወ​ርድ እንደ ዘገየ ባዩ ጊዜ፥ ወደ አሮን ተሰ​ብ​ስ​በው፥ “ይህ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣን ሰው ሙሴ ምን እንደ ሆነ አና​ው​ቅ​ምና ተነ​ሥ​ተህ በፊ​ታ​ችን የሚ​ሄዱ አማ​ል​ክት ሥራ​ልን” አሉት።


እነ​ርሱ ግን ዐመ​ፁ​በት፤ ቅዱስ መን​ፈ​ሱ​ንም አስ​መ​ረሩ፤ ስለ​ዚህ ተመ​ልሶ ጠላት ሆና​ቸው፤ እር​ሱም ተዋ​ጋ​ቸው።


እነ​ርሱ ሁሉ ግን በክፉ ልባ​ቸው እል​ከ​ኝ​ነት ሄዱ እንጂ አል​ሰ​ሙም፤ ጆሮ​አ​ቸ​ው​ንም አላ​ዘ​ነ​በ​ሉም፤ ስለ​ዚህ ያዘ​ዝ​ኋ​ቸ​ውን እነ​ር​ሱም ያላ​ደ​ረ​ጉ​ትን የዚ​ህን ቃል ኪዳን ቃል ሁሉ አመ​ጣ​ሁ​ባ​ቸው።”


እነ​ር​ሱም ገብ​ተው ወረ​ሱ​አት፤ ነገር ግን ቃል​ህን አል​ሰ​ሙም፤ በሕ​ግ​ህም አል​ሄ​ዱም፤ ያደ​ር​ጉም ዘንድ ካዘ​ዝ​ሃ​ቸው ሁሉ ምንም አላ​ደ​ረ​ጉም፤ ስለ​ዚህ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመ​ጣ​ህ​ባ​ቸው።


ነገር ግን በክፉ ልባ​ቸው አሳ​ብና እል​ከ​ኝ​ነት ሄዱ፤ ወደ​ፊ​ትም ሳይ​ሆን ወደ ኋላ​ቸው ሄዱ እንጂ አል​ሰ​ሙ​ኝም ጆሮ​አ​ቸ​ው​ንም አላ​ዘ​ነ​በ​ሉም።


ነገር ግን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት በም​ድረ በዳ በት​እ​ዛዜ ሂዱ አል​ኋ​ቸው፤ አል​ሄ​ዱ​ምም፤ ሰው ቢያ​ደ​ር​ገው ኖሮ በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ር​በ​ት​ንም ሕጌን አፈ​ረሱ፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም ፈጽ​መው አረ​ከሱ። በዚ​ህም ጊዜ አጠ​ፋ​ቸው ዘንድ ቍጣ​ዬን በም​ድረ በዳ አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ አልሁ።


ፍር​ዴ​ንም ጥሰ​ዋ​ልና፥ በሥ​ር​ዐ​ቴም አል​ሄ​ዱ​ምና፥ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም አር​ክ​ሰ​ዋ​ልና በል​ባ​ቸው ዐሳብ ሄዱ።


ልጆ​ቻ​ቸው ግን አማ​ረ​ሩኝ፤ ሰው ቢያ​ደ​ር​ገው ኖሮ በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ር​በ​ትን ፍር​ዴን ጠብ​ቀው አላ​ደ​ረ​ጉ​ትም፤ በሥ​ር​ዐ​ቴም አል​ሄ​ዱም፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም አረ​ከሱ፤ በዚ​ህም ጊዜ፦ መዓ​ቴን አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ቍጣ​ዬ​ንም በም​ድረ በዳ እፈ​ጽ​ም​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ አልሁ።


እኔም፦ ከእ​ና​ንተ እያ​ን​ዳ​ንዱ ርኵ​ሰ​ቱን ከፊቱ ያስ​ወ​ግድ፤ በግ​ብ​ፅም ጣዖ​ታት አት​ር​ከሱ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ አል​ኋ​ቸው።


ብርም በከ​ውር ውስጥ እን​ደ​ሚ​ቀ​ልጥ፥ እን​ዲሁ በው​ስ​ጥዋ ትቀ​ል​ጣ​ላ​ችሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዓ​ቴን እን​ዳ​ፈ​ሰ​ስ​ሁ​ባ​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።”


በግ​ብፅ ሀገር አመ​ነ​ዘሩ፤ በኮ​ረ​ዳ​ነ​ታ​ቸው ሳሉ አመ​ነ​ዘሩ፤ በዚ​ያም ጡቶ​ቻ​ቸው ወደቁ፤ በዚ​ያም ድን​ግ​ል​ና​ቸ​ውን አጡ።


“ቍጣ​ዬ​ንና መዓ​ቴ​ንም በእ​ነ​ርሱ ላይ እጨ​ር​ሳ​ለሁ፤ መዓ​ቴ​ንም በፈ​ጸ​ም​ሁ​ባ​ቸው ጊዜ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቅ​ን​ዓቴ እንደ ተና​ገ​ርሁ ታው​ቂ​ያ​ለሽ።


አሁን በቅ​ርብ መዓ​ቴን አፈ​ስ​ስ​ብ​ሻ​ለሁ፤ ቍጣ​ዬ​ንም እፈ​ጽ​ም​ብ​ሻ​ለሁ፤ እን​ደ​መ​ን​ገ​ድ​ሽም መጠን እፈ​ር​ድ​ብ​ሻ​ለሁ፤ ጕስ​ቍ​ል​ና​ሽ​ንም ሁሉ አመ​ጣ​ብ​ሻ​ለሁ።


እስ​ራ​ኤ​ልን በም​ድረ በዳ እንደ አለ ወይን ሆኖ አገ​ኘ​ሁት፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያዋ ዓመት እንደ በለስ በኵ​ራት ሆነው አየ​ኋ​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን ወደ ብዔ​ል​ፌ​ጎር መጡ፤ ለነ​ው​ርም ተለዩ፤ እንደ ወደ​ዱ​ትም ርኩስ ሆኑ።


እንደ ተቀ​መ​ጣ​ች​ሁ​ባት እንደ ግብፅ ምድር ሥራ አት​ሥሩ፤ እኔም ወደ እር​ስዋ እን​ደ​ማ​ገ​ባ​ችሁ እንደ ከነ​ዓን ምድር ሥራ አት​ሥሩ፤ በሥ​ር​ዐ​ታ​ቸ​ውም አት​ሂዱ።


ለእ​ና​ንተ ከታ​ወ​ቀ​በት ቀን ጀምሮ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐመ​ፀ​ኞች ነበ​ራ​ችሁ።


“አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በም​ድረ በዳ ምን ያህል እን​ዳ​ሳ​ዘ​ን​ኸው፥ ከግ​ብፅ ሀገር ከወ​ጣ​ህ​በት ቀን ጀምሮ ወደ​ዚህ ስፍራ እስከ መጣ​ችሁ ድረስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ እን​ዳ​መ​ፃ​ችሁ አስብ፤ አት​ር​ሳም።


跟着我们:

广告


广告