ሕዝቅኤል 18:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 ሰውንም ባያስጨንቅ፥ ለባለ ዕዳም መያዣውን ቢመልስ፥ ፈጽሞም ባይቀማ፥ ከእንጀራውም ለተራበ ቢሰጥ፥ የተራቈተውንም ከልብሱ ቢያለብስ፤ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ማንንም አይጨቍንም፤ ነገር ግን በመያዣ የወሰደውን እንኳ ለተበዳሪው ይመልሳል፤ ለተራበ የራሱን እንጀራ፣ ለተራቈተም ልብስ ይሰጣል እንጂ፣ በጕልበት አይቀማም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 ማንንም ሰው ባያስጨንቅ፥ ነገር ግን ለባለ ዕዳው መያዣውን ቢመልስ፥ ባይቀማ፥ ከምግቡ ለተራበ ቢሰጥ፥ የተራቆተውንም በልብስ ቢሸፍን፥ 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 ማንንም አይጨቊንም፤ ነገር ግን በመያዣ የያዘውን ይመልሳል፤ አይቀማም፤ ለተራበ ያበላል፤ ለታረዘ ያለብሳል፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 ሰውንም ባያስጨንቅ ለባለ ዕዳም መያዣውን ቢመልስ ፈጽሞም ባይቀማ ከእንጀራውም ለተራበ ቢሰጥ የተራቈተውንም በልብስ ቢያለብስ፥ 参见章节 |