Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 20:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 “ለል​ጆ​ቻ​ቸ​ውም በም​ድረ በዳ እን​ዲህ አል​ኋ​ቸው፦ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ልማድ አት​ሂዱ፤ ሥር​ዐ​ታ​ቸ​ው​ንም አት​ጠ​ብቁ፤ በበ​ደ​ላ​ቸ​ውም አንድ አት​ሁኑ፤ አት​ር​ከ​ሱም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ለልጆቻቸው በምድረ በዳ እንዲህ አልኋቸው፤ “የአባቶቻችሁን ሥርዐት አትከተሉ፤ ወጋቸውን አትጠብቁ፤ ራሳችሁንም በጣዖቶቻቸው አታርክሱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ለልጆቻቸውም በምድረ በዳ እንዲህ አልኋቸው፦ በአባቶቻችሁ ሥርዓት አትሂዱ ወጋቸውንም አትጠብቁ በጣዖቶቻቸውም አትርከሱ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ለልጆቻቸውም እንዲህ ብዬ ነገርኳቸው፦ “የቀድሞ አባቶቻችሁ ባወጡት ድንጋጌ አትመሩ፤ ሥርዓታቸውንም አትከተሉ፤ ወይም በጣዖቶቻቸው አትርከሱ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ለልጆቻቸውም በምድረ በዳ እንዲህ አልኋቸው፦ በአባቶቻችሁ ሥርዓት አትሂዱ ወጋቸውንም አትጠብቁ በጣዖቶቻቸውም አትርከሱ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 20:18
19 交叉引用  

እነ​ርሱ በክፉ መከ​ራና በጭ​ን​ቀት ተሠ​ቃዩ፥ እያ​ነ​ሱም ሄዱ፤


ቃሌን ይሰሙ ዘንድ እንቢ ወደ አሉ ወደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው ኀጢ​አት ተመ​ለሱ፥ ያመ​ል​ኩ​አ​ቸ​ውም ዘንድ እን​ግ​ዶ​ችን አማ​ል​ክት ተከ​ተሉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤትና የይ​ሁዳ ቤት ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ቃል ኪዳን አፈ​ረሱ።


ፍሬ​ዋ​ንና በረ​ከ​ቷ​ንም ትበሉ ዘንድ ወደ ቀር​ሜ​ሎስ አገ​ባ​ኋ​ችሁ፤ ነገር ግን በገ​ባ​ችሁ ጊዜ ምድ​ሬን አረ​ከ​ሳ​ችሁ፤ ርስ​ቴ​ንም አጐ​ሳ​ቈ​ላ​ችሁ።


ዝሙ​ቷም ከንቱ ሆነ፤ እር​ስ​ዋም ከድ​ን​ጋ​ይና ከግ​ንድ ጋር አመ​ነ​ዘ​ረች።


እነ​ር​ሱም ገብ​ተው ወረ​ሱ​አት፤ ነገር ግን ቃል​ህን አል​ሰ​ሙም፤ በሕ​ግ​ህም አል​ሄ​ዱም፤ ያደ​ር​ጉም ዘንድ ካዘ​ዝ​ሃ​ቸው ሁሉ ምንም አላ​ደ​ረ​ጉም፤ ስለ​ዚህ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመ​ጣ​ህ​ባ​ቸው።


“እነ​ሆም ልጅ ቢወ​ልድ፥ እር​ሱም አባቱ የሠ​ራ​ውን ኀጢ​አት አይቶ ቢፈራ፥ እን​ደ​ር​ሱም ባይ​ሠራ፥


“እና​ንተ ግን፦ ልጅ የአ​ባ​ቱን ኀጢ​አት ስለ ምን አይ​ሸ​ከ​ምም? ትላ​ላ​ችሁ። ልጅ ፍር​ድ​ንና ቅን ነገ​ርን በአ​ደ​ረገ፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ሁሉ በጠ​በ​ቀና በአ​ደ​ረገ ጊዜ ፈጽሞ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል።


እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! እኔን ወደ አስ​መ​ረ​ሩኝ ወደ እስ​ራ​ኤል ቤት እል​ክ​ሃ​ለሁ። እነ​ር​ሱና አባ​ቶ​ቻ​ቸው እስከ ዛሬ ድረስ ዐመ​ፁ​ብኝ።


እኔም፦ ከእ​ና​ንተ እያ​ን​ዳ​ንዱ ርኵ​ሰ​ቱን ከፊቱ ያስ​ወ​ግድ፤ በግ​ብ​ፅም ጣዖ​ታት አት​ር​ከሱ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ አል​ኋ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ አፍ​ር​ሰ​ዋ​ልና፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም አል​ጠ​በ​ቁ​ምና፥ አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም የተ​ከ​ተ​ሉት ከንቱ ነገር አስ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የይ​ሁዳ ኀጢ​አት መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም።


ንጥ​ቂያ ይሆ​ናሉ ያላ​ች​ኋ​ቸ​ውን ልጆ​ቻ​ች​ሁን እነ​ር​ሱን አገ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም የና​ቃ​ች​ኋ​ትን ምድር ይወ​ር​ሷ​ታል።


“እና​ንተ አን​ገ​ታ​ችሁ የደ​ነ​ደነ፥ ልባ​ች​ሁም የተ​ደ​ፈነ፥ ጆሮ​አ​ች​ሁም የደ​ነ​ቈረ፥ እንደ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ መን​ፈስ ቅዱ​ስን ዘወ​ትር ትቃ​ወ​ማ​ላ​ችሁ።


ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ።


跟着我们:

广告


广告