Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 16:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 በተ​ወ​ለ​ድ​ሽ​በት ቀን ከሰ​ው​ነ​ትሽ ጕስ​ቍ​ልና የተ​ነሣ በሜዳ ላይ ተጣ​ልሽ እንጂ፥ ከዚህ አን​ዳች ይደ​ረ​ግ​ልሽ ዘንድ ዐይኔ አል​ራ​ራ​ል​ሽም፤ ማንም አላ​ዘ​ነ​ል​ሽም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 በርኅራኄ ዐይን ተመልክቶሽ ወይም ዐዝኖልሽ ከእነዚህ አንዱን እንኳ ያደረገልሽ ሰው አልነበረም፤ ይልቁንም በተወለድሽበት ቀን ተንቀሽ ስለ ነበር ሜዳ ላይ ተጣልሽ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 አዝኖልሽ ከእነዚህ ነገሮች አንዱን እንኳ ሊያደርግልሽ አንድም ዐይን አልራራልሽም፥ ነገር ግን በተወለድሽበት ቀን ሰውነትሽ የተጠላ ስለ ነበር በሜዳ ላይ ተጣልሽ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ከነዚህ ነገሮች አንዱን እንኳ ለማድረግ ለአንቺ ርኅራኄ ያለው ማንም አልነበረም፤ ስትወለጂ የተጠላሽ ስለ ነበርሽ በሜዳ ላይ ተጣልሽ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 በተወለድሽበት ቀን ከሰውነትሽ ጕስቁልና የተነሣ በሜዳ ላይ ተጣልሽ እንጂ ከዚህ አንዳች ይደረግልሽ ዘንድ ዓይን አልራራልሽም፥ ማንም አላዘነልሽም።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 16:5
13 交叉引用  

ሣራም አብ​ር​ሃ​ምን አለ​ችው፥ “ይህ​ችን ባሪያ ከነ​ል​ጅዋ አባ​ር​ራት፤ የዚ​ህች ባሪያ ልጅ ከልጄ ከይ​ስ​ሐቅ ጋር አይ​ወ​ር​ስ​ምና።”


ፈር​ዖ​ንም፥ “የሚ​ወ​ለ​ደ​ውን ወንድ ልጅ ሁሉ ወደ ወንዝ ጣሉት፤ ሴትን ልጅ ሁሉ ግን በሕ​ይ​ወት አድ​ኑ​አት” ብሎ ሕዝ​ቡን ሁሉ አዘዘ።


“በውኑ ሴት፥ ልጅ​ዋን ትረ​ሳ​ለ​ችን? ከማ​ኅ​ፀ​ንዋ ለተ​ወ​ለ​ደ​ውስ አት​ራ​ራ​ምን? ሴት ይህን ብት​ረሳ፥ እኔ አን​ቺን አል​ረ​ሳ​ሽም።


አህ​ያም እን​ደ​ሚ​ቀ​በር ይቀ​በ​ራል፤ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በር ወደ ውጭ ተጐ​ትቶ፥ በው​ራጅ ጨርቅ ተጠ​ቅ​ልሎ ይጣ​ላል።”


ካፍ። ሕፃ​ኑና ጡት የሚ​ጠ​ባው በከ​ተ​ማ​ዪቱ ጎዳና ላይ ሲዝሉ፥ ዐይኔ በእ​ንባ ደከ​መች፤ ልቤም ታወከ፤ ስለ ወገኔ ሴት ልጅ መከራ ክብሬ በም​ድር ላይ ተዋ​ረደ።


ቆፍ። ተነሺ፤ በሌ​ሊት በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ሰዓት ጩኺ፥ በጌ​ታም ፊት ልብ​ሽን እንደ ውኃ አፍ​ስሺ፤ በጎ​ዳና ሁሉ ራስ ላይ በራብ ስለ ደከሙ ስለ ሕፃ​ና​ትሽ ነፍስ እጆ​ች​ሽን ወደ እርሱ አንሺ።


ዮድ። የር​ኅ​ሩ​ኆች ሴቶች እጆች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ቀቅ​ለ​ዋል፤ የወ​ገኔ ሴት ልጅ በመ​ቀ​ጥ​ቀ​ጥዋ መብል ሆኖ​አ​ቸው።


ጋሜል። አራ​ዊት እንኳ ጡታ​ቸ​ውን ገል​ጠው ግል​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ውን አጠቡ፤ የወ​ገኔ ሴት ልጆች ግን እንደ ምድረ በዳ ሰጐን ጨካ​ኞች ሆኑ።


“በአ​ን​ቺም ዘንድ ባለ​ፍሁ ጊዜ፤ በደ​ም​ሽም ተለ​ው​ሰሽ በአ​የ​ሁሽ ጊዜ፦ ከደ​ምሽ ዳኝ አል​ሁሽ፤


አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ኩር​ን​ች​ትና እሾህ ከአ​ንተ ጋር ቢኖ​ሩም፥ አን​ተም በጊ​ን​ጦች መካ​ከል ብት​ቀ​መጥ፥ አት​ፍ​ራ​ቸው፤ ቃላ​ቸ​ው​ንም አት​ፍራ፤ አንተ ቃላ​ቸ​ውን አት​ፍራ፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ አት​ደ​ን​ግጥ፤ እነ​ርሱ ዐመ​ፀኛ ቤት ናቸ​ውና።


በሜ​ዳም የተ​ገ​ደ​ለ​ውን ወይም የሞ​ተ​ውን በድን፥ ወይም የሰ​ውን አጥ​ንት፥ ወይም መቃ​ብር የሚ​ነካ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆ​ናል።


በም​ድረ በዳ አጠ​ገ​ባ​ቸው፤ በጥ​ማ​ትና በድ​ካም ቦታ፥ በው​ድማ ከበ​ባ​ቸው፤ መገ​ባ​ቸው፤ መራ​ቸ​ውም፤ እንደ ዐይን ብሌ​ንም ጠበ​ቃ​ቸው።


跟着我们:

广告


广告