Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 17:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 “ታላቅ ክን​ፍና ብዙ ጽፍ​ርም ያለው ሌላ ታላቅ ንስር ነበረ፤ እነ​ሆም ያጠ​ጣው ዘንድ ይህ ወይን ሥሩን ወደ እርሱ ሰደደ፤ ሐረ​ጉ​ንም ከተ​ተ​ከ​ለ​በት ከመ​ደቡ ወደ እርሱ አዘ​ነ​በለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “ ‘ደግሞም ትልቅ ክንፍ ያለውና አካሉ በላባ የተሸፈነ ሌላ ታላቅ ንስር ነበር። ያ የወይን ተክልም ውሃ ለማግኘት ከተተከለበት ቦታ ሥሩን ወደ እርሱ ሰደደ፤ ቅርንጫፉንም ወደ እርሱ ዘረጋ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ትልልቅ ክንፎችና ብዙ ላባ ያለው ሌላ አንድ ትልቅ ንስር ነበረ፥ እነሆም ይህ ወይን እንዲያጠጣው ሥሩን ወደ እርሱ አዘነበለ፥ ቅርንጫፉንም ከተተከለበት ከመደብ ወደ እርሱ ሰደደ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 “እንዲሁም ታላላቅ ክንፎችና ብዙ ላባዎች ያሉት ሌላ ግዙፍ ንስር ነበረ፤ አሁን እንግዲህ የወይን ተክሉ ሥሮቹንና ቅርንጫፎቹን ወደ ንስሩ ዘረጋ፤ ይህንንም ያደረገው ከተተከለበት መደብ ውሃ ያጠጣው ዘንድ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ታላቅ ክንፍና ብዙ ላባም ያለው ሌላ ታላቅ ንስር ነበረ፥ እነሆም፥ ያጠጣው ዘንድ ይህ ወይን ሥሩን ወደ እርሱ አዘነበለ አረጉንም ከተተከለበት ከመደቡ ወደ እርሱ ሰደደ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 17:7
7 交叉引用  

ከፊቱ አው​ጥቶ እስ​ኪ​ጥ​ላ​ቸው ድረስ ይህ ነገር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በይ​ሁዳ ላይ ሆኖ​አ​ልና፤ ሴዴ​ቅ​ያ​ስም በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።


ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ወደ ሰልፍ የሚ​ወጡ ሦስት መቶ ሰባት ሺህ አም​ስት መቶ ሠራ​ዊት ነበሩ፤ እነ​ዚ​ህም ንጉ​ሡን በጠ​ላቱ ላይ የሚ​ያ​ግዙ፥ በታ​ላቅ ኀይል ወደ ሰልፍ የሚ​ወጡ ጽኑ​ዓን ነበሩ።


እርሱ ግን በእ​ርሱ ላይ ሸፈተ፤ ፈረ​ሶ​ች​ንና ብዙ​ንም ሕዝብ ይሰ​ጡት ዘንድ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ወደ ግብፅ ላከ። በውኑ ይከ​ና​ወ​ን​ለት ይሆን? ይህ​ንስ ያደ​ረገ ያመ​ል​ጣ​ልን? ቃል ኪዳ​ን​ንስ ያፈ​ረሰ ያመ​ል​ጣ​ልን?


በበ​ቀ​ለም ጊዜ ቁመቱ ያጠረ፥ ሐረ​ጉም ወደ እርሱ የሚ​መ​ለስ፥ ሥሩም በበ​ታቹ የነ​በረ ሰፊ ወይን ሆነ፤ እን​ዲሁ ወይን ሆነ፤ ሐረ​ግም ሰደደ፤ ቀን​በ​ጥም አወጣ።


ሐረ​ግም ያወጣ፥ ፍሬም ያፈራ፥ የከ​በረ ወይ​ንም ይሆን ዘንድ በመ​ል​ካም መሬት ውስጥ፥ በብ​ዙም ውኃ አጠ​ገብ ተተ​ክሎ ነበር።


ውኃም አበ​ቀ​ለው፥ ቀላ​ይም አሳ​ደ​ገው፥ ወን​ዞ​ችም በተ​ተ​ከ​ለ​በት ዙሪያ ይጎ​ርፉ ነበር፤ ፈሳ​ሾ​ቹ​ንም ወደ ምድረ በዳ ዛፍ ሁሉ ላከ።


跟着我们:

广告


广告