Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 17:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ተተ​ክ​ሎስ፥ እነሆ ይከ​ና​ወ​ን​ለት ይሆን? የም​ሥ​ራቅ ነፋስ ባገ​ኘው ጊዜ ፈጽሞ አይ​ደ​ር​ቅ​ምን? በተ​ተ​ከ​ለ​በት መደብ ላይ ይደ​ር​ቃል።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በሌላ ስፍራ ቢተከልስ ይጸድቅ ይሆን? የምሥራቅ ነፋስ ሲመታውስ ባደገበት ስፍራ ፈጽሞ አይደርቅምን?’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እነሆ ሲተከልስ ያድግ ይሆንን? የምሥራቅ ነፋስ በመታው ጊዜ ፈጽሞ አይደርቅምን? በተተከለበት መደብ ላይ ይደርቃል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 የወይኑ ተክል ተተክሏል። ታዲያ ጸድቆ ማደግ ይችላልን? ኀይለኛው የበረሓ ነፋስ በሚመታው ጊዜ ባደገበት በመደቡ ላይ እንዳለ ፈጽሞ አይደርቅምን?”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ተተክሎስ፥ እነሆ፥ ይከናወንለት ይሆንን? የምሥራቅ ነፋስ ባገኘው ጊዜ ፈጽሞ አይደርቅምን? በተተከለበት መደብ ላይ ይደርቃል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 17:10
12 交叉引用  

እነ​ሆም፥ ከእ​ነ​ርሱ በኋላ የሰ​ለ​ቱና በነ​ፋስ የተ​መቱ ሰባት እሸ​ቶች ወጡ፤


ሴዴ​ቅ​ያ​ስም ወደ ባቢ​ሎን ይገ​ባል፤ እኔም እስ​ክ​ጐ​በ​ኘው ድረስ በዚያ ይኖ​ራል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን ጋር ብቷጉ ምንም አይ​ቀ​ና​ች​ሁም።”


በዚያ ጊዜ ለዚህ ሕዝ​ብና ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ዲህ ይሏ​ቸ​ዋል፦ በም​ድረ በዳ የሚ​ያ​ስት ጋኔን አለ፤ የሕ​ዝቤ ሴት ልጅ መን​ገ​ድም ለን​ጽ​ሕና ወይም ለቅ​ድ​ስና አይ​ደ​ለም።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦


እን​ዲ​ህም በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በውኑ ይከ​ና​ወ​ን​ለት ይሆን? ይደ​ር​ቅስ ዘንድ፥ አዲስ የበ​ቀ​ለ​ውስ ቅጠሉ ይጠ​ወ​ልግ ዘንድ ሥሩን አይ​ነ​ቅ​ለ​ው​ምን? ፍሬ​ው​ንስ አይ​ለ​ቅ​መ​ው​ምን? ሥሩም የተ​ነ​ቀ​ለው በብ​ርቱ ክን​ድና በብዙ ሕዝብ አይ​ደ​ለም።


ኤፍ​ሬም በሐ​ሰት፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤትና ይሁ​ዳም በተ​ን​ኰል ከበ​ቡኝ፤ አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐወ​ቃ​ቸው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቅዱስ ሕዝብ ተባሉ።


ከወ​ን​ድ​ሞቹ መካ​ከል ይለ​ያል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከም​ድረ በዳ የሚ​ያ​ቃ​ጥል ነፋ​ስን ያመ​ጣል፤ ሥሩን ያደ​ር​ቃል፤ ምን​ጩ​ንም ያነ​ጥ​ፋል፤ ምድ​ርን ያደ​ር​ቃል፤ የተ​ወ​ደዱ ዕቃ​ዎ​ች​ንም ሁሉ ያጠ​ፋል።


በመንገድም አጠገብ በለስ አይቶ ወደ እርስዋ መጣ፤ ከቅጠልም ብቻ በቀር ምንም አላገኘባትምና “ለዘላለሙ ፍሬ አይገኝብሽ፤” አላት። በለሲቱም ያንጊዜውን ደረቀች።


ማለዳም ሲያልፉ በለሲቱን ከሥርዋ ደርቃ አዩአት።


በእኔ የማ​ይ​ኖር ቢኖር እንደ ደረቅ ቅር​ን​ጫፍ ወደ ውጭ ይጥ​ሉ​ታል፤ ሰብ​ስ​በ​ውም በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ሉ​ታል።


እነዚህ ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣችሁ እንደ እድፍ ናቸው፤ እንደ እረኞች ያለ ፍርሃት ራሳቸውን ይጠብቃሉ፤ በነፋስ የተወሰዱ ውሃ የሌለባቸው ደመናዎች፥ ፍሬ የማያፈሩ ሁለት ጊዜ የሞቱ ከነሥራቸው የተነቀሉ በበጋ የደረቁ ዛፎች፥


跟着我们:

广告


广告