Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 20:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 “እኔ ሕያው ነኝ! በበ​ረ​ታች እጅና በተ​ዘ​ረ​ጋች ክንድ፥ በፈ​ሰ​ሰ​ችም መዓት እነ​ግ​ሥ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 በሕያውነቴ እምላለሁ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ በብርቱ ክንድና በተዘረጋች እጅ መዓትንም በማፍሰስ በላያችሁ እነግሣለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 እኔ ሕያው ነኝና በበረታች እጅና በተዘረጋች ክንድ በፈሰሰችም መዓት እነግሥባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔ ሕያው እንደ መሆኔ በእርግጥ በሥልጣኔ፥ በሙሉ ኀይሌና በቊጣዬ በእናንተ ላይ እነግሣለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 እኔ ሕያው ነኝና በበረታች እጅና በተዘረጋች ክንድ በፈሰሰችም መዓት እነግሥባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 20:33
13 交叉引用  

ታላ​ቁን ስም​ህን፥ ብር​ቱ​ይ​ቱ​ንም እጅ​ህን፥ የተ​ዘ​ረ​ጋ​ች​ው​ንም ክን​ድ​ህን ሰም​ተው ቢመ​ጡና በዚህ ቤት ቢጸ​ልዩ፥


ስለ​ዚ​ህም ፈጥ​ነህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ በላ​ቸው፥ “እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ ከግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም ተገ​ዥ​ነት አወ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከባ​ር​ነ​ታ​ቸ​ውም አድ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ በተ​ዘ​ረጋ ክንድ፤ በታ​ላቅ ፍር​ድም እታ​ደ​ጋ​ች​ኋ​ለሁ፤


ግብ​ፃ​ው​ያን ሰዎች እንጂ አም​ላክ አይ​ደ​ሉም፤ ፈረ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም ሥጋ እንጂ መን​ፈስ አይ​ደ​ሉም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ነ​ርሱ ላይ እጁን በዘ​ረጋ ጊዜ፥ ረጂው ይሰ​ና​ከ​ላል፤ ተረ​ጂ​ውም ይወ​ድ​ቃል፤ ሁሉም በአ​ንድ ላይ ይጠ​ፋሉ።


እኔም በተ​ዘ​ረ​ጋች እጅና በብ​ርቱ ክንድ፥ በቍ​ጣና በመ​ዓት፥ በታ​ላ​ቅም መቅ​ሠ​ፍት አወ​ጋ​ች​ኋ​ለሁ።


“የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ቍጣ​ዬና መቅ​ሠ​ፍቴ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሚ​ኖሩ ላይ እንደ ፈሰሰ፥ እን​ዲሁ ወደ ግብፅ በገ​ባ​ችሁ ጊዜ መዓቴ ይፈ​ስ​ስ​ባ​ች​ኋል፤ እና​ን​ተም ለጥ​ላ​ቻና ለጥ​ፋት ለስ​ድ​ብና ለር​ግ​ማን ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ ይች​ንም ስፍራ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አታ​ዩ​አ​ትም።


ስለ​ዚህ መዓ​ቴና መቅ​ሠ​ፍቴ ወረደ፤ በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ ነደደ፤ ዛሬም እንደ ሆነው ጠፍና ባድማ ሆኑ።


መሳ​ፍ​ን​ቶ​ች​ዋ​ንና ጥበ​በ​ኞ​ች​ዋ​ንም፥ አለ​ቆ​ች​ዋ​ንና ሹሞ​ች​ዋን፥ ኀያ​ላ​ኖ​ች​ዋ​ንም አሰ​ክ​ራ​ለሁ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም አን​ቀ​ላ​ፍ​ተው አይ​ነ​ቁም ይላል ስሙ ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ባ​ለው ንጉሥ።


ዳሌጥ። ቀስ​ቱን እንደ ተቃ​ዋሚ ጠላት ገተረ፤ እንደ ባላ​ጋ​ራም ቀኝ እጁን አጸና፤ በጽ​ዮን ሴት ልጅ ድን​ኳን ለዐ​ይኑ የሚ​ያ​ም​ረ​ውን ሁሉ ገደለ፤ መዓ​ቱ​ንም እንደ እሳት አፈ​ሰሰ።


ብርም በከ​ውር ውስጥ እን​ደ​ሚ​ቀ​ልጥ፥ እን​ዲሁ በው​ስ​ጥዋ ትቀ​ል​ጣ​ላ​ችሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዓ​ቴን እን​ዳ​ፈ​ሰ​ስ​ሁ​ባ​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።”


እጄ​ንም እዘ​ረ​ጋ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በሚ​ኖ​ሩ​በ​ትም ስፍራ ሁሉ ምድ​ሪ​ቱን ከዴ​ብ​ላታ ምድረ በዳ ይልቅ ውድ​ማና በረሃ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”


ስለ​ዚህ እኔ ደግሞ በመ​ዓት እሠ​ራ​ለሁ፤ ዐይኔ አይ​ራ​ራም፤ እኔም ይቅ​ርታ አላ​ደ​ር​ግም፤ ወደ ጆሮ​ዬም በታ​ላቅ ድምፅ ቢጮኹ አል​ሰ​ማ​ቸ​ውም” አለኝ።


ስለ​ዚህ እነሆ አቅ​በ​ዘ​ብ​ዛ​ታ​ለሁ፤ ወደ ምድረ በዳም አመ​ጣ​ታ​ለሁ፤ ለል​ብ​ዋም እና​ገ​ራ​ለሁ።


跟着我们:

广告


广告