Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 18:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውም ከሠ​ራው ኀጢ​አት ቢመ​ለስ፥ ፍር​ድ​ንና ቅን ነገ​ር​ንም ቢያ​ደ​ርግ ነፍ​ሱን ይጠ​ብ​ቃል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ክፉም ሰው ግን ከክፉ ሥራው ተመልሶ ቀናውንና ትክክለኛውን ቢያደርግ ሕይወቱን ያድናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ክፉ ሰውም ከሠራው ክፋት ቢመለስ፥ ፍትሕንና ጽድቅንም ቢያደርግ ነፍሱን በሕይወት ያኖራል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 እንዲሁም ክፉ ሰው ኃጢአት መሥራት ትቶ ፍትሓዊና ትክክለኛ ሥራ ቢሠራ ሕይወቱን ያድናል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ኃጢአተኛውም ከሠራው ኃጢአት ቢመለስ ፍርድንና ቅን ነገርንም ቢያደርግ ነፍሱን ይጠብቃል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 18:27
15 交叉引用  

“ኑና እን​ዋ​ቀስ” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ኀጢ​አ​ታ​ችሁ እንደ አለላ ቢሆን እንደ በረዶ አነ​ጻ​ዋ​ለሁ፤ እንደ ደምም ቢቀላ እንደ ባዘቶ አጠ​ራ​ዋ​ለሁ።


ክፉ ሰው መን​ገ​ዱን፥ በደ​ለ​ኛም ዐሳ​ቡን ይተው፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይመ​ለስ፤ እር​ሱም ይም​ረ​ዋል፤ እርሱ ብዙ በደ​ላ​ች​ሁን ይተ​ው​ላ​ች​ኋ​ልና።


እኔም ያል​መ​ለ​ስ​ሁ​ትን የጻ​ድ​ቁን ልብ ወደ ዐመፃ መል​ሳ​ች​ኋ​ልና፥ በሕ​ይ​ወ​ትም ይኖር ዘንድ ከክፉ መን​ገድ እን​ዳ​ይ​መ​ለስ የኀ​ጢ​አ​ተ​ኛ​ውን እጅ አበ​ር​ት​ታ​ች​ኋ​ልና፤


“ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውም ከአ​ደ​ረ​ጋት ኀጢ​አት ሁሉ ቢመ​ለስ፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ሁሉ ቢጠ​ብቅ፥ ፍር​ድ​ንና ቅን ነገ​ር​ንም ቢያ​ደ​ርግ ፈጽሞ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል እንጂ አይ​ሞ​ትም።


ጻድቁ ከጽ​ድቁ ቢመ​ለስ፥ ኀጢ​አ​ት​ንም በሠራ ጊዜ፥ በዚያ ቢሞት፥ እርሱ በአ​ደ​ረ​ገው በደል ይሞ​ታል።


ከሠ​ራው ሁሉ በደል አይቶ ተመ​ል​ሶ​አ​ልና ፈጽሞ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል እንጂ አይ​ሞ​ትም።


እኔም ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን፦ በር​ግጥ ትሞ​ታ​ለህ ባልሁ ጊዜ፥ እርሱ ከኀ​ጢ​አቱ ተመ​ልሶ ፍር​ድ​ንና ቅን ነገ​ርን ቢያ​ደ​ርግ፤


የመ​ለ​ከ​ቱን ድምፅ ሰምቶ ስላ​ል​ተ​ጠ​ነ​ቀቀ ደሙ በራሱ ላይ ይሆ​ናል፤ ቢጠ​ነ​ቀ​ቅስ ኖሮ ነፍ​ሱን በአ​ዳነ ነበር።


ነገር ግን ሄዳችሁ ‘ምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም፤’ ያለው ምን እንደ ሆነ ተማሩ፤ ኀጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና፤” አላቸው።


ሌላም ብዙ ነገር ነገ​ራ​ቸው፤ “ከዚህ ከክፉ ዓለ​ምም ነፍ​ሳ​ች​ሁን አድኑ” ብሎ መከ​ራ​ቸው።


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መመ​ለ​ስ​ንና በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ማመ​ንን ለአ​ይ​ሁ​ድና ለአ​ረ​ማ​ው​ያን እየ​መ​ሰ​ከ​ርሁ፤


አስ​ቀ​ድሜ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በደ​ማ​ስቆ ላሉት፥ ለይ​ሁዳ አው​ራ​ጃ​ዎ​ችም ሁሉ ነገ​ር​ኋ​ቸው፤ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ንስሓ ገብ​ተው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ለሱ ዘንድ፥ ለን​ስ​ሓ​ቸ​ውም የሚ​ገባ ሥራን ይሠሩ ዘንድ አስ​ተ​ማ​ር​ኋ​ቸው።


እን​ግ​ዲህ ኀጢ​አ​ታ​ችሁ ይሰ​ረ​ይ​ላ​ችሁ ዘንድ ንስሓ ግቡ፥ ተመ​ለ​ሱም።


ለራስህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፤ በእነዚህም ጽና፤ ይህን ብታደርግ፥ ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህና።


跟着我们:

广告


广告