ሕዝቅኤል 20:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤልን ቤት በመረጥሁበት፥ ለያዕቆብም ቤት ዘር በታወቅሁበት ቀን፥ በግብፅም ምድር በተገለጥሁላቸው ጊዜ እጄን አንሥቼ፦ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ አልኋቸው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም5 እንዲህም በላቸው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ እስራኤልን በመረጥሁበት ቀን፣ ለያዕቆብ ቤት ዘር እጄን አንሥቼ ማልሁላቸው፤ በግብጽም ራሴን ገለጥሁላቸው። እጄንም አንሥቼ፣ “እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ አልኋቸው።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እስራኤልን በመረጥሁበት ቀን፥ ለያዕቆብ ቤት ዘር ማልሁላቸው፥ በግብጽም ምድር ራሴን ገለጥሁላቸው፦ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ ብዬ ማልሁላቸው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 እንዲህም በላቸው፦ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘እስራኤልን በመረጥኩ ጊዜ ለያዕቆብ ዘር በግብጽ ምድር ራሴን በማሳወቅ ቃል ገባሁላቸው፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ’ አልኳቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እስራኤልን በመረጥሁበት ለያዕቆብም ቤት ዘር በማልሁበት ቀን በግብጽም ምድር በተገለጥሁላቸውና፦ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ ብዬ በማልሁላችሁ ጊዜ፥ 参见章节 |