ሕዝቅኤል 16:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)39 በእጃቸውም አሳልፌ እሰጥሻለሁ፤ የምንዝርናሽንም ስፍራ ያፈርሳሉ፤ ከፍ ያለውንም ቦታሽን ይገለብጣሉ፤ ልብስሽንም ይገፉሻል፤ የክብርሽንም ጌጥ ይወስዳሉ፤ ዕራቁትሽንም ይተዉሻል፤ ቷረጃለሽም። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም39 ለወዳጆችሽ አሳልፌ እሰጥሻለሁ፤ እነርሱም ጕብታሽንና የማምለኪያ ኰረብታሽን ያፈርሳሉ፤ ልብስሽን ይገፉሻል፤ ምርጥ ጌጣጌጥሽን ይቀሙሻል፤ ዕርቃንሽንና ባዶ እጅሽን ያስቀሩሻል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)39 በእጃቸውም አሳልፌ እሰጥሻለሁ፥ ጉብታሽን ያፈርሳሉ፥ ከፍ ያለውንም ቦታሽን ይገለብጣሉ፤ ልብሶችሽንም ይገፉሻል፥ የሚያምሩ ጌጣጌጦችሽን ይወስዳሉ፥ ዕርቃንሽንና ዕራቁትሽን ይተዉሻል። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም39 በሥልጣናቸው ሥር እንድትሆኚ አሳልፌ እሰጥሻለሁ፤ እነርሱም መድረክሽንና ከፍተኛ ቦታዎችሽን ያፈራርሳሉ፤ ልብስሽን ገፈው ጌጣጌጥሽንም ወስደው ያራቊቱሻል፤ ባዶ እጅሽንም ያስቀሩሻል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)39 በእጃቸውም አሳልፌ እሰጥሻለሁ፥ የምዝርናሽንም ስፍራ ያፈርሳሉ ከፍ ያለውንም ቦታሽን ይገለብጣሉ፥ ልብስሽንም ይገፉሻል የክብርሽንም ጌጥ ይወስዳሉ፥ ዕርቃንሽን አድርገው ዕራቁትሽን ይተውሻል። 参见章节 |