Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 16:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 በአ​መ​ን​ዝ​ሮ​ችና በደም አፍ​ሳ​ሾች በቀል እበ​ቀ​ል​ሻ​ለሁ፤ በመ​ዓ​ትና በቅ​ን​አት ደምም አስ​ቀ​ም​ጥ​ሻ​ለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 ለአመንዝራና ለነፍሰ ገዳይ ሴቶች የሚገባውን ፍርድ እፈርድብሻለሁ፤ በመዓቴና በቅናቴ እስከ ደም እበቀልሻለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 በአመንዝሮችና በደም አፍሳሽ ሴቶች ላይ የሚፈረደውን ፍርድ እፈርድብሻለሁ፥ የመዓትንና የቅንዓትን ደም አመጣብሻለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 እኔ በአንቺ ላይ፥ ዝሙት በፈጸሙና ሕይወት ባጠፉ ሴቶች ላይ የሚፈረደውን ፍርድ እፈርድብሻለሁ፤ አንቺን በቅናቴና በቊጣዬ አጠፋሻለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 በአመንዝሮችና በደም አፍሳሾች ላይ የሚፈረደውን ፍርድ እፈርድብሻለሁ፥ የመዓትንና የቅንዓትን ደምም አመጣብሻለሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 16:38
26 交叉引用  

ይሁ​ዳም ምራ​ቱን ትዕ​ማ​ርን፥ “ልጄ ሴሎም እስ​ኪ​ያ​ድግ ድረስ በአ​ባ​ትሽ ቤት መበ​ለት ሆነሽ ተቀ​መጪ” አላት፤ እርሱ ደግሞ እንደ ወን​ድ​ሞቹ እን​ዳ​ይ​ሞ​ት​ብኝ ብሎ​አ​ልና። ትዕ​ማ​ርም ሄዳ በአ​ባቷ ቤት ተቀ​መ​ጠች።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከሦ​ስት ወር በኋላ ለይ​ሁዳ፥ “ምራ​ትህ ትዕ​ማር ሴሰ​ነች፤ እነሆ፥ በዝ​ሙት ፀነ​ሰች” ብለው ነገ​ሩት። ይሁ​ዳም፥ “አው​ጡ​አ​ትና በእ​ሳት ትቃ​ጠል” አለ።


የሰ​ውን ደም የሚ​ያ​ፈ​ስስ ሁሉ ስለ​ዚያ ደም ፈንታ ደሙ ይፈ​ስ​ሳል፤ ሰውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መልክ ፈጥ​ሬ​ዋ​ለ​ሁና።


“ሰው ሰውን ቢመታ፥ ቢሞ​ትም፥ የመ​ታው ፈጽሞ ይገ​ደል።


ስለ​ዚህ ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለራብ ስጥ፤ ለሰ​ይ​ፍም እጅ አሳ​ል​ፈህ ስጣ​ቸው፤ ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም የወ​ላድ መካ​ንና መበ​ለ​ቶች ይሁኑ፤ ወን​ዶ​ቻ​ቸ​ውም በሞት ይጥፉ፤ ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም በጦ​ር​ነት ጊዜ በሰ​ይፍ ይመቱ።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ወር​ቄን በት​ነ​ሻ​ልና ከኀ​ጢ​አት ምኞት በሠ​ራ​ሽው ዝሙት ኀፍ​ረተ ሥጋ​ሽን ገል​ጠ​ሻ​ልና በሰ​ጠ​ሻ​ቸ​ውም በል​ጆ​ችሽ ደም፥


ብዙ ሕዝ​ብን ይሰ​በ​ሰ​ቡ​ብ​ሻል፤ በድ​ን​ጋ​ይም ይወ​ግ​ሩ​ሻል፤ በሰ​ይ​ፋ​ቸ​ውም ይወ​ጉ​ሻል።


ስማ​ቸ​ውን ያስ​ጠሩ ሰዎች ሁሉ በመ​ን​ኰ​ራ​ኵ​ርና በሠ​ረ​ገላ፥ በአ​ሕ​ዛ​ብም ጉባኤ ይመ​ጡ​ብ​ሻል፤ ጋሻና አላ​ባሽ ጋሻ፥ ራስ ቍርም ይዘው በዙ​ሪ​ያሽ ጥበቃ ያደ​ር​ጋሉ፤ ፍር​ድ​ንም እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እንደ ፍር​ዳ​ቸ​ውም ይፈ​ር​ዱ​ብ​ሻል።


ቅን​አ​ቴ​ንም በአ​ንቺ ላይ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በመ​ዓ​ትም ያደ​ር​ጉ​ብ​ሻል፤ አፍ​ን​ጫ​ሽ​ንና ጆሮ​ሽ​ንም ከአ​ንቺ ይቈ​ር​ጣሉ፤ ከአ​ን​ቺም የቀረ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃል፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ች​ሽ​ንም ማር​ከው ይወ​ስ​ዳሉ፤ ከአ​ን​ቺም የቀ​ሩ​ትን እሳት ትበ​ላ​ቸ​ዋ​ለች።


ስለ​ዚህ እኔ ሕያው ነኝ! በደም እንደ በደ​ልህ ደም ያሳ​ድ​ድ​ሃል፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በም​ድር ላይ ስለ አፈ​ሰ​ሱት ደም፥ በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ስለ አረ​ከ​ሱ​አት መዓ​ቴን አፈ​ሰ​ስ​ሁ​ባ​ቸው፤


“ማና​ቸ​ውም ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ወይም ከባ​ል​ን​ጀ​ራው ሚስት ጋር ቢያ​መ​ነ​ዝር አመ​ን​ዝ​ራ​ውና አመ​ን​ዝ​ራ​ዪቱ ፈጽ​መው ይገ​ደሉ።


እግዚአብሔር ቀናተኛና ተበቃይ አምላክ ነው፣ እግዚአብሔር ተበቃይና መዓትን የተሞላ ነው፣ እግዚአብሔር ተቃዋሚዎቹን ይበቀላል፥ ለጠላቶቹም ቍጣውን ይጠብቃል።


በእግዚአብሔርም ላይ ኃጢአት ሠርተዋልና እንደ ዕውር እስኪሄዱ ድረስ ሰዎችን አስጨንቃለሁ፣ ደማቸውም እንደ ትቢያ፥ ሥጋቸውም እንደ ጕድፍ ይፈስሳል።


“በብ​ረት መሣ​ሪያ ቢመ​ታው፥ ቢሞ​ትም ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነፍሰ ገዳ​ዩም ፈጽሞ ይገ​ደል።


ሰውም በሚ​ሞ​ት​በት በእጁ ባለው ድን​ጋይ ቢመ​ታው፥ የተ​መ​ታ​ውም ቢሞት፥ እርሱ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነፍሰ ገዳ​ዩም ፈጽሞ ይገ​ደል።


ሰውም በሚ​ሞ​ት​በት በእጁ ባለው በእ​ን​ጨት መሣ​ሪያ ቢመ​ታው፥ የተ​መ​ታ​ውም ቢሞት፥ እርሱ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነፍሰ ገዳ​ዩም ፈጽሞ ይገ​ደል።


ወይም በጥ​ላቻ እስ​ኪ​ሞት ድረስ በእጁ ቢመ​ታው፥ የመ​ታው ፈጽሞ ይገ​ደል፤ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ባለ ደሙ ወይም ተበ​ቃዩ ባገ​ኘው ጊዜ ነፍሰ ገዳ​ዩን ይግ​ደ​ለው።


ሞት የተ​ፈ​ረ​ደ​በ​ትን ነፍሰ ገዳ​ዩ​ንም ለማ​ዳን የነ​ፍስ ዋጋ አት​ቀ​በሉ፤ እርሱ ፈጽሞ ይገ​ደል።


የቅዱሳንንና የነቢያትን ደም ስላፈሰሱ ደምን ደግሞ አጠጥተሃቸዋል፤ የሚገባቸው ነውና፤” ብሎ ሲናገር ሰማሁ።


跟着我们:

广告


广告