ሕዝቅኤል 19:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 እርሱም በአንበሶች መካከል አደገ፤ ደቦል አንበሳም ሆነ፤ ንጥቂያም ተማረ፤ ሰዎችንም ነጥቆ በላ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም6 እርሱም በአንበሶች መካከል ተጐማለለ፤ እየበረታም ሄደ፤ ግዳይ መንጠቅን ተማረ፤ ሰዎችንም በላ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 እርሱም በአንበሶች መካከል ተመላለሰ፤ ደቦል አንበሳም ሆነ፥ አደንም ተማረ፤ ሰዎችን በላ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ከሌሎች አንበሶች ጋር መዞር ጀመረ። ደቦል አንበሳ ሆነ፤ ዐደንንም ተማረ፤ ሰውንም መብላት ጀመረ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 እርሱም በአንበሶች መካከል ተመላለሰ ደቦል አንበሳም ሆነ፥ ንጥቂያም ተማረ፥ ሰዎችንም በላ። 参见章节 |
ኢዮአቄምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሃያ አምስት ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ዘካራ የምትባል የኔሬያሳ ልጅ የራማ ሴት ነበረች፤ አባቶቹም እንዳደረጉ በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ። 5 ‘ሀ’ በእነዚያም ወራት የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደዚያ ሀገር መጣና ሦስት ዓመት ተገዛለት። ከእርሱም ከዳ። 5 ‘ለ’ እግዚአብሔርም የከለዳውያንንና የሶርያውያንን፥ የሞዓባውያንንና የአሞናውያንን ልጆችና የሰማርያን አደጋ ጣዮች ላከበት፤ ከዚህም በኋላ በአገልጋዮቹ በነቢያት እንደ ተነገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል ራቁ። 5 ‘ሐ’ ነገር ግን ምናሴ ስለሠራቸው ኀጢአቶችና ኢዮአቄም ስላፈሰሰው ንጹሕ ደም፥ ኢየሩሳሌምንም በንጹሕ ደም ስለ ሞላት ከፊቱ ይርቁ ዘንድ የእግዚአብሔር ቍጣ በይሁዳ ላይ ነበር። 5 ‘መ’ እግዚአብሔርም ሊያጠፋቸው አልፈለገም ነበር።