Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 16:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 የም​ት​ሰ​ስ​ኝ​በ​ትን ቤት ለራ​ስሽ ሠራሽ፤ በአ​ደ​ባ​ባዩ ሁሉ ከፍ ያለ ቦታን አደ​ረ​ግሽ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ለራስሽ ጕብታን አበጀሽ፤ በየአደባባዩም የማምለኪያ ኰረብታ ሠራሽ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ለራስሽ ጉብታን ሠራሽ፥ በየአደባባዩም ከፍ ያለ ቦታን ለራስሽ አዘጋጀሽ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 መድረክ እየሠራሽ በየ አደባባዩ ለራስሽ ከፍ ያለ ቦታ አዘጋጀሽ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ከክፋትሽም ሁሉ በኋላ የምንዝርናን ስፍራ፥ በየአደባባዩም ከፍ ያለ ቦታን ለራስሽ ሠራሽ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 16:24
19 交叉引用  

እነ​ር​ሱም ደግሞ ከፍ ባለው ኮረ​ብታ ሁሉ ላይ፥ ቅጠ​ሉም ከለ​መ​ለመ ዛፍ ሁሉ በታች መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችን ሠሩ፤ ሐው​ል​ቶ​ች​ንና የማ​ም​ለ​ኪያ አፀ​ዶ​ች​ንም ለራ​ሳ​ቸው አቆሙ።


ደግ​ሞም በይ​ሁዳ ተራ​ሮች ላይ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችን ሠራ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን እን​ዲ​ያ​መ​ነ​ዝሩ አደ​ረ​ጋ​ቸው፤ የይ​ሁ​ዳ​ንም ሰዎች አሳ​ታ​ቸው።


በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች ሁሉ ለሌ​ሎች አማ​ል​ክት ያጥን ዘንድ የኮ​ረ​ብታ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችን አሠራ፤ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አስ​ቈጣ።


እና​ንተ በለ​መ​ለመ ዛፍ ሁሉ በታች በጣ​ዖት ደስ የም​ት​ሰኙ፥ እና​ን​ተም በሸ​ለ​ቆች ውስጥ በዓ​ለ​ትም ስን​ጣ​ቂ​ዎች በታች ልጆ​ቻ​ች​ሁን የም​ት​ሠዉ፥ እና​ንተ የጥ​ፋት ልጆ​ችና የዐ​መ​ፀ​ኞች ዘሮች አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምን?


ከፍ ባለ​ውና በረ​ዘ​መ​ውም ተራራ ላይ መኝ​ታ​ሽን አደ​ረ​ግሽ፤ በዚ​ያም መሥ​ዋ​ዕ​ት​ሽን ሠዋሽ።


ይሁዳ ሆይ! አማ​ል​ክ​ትህ እንደ ከተ​ሞ​ችህ ቍጥር እን​ዲሁ ናቸው፤ እንደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም መን​ገ​ዶች ቍጥር ለነ​ው​ረኛ ነገር ለበ​ዓል ታጥ​ኑ​ባ​ቸው ዘንድ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ችን አድ​ር​ጋ​ች​ኋል።


በሜዳ ያለው ተራ​ራዬ ሆይ! ባለ​ጠ​ግ​ነ​ት​ህ​ንና መዝ​ገ​ብ​ህን ሁሉ፥ የኮ​ረ​ብ​ታ​ውን መስ​ገ​ጃ​ዎ​ች​ህ​ንም ስለ ኀጢ​አ​ትህ በድ​ን​በ​ሮ​ችህ ሁሉ ለመ​በ​ዝ​በዝ እሰ​ጣ​ለሁ።


ከጥ​ንት ጀምሬ ቀን​በ​ር​ሽን ሰብ​ሬ​አ​ለሁ፤ እስ​ራ​ት​ሽ​ንም ቈር​ጫ​ለሁ፤ አን​ቺም፦ አላ​ገ​ለ​ግ​ልም አልሽ፤ ነገር ግን ከፍ ባለው ኮረ​ብታ ሁሉ ላይ፤ ከለ​ም​ለ​ምም ዛፍ ሁሉ በታች ለማ​መ​ን​ዘር ተጋ​ደ​ምሽ።


ዐይ​ኖ​ች​ሽን አቅ​ን​ተሽ አንሺ፤ ያል​ተ​ጋ​ደ​ም​ሽ​በት ስፍራ እን​ዳ​ለም ተመ​ል​ከች። እንደ ምድረ በዳ ቍራ​ዎች በመ​ን​ገድ ላይ ተቀ​ም​ጠሽ በዝ​ሙ​ት​ሽና በክ​ፋ​ትሽ ምድ​ሪ​ቱን አር​ክ​ሰ​ሻ​ታ​ልና።


“ከዚ​ህም ከክ​ፋ​ትሽ ሁሉ በኋላ ወዮ​ልሽ! ወዮ​ልሽ! ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በየ​መ​ን​ገዱ ራስ የም​ን​ዝ​ር​ና​ሽን ስፍራ ሠር​ተ​ሻል፤ በየ​አ​ደ​ባ​ባ​ዩም ከፍ ያለ​ውን ቦታ​ሽን አድ​ር​ገ​ሻል። ዋጋ​ዋን እን​ደ​ም​ት​ሰ​በ​ስብ እንደ ጋለ​ሞ​ታም አል​ሆ​ን​ሽም።


በእ​ጃ​ቸ​ውም አሳ​ልፌ እሰ​ጥ​ሻ​ለሁ፤ የም​ን​ዝ​ር​ና​ሽ​ንም ስፍራ ያፈ​ር​ሳሉ፤ ከፍ ያለ​ው​ንም ቦታ​ሽን ይገ​ለ​ብ​ጣሉ፤ ልብ​ስ​ሽ​ንም ይገ​ፉ​ሻል፤ የክ​ብ​ር​ሽ​ንም ጌጥ ይወ​ስ​ዳሉ፤ ዕራ​ቁ​ት​ሽ​ንም ይተ​ዉ​ሻል፤ ቷረ​ጃ​ለ​ሽም።


የኮ​ረ​ብታ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ቻ​ች​ሁን አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ በእጅ የተ​ሠሩ የዕ​ን​ጨት ምስ​ሎ​ቻ​ች​ሁ​ንም አጠ​ፋ​ለሁ፤ ሬሳ​ች​ሁ​ንም በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ችሁ ሬሳ​ዎች ላይ እጥ​ላ​ለሁ፤ ነፍ​ሴም ትጸ​የ​ፋ​ች​ኋ​ለች።


跟着我们:

广告


广告