Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 16:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 ስለ​ዚህ እነሆ እኔ ከአ​ንቺ ጋር አንድ የሆኑ ውሽ​ሞ​ች​ሽን በአ​ንቺ ላይ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የም​ት​ወ​ጃ​ቸ​ው​ንም ከም​ት​ጠ​ያ​ቸው ጋር በአ​ንቺ ላይ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ይከ​ቡ​ሻል፤ በእ​ነ​ር​ሱም ዘንድ ጕስ​ቍ​ል​ና​ሽን እገ​ል​ጥ​ብ​ሻ​ለሁ፤ ሁሉም ኀፍ​ረ​ት​ሽን ያዩ​ብ​ሻል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 በዚህ ምክንያት ደስ የተሠኘሽባቸውን ወዳጆችሽን፣ የወደድሻቸውንና የጠላሻቸውን ሁሉ እሰበስባለሁ፤ ከየአቅጣጫው ሁሉ በዙሪያሽ እሰበስባቸዋለሁ፤ በፊታቸው ዕርቃንሽን እገልጣለሁ፤ እነርሱም ኀፍረተ ሥጋሽን ሁሉ ያያሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 ስለዚህ እነሆ እኔ ደስ የተሰኘሽባቸውን ወዳጆችሽን ሁሉ፥ የወደድሻቸውን ሁሉ ከጠላሻቸው ሁሉ ጋር እሰበስባቸዋለሁ፤ ሁሉንም ከየአቅጣጫው በአንቺ ላይ እሰበስባቸዋለሁ፥ ራቁትነትሽን ሁሉ እንዲያዩ በፊታቸው ዕርቃንሽን እገልጣለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 በዚህ ምክንያት ከእነርሱ ጋር የተደሰትሽባቸውን ማለት የወደድሻቸውንና የጠላሻቸውን ሁሉ ተጋልጠሽ ዕርቃንሽን ያዩ ዘንድ ከአካባቢው ሰብስቤ አንቺን በፊታቸው አራቊትሻለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 ስለዚህ፥ እነሆ፥ ከእነርሱ ጋር ደስ ያለሽን የወደድሻቸውንም ውሽሞችሽ ሁሉ ከጠላሻቸው ሁሉ ጋር እሰበስባቸዋለሁ፥ በአንቺ ላይ በዙሪያሽ እሰበስባቸዋለሁ፥ ኅፍረተ ሥጋሽንም ሁሉ እንዲያዩ በፊታቸው ኀፍረተ ሥጋሽን እገልጣለሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 16:37
16 交叉引用  

ኀፍ​ረ​ትሽ ይገ​ለ​ጣል፤ ውር​ደ​ት​ሽም ይታ​ያል፤ ጽድቅ ከአ​ንቺ ይወ​ሰ​ዳል፤ እን​ዲ​ሁም በአ​ንቺ ፋንታ ሰውን አሳ​ልፌ አል​ሰ​ጥም።


በል​ብ​ሽም፦ እን​ዲህ ያለ ነገር ስለ ምን ደረ​ሰ​ብኝ? ብትዪ፥ ከኀ​ጢ​አ​ትሽ ብዛት የተ​ነሣ ልብ​ስሽ በስ​ተ​ኋ​ላሽ ተገ​ፎ​አል፤ ተረ​ከ​ዝ​ሽም ተገ​ል​ጦ​አል።


ስለ​ዚ​ህም የል​ብ​ስ​ሽን ዘርፍ በስ​ተ​ኋ​ላሽ ወደ ፊትሽ እገ​ል​ጣ​ለሁ እፍ​ረ​ት​ሽም ይታ​ያል።


ወዳ​ጆ​ችሽ ሁሉ ጠፍ​ተ​ዋ​ልና ወደ ሊባ​ኖስ ወጥ​ተሽ ጩኺ፤ በባ​ሳ​ንም ላይ ድም​ፅ​ሽን አንሺ፤ በባ​ሕ​ሩም ማዶ ጩኺ።


አን​ቺስ ምን ታደ​ር​ጊ​ያ​ለሽ? ቀይ በለ​በ​ስሽ ጊዜ፥ በወ​ርቅ አን​ባ​ርም ባጌ​ጥሽ ጊዜ፥ ዐይ​ን​ሽ​ንም በኵል በተ​ኳ​ልሽ ጊዜ፥ በከ​ንቱ ታጌ​ጫ​ለሽ፤ ፍቅ​ረ​ኞ​ችሽ አቃ​ለ​ሉሽ፥ ነፍ​ስ​ሽን ይሹ​አ​ታል።


ቆፍ። ወዳ​ጆ​ችን ጠራሁ፤ እነ​ር​ሱም ቸል አሉኝ፤ ካህ​ና​ቶ​ችና ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን ያበ​ረቱ ዘንድ መብል ሲፈ​ልጉ በከ​ተማ ውስጥ ሳያ​ገኙ አለቁ።


ሔት። ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እጅግ ኀጢ​አት ሠር​ታ​ለች፤ ስለ​ዚህ ረክ​ሳ​ለች፤ በተ​ጨ​ነ​ቀ​ች​በት ቦታ ያከ​ብ​ሩ​አት የነ​በሩ ሁሉ ውር​ደ​ቷን አይ​ተ​ዋ​ልና አቃ​ለ​ሉ​አት፤ እር​ስ​ዋም እየ​ጮ​ኸች ታለ​ቅ​ሳ​ለች፤ ወደ ኋላ​ዋም ዘወር አለች።


ክፋ​ትሽ እንደ ዛሬው ሳይ​ገ​ለጥ ለሶ​ርያ ሴቶች ልጆ​ችና ለጐ​ረ​ቤ​ቶ​ችዋ ሁሉ በዙ​ሪ​ያ​ሽም ለሚ​ከ​ቡሽ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያት ሴቶች ልጆች መሰ​ደ​ቢያ ሆነ​ሻል።


የባ​ቢ​ሎ​ንም ልጆች ወደ እር​ስዋ መጥ​ተው በመ​ኝ​ታዋ ከእ​ር​ስዋ ጋር ተኙ፤ በዝ​ሙ​ታ​ቸ​ውም አረ​ከ​ሱ​አት፤ እር​ስ​ዋም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ረከ​ሰች፤ ነፍ​ስ​ዋም ከእ​ነ​ርሱ ተለ​የች።


አሁ​ንም በወ​ዳ​ጆ​ችዋ ፊት ነው​ር​ዋን እገ​ል​ጣ​ለሁ፤ ከእ​ጄም ማንም አያ​ድ​ና​ትም።


ዕራ​ቁ​ት​ዋ​ንም እን​ድ​ት​ቆም አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ እንደ ሕፃ​ን​ነ​ትዋ ወራት፥ እንደ ተወ​ለ​ደ​ች​ባት እንደ መጀ​መ​ሪ​ያ​ዪ​ቱም ቀን አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ። እንደ ምድረ በዳም አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ ውኃም እን​ደ​ሌ​ላት ምድር አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ በው​ኃም ጥም እገ​ድ​ላ​ታ​ለሁ።


ስለ​ዚህ ለአ​ሕ​ዛብ አል​ፈው ይሰ​ጣሉ፤ እኔም አሁን እቀ​በ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ንጉ​ሥ​ንና አለ​ቆ​ች​ንም ይቀቡ ዘንድ ፈጽ​መው ያን​ሣሉ።


ያየሃቸውም ዐሥር ቀንዶችና አውሬው ጋለሞታይቱን ይጣላሉ፤ ባዶዋንና ራቁትዋንም ያደርጓታል፤ ሥጋዋንም ይበላሉ፤ በእሳትም ያቃጥሉአታል።


跟着我们:

广告


广告