ሕዝቅኤል 17:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 ከፍ ባለው በእስራኤል ተራራ ላይ እተክለዋለሁ፤ ቅርንጫፎችንም ያወጣል፤ ፍሬም ያፈራል፤ ታላቅም ዝግባ ይሆናል፤ በበታቹም ወፎች ሁሉ ያርፋሉ፤ በቅርንጫፎቹም ጥላ በክንፍ የሚበርር ሁሉ ይጠጋል፤ ቅርንጫፉም ይሰፋል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም23 ከፍ ባለው የእስራኤል ተራራ ላይ እተክለዋለሁ፤ ቅርንጫፎች ያወጣል፤ ፍሬ ያፈራል፤ ያማረም ዝግባ ይሆናል። የወፍ ዐይነት ሁሉ መኖሪያውን በዚያ ያደርጋል፤ በቅርንጫፎቹም ጥላ ሥር ያርፋል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 ከፍ ባለው በእስራኤል ተራራ ላይ እተክለዋለሁ፥ ቅርንጫፎችም ያወጣል፥ ፍሬም ያፈራል፥ የተዋበ ዝግባ ይሆናል፥ በበታቹም ወፎች ሁሉ ይኖራሉ፥ በቅርንጫፎቹም ጥላ በክንፍ የሚበርሩ ሁሉ ይቀመጣሉ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 የምተክለው በእስራኤል በሚገኝ በከፍተኛ ተራራ ላይ ነው፤ ይህንንም የማደርገው ቅርንጫፎችን አስገኝቶ ፍሬ በማፍራት የተዋበ የሊባኖስ ዛፍ እንዲሆን ነው። በሥሩም የተለያዩ ወፎች ይኖሩበታል፤ በቅርንጫፎቹም ጥላ ሥር ክንፍ ያላቸው ፍጥረቶች ሁሉ ጎጆዎቻቸውን ይሠሩበታል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 ከፍ ባለው በእስራኤል ተራራ ላይ እተክለዋለሁ፥ ቅርንጫፎችም ያወጣል ፍሬም ያፈራል የከበረም ዝግባ ይሆናል፥ በበታቹም ወፎች ሁሉ ያርፋሉ፥ በቅርንጫፎቹም ጥላ በክንፍ የሚበርር ሁሉ ይጠጋል። 参见章节 |