Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 20:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 ከእ​ና​ን​ተም ዘንድ ዐመ​ፀ​ኞ​ች​ንና የበ​ደ​ሉ​ኝን እለ​ያ​ለሁ፤ ከኖ​ሩ​ባ​ትም ምድር አወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ እስ​ራ​ኤል ምድር ግን አይ​ገ​ቡም፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 በእኔ ላይ ያመፁትንና የበደሉኝን ከመካከላችሁ አስወግዳለሁ፤ ከሚኖሩበት አገር አወጣቸዋለሁ፤ ወደ እስራኤል ምድር ግን አይገቡም፤ በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 ከእናንተም ዘንድ ዓመፀኞችንና የበደሉኝን እለያለሁ። ከኖሩባትም ምድር አወጣቸዋለሁ፥ ወደ እስራኤል ምድር ግን አይገቡም፥ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 ዐመፀኞችንና የበደሉኝን ከመካከላችሁ አስወግዳለሁ፤ አሁን ከሚኖሩባቸው አገሮች አወጣቸዋለሁ፤ ነገር ግን ወደ እስራኤል ምድር እንዲመለሱ ከቶ አልፈቅድላቸውም፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 ከእናንተም ዘንድ ዓመፀኞችንና የበደሉኝን እለያለሁ። ከኖሩባትም ምድር አወጣቸዋለሁ፥ ወደ እስራኤል ምድር ግን አይገቡም፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 20:38
26 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍር​ድን ማድ​ረግ ያው​ቃል፤ ኀጢ​አ​ተ​ኛው በእ​ጆቹ ሥራ ተጠ​መደ።


ሰማ​ያት ደስ ይላ​ቸ​ዋል፥ ምድ​ርም ሐሤ​ትን ታደ​ር​ጋ​ለች፤ ባሕር ሞላዋ ትና​ወ​ጣ​ለች፤


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ አሔ​ል​ማ​ዊ​ውን ሸማ​ያ​ንና ዘሩን እቀ​ጣ​ለሁ፤ እኔም ለሕ​ዝቤ የማ​ደ​ር​ገ​ውን መል​ካ​ሙን ነገር የሚ​ያይ ሰው በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ አይ​ኖ​ር​ላ​ቸ​ውም፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ዐመ​ፃን ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።”


በዚያ ለመ​ቀ​መጥ በል​ባ​ቸው ተስፋ ወደ​ሚ​ያ​ደ​ር​ጓት ወደ ይሁዳ ምድር ይመ​ለሱ ዘንድ በግ​ብፅ ለመ​ኖር ከመጡ ከይ​ሁዳ ቅሬታ ወገን የሚ​ያ​መ​ል​ጥና የሚ​ቀር፥ ወደ​ዚ​ያም የሚ​መ​ለስ አይ​ኖ​ርም፤ ከሚ​ያ​መ​ል​ጥም በቀር ማንም አይ​መ​ለ​ስም።”


ጣዖት በሚ​ያ​መ​ል​ኩ​በት ልባ​ቸ​ውና በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው እንደ ልባ​ቸው ቢሄዱ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን በራ​ሳ​ቸው ላይ እመ​ል​ሳ​ለሁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እጄም ሐሰ​ተኛ ራእ​ይን በሚ​ያዩ፥ ሕዝ​ቤ​ንም ለማ​ታ​ለል በከ​ንቱ በሚ​ያ​ም​ዋ​ርቱ ነቢ​ያት ላይ ትሆ​ና​ለች። እነ​ር​ሱም በሕ​ዝቤ ማኅ​በር ውስጥ አይ​ኖ​ሩም፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት መጽ​ሐፍ አይ​ጻ​ፉም፥ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ምድር አይ​ገ​ቡም፤ እኔም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።


ፊቴ​ንም በእ​ነ​ርሱ ላይ አጸ​ና​ለሁ፤ ከእ​ሳ​ትም አይ​ወ​ጡም፤ እሳ​ትም ይበ​ላ​ቸ​ዋል፤ ፊቴ​ንም በእ​ነ​ርሱ ላይ በአ​ጸ​ናሁ ጊዜ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


ወተ​ትና ማርም ወደ​ም​ታ​ፈ​ስ​ሰው ከም​ድር ሁሉ ወደ​ም​ታ​ምር ወደ ሰጠ​ኋ​ቸው ምድር እን​ዳ​ላ​ገ​ባ​ቸው በም​ድረ በዳ በእ​ነ​ርሱ ላይ ፈጽሜ እጄን አነ​ሣሁ።


ፍር​ዴ​ንም ጥሰ​ዋ​ልና፥ በሥ​ር​ዐ​ቴም አል​ሄ​ዱ​ምና፥ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም አር​ክ​ሰ​ዋ​ልና በል​ባ​ቸው ዐሳብ ሄዱ።


ከአ​ሕ​ዛ​ብም ዘንድ አወ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከተ​በ​ተ​ና​ች​ሁ​ባ​ትም ሀገር ሁሉ በበ​ረ​ታች እጅና በተ​ዘ​ረ​ጋች ክንድ፥ በፈ​ሰ​ሰ​ችም መዓት እሰ​በ​ስ​ባ​ች​ኋ​ለሁ።


እን​ግ​ዲህ በደ​ላ​ችሁ በላ​ያ​ችሁ ላይ ይመ​ለ​ሳል፤ እና​ን​ተም የጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ኀጢ​አት ትሸ​ከ​ማ​ላ​ችሁ፤ እኔም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።”


ሙታ​ኖ​ቻ​ች​ሁም በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ይወ​ድ​ቃሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


እርሱም ብርን እንደሚያነጥርና እንደሚያጠራ ሰው ይቀመጣል፥ የሌዊንም ልጆች ያጠራል፥ እንደ ወርቅና እንደ ብርም ያነጥራቸዋል፣ እነርሱም ለእግዚአብሔር በጽድቅ ቍርባንን የሚያቀርቡ ይሆናሉ።


መንሹም በእጁ ነው፤ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፤ ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ከእ​ነ​ርሱ በሁ​ሉም ደስ አላ​ለ​ውም፤ ብዙ​ዎቹ በም​ድረ በዳ ወድ​ቀ​ዋ​ልና።


ሥራዉ ዓለም ከተ​ፈ​ጠረ ጀምሮ ምንም እንኳ ቢፈ​ጸም፥ “እን​ግ​ዲህ ወደ ዕረ​ፍቴ አይ​ገ​ቡም ብዬ በቍ​ጣዬ ማልሁ” እን​ዳለ እኛስ ያመ​ንን ወደ ዕረ​ፍቱ እን​ገ​ባ​ለን።


እን​ግ​ዲህ አን​ዳ​ን​ዶች በዚያ እን​ዲ​ገቡ መን​ገድ ስለ ነበ​ራ​ቸው ቀድ​ሞም የም​ሥ​ራች የተ​ሰ​በ​ከ​ላ​ቸው ባለ መታ​ዘዝ ጠንቅ ስላ​ል​ገቡ፦


ዳሩ ግን ሁሉን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ምንም የተማራችሁ ብትሆኑ ጌታ ከግብጽ አገር ሕዝቡን አድኖ የማያምኑትን በኋላ እንዳጠፋቸው ላሳስባችሁ እወዳለሁ።


跟着我们:

广告


广告