Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 16:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በወ​ር​ቅና በብር አጌ​ጥሽ፤ ልብ​ስ​ሽም ጥሩ በፍ​ታና ሐር፥ ወርቀ ዘቦም ነበረ፤ አን​ቺም መል​ካ​ምን ዱቄ​ትና ማርን፥ ዘይ​ት​ንም በላሽ፤ ወፈ​ርሽ፤ እጅ​ግም ውብ ሆንሽ፤ ለመ​ን​ግ​ሥ​ትም የተ​ዘ​ጋ​ጀሽ አደ​ረ​ግ​ሁሽ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 በወርቅና በብር አጌጥሽ፤ ልብስሽም ያማረ በፍታ፣ ሐርና ወርቀ ዘቦ ነበር፤ ምግብሽም የላመ ዱቄት፣ ማርና የወይራ ዘይት ነበር። እጅግ ውብ ሆንሽ፤ ንግሥት ለመሆንም በቃሽ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በወርቅና በብር አጌጥሽ፥ ልብስሽም ጥሩ በፍታ፥ ሐርና ወርቀዘቦ ነበር፥ የላመ ዱቄት፥ ማርና ዘይትም በላሽ፥ እጅግ በጣም ውብ ሆንሽ፥ ለንግሥትነትም በቃሽ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ከብርና ከወርቅ የተሠሩ ብዙ ጌጣጌጦች ነበሩሽ፤ ከልዩ ልዩ ሐር የተሠሩና በጥልፍ ጌጥ የተዋቡ ውድ ልብሶች ነበሩሽ፤ ምርጥ ከሆነ ዱቄት የተጋገረ ዳቦ፥ ማርና የወይራ ዘይት ትመገቢ ነበር፤ ውበትሽ እጅግ እየጨመረ ስለ ሄደ ንግሥት ለመሆን በቃሽ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በወርቅና በብር አጌጥሽ፥ ልብስሽም ጥሩ በፍታና ሐር ወርቀ ዘቦም ነበረ፥ አንቺም መልካም ዱቄትና ማርን ዘይትንም በላሽ፥ እጅግ በጣም ውብ ሆንሽ ለመንግሥትም ደረስሽ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 16:13
25 交叉引用  

እጅ​ግም በጣም አበ​ዛ​ሃ​ለሁ፤ ሕዝ​ብም፥ ነገ​ሥ​ታ​ትም ከአ​ንተ እን​ዲ​ወጡ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ።


ዳዊ​ትም በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ላይ ነገሠ፤ ዳዊ​ትም ለሕ​ዝቡ ሁሉ ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን አደ​ረ​ገ​ላ​ቸው።


ሰሎ​ሞ​ንም ከወ​ንዙ ጀምሮ እስከ ግብፅ ምድር ዳርቻ እስከ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሀገር ድረስ በመ​ን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ ላይ ነግሦ ነበር፤ ግብ​ርም ያመ​ጡ​ለት ነበር፤ በዕ​ድ​ሜ​ውም ሙሉ ለሰ​ሎ​ሞን ይገዙ ነበር።


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም እጅግ ኀያ​ላን ነገ​ሥ​ታት ነበሩ፤ በወ​ን​ዝም ማዶ ያለ​ውን ሀገር ሁሉ ይገዙ ነበር፤ ግብ​ር​ንና እጅ መን​ሻ​ንም ይቀ​በሉ ነበር።


እን​ደ​ዚ​ህም ብለው መለ​ሱ​ልን፦ እኛ የሰ​ማ​ይና የም​ድር አም​ላክ ባሪ​ያ​ዎች ነን፥ ከብ​ዙም ዘመን ጀምሮ ተሠ​ርቶ የነ​በ​ረ​ውን፥ ታላ​ቁም የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ሠርቶ ፈጽ​ሞ​ላ​ቸው የነ​በ​ረ​ውን ቤት እን​ሠ​ራ​ለን።


ቅቤ በመ​ን​ገዴ ይፈ​ስስ በነ​በረ ጊዜ፥ ወተት በተ​ራ​ራዬ ይፈ​ስ​ስ​ልኝ በነ​በረ ጊዜ።


የሰው ልጆች ባለ​ጠ​ጎ​ችና ድሆች፥ በየ​ሀ​ገ​ራ​ችሁ በአ​ን​ድ​ነት።


ከበ​ደሌ ፈጽሞ እጠ​በኝ፥ ከኀ​ጢ​አ​ቴም አን​ጻኝ፤


አባ​ቶ​ቻ​ችን ያከ​በ​ሩት ክብ​ራ​ችን ቤተ መቅ​ደ​ስህ በእ​ሳት ተቃ​ጥ​ሎ​አል፤ ያማ​ረ​ውም ስፍ​ራ​ችን ፈር​ሶ​አል።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ! ዐይ​ን​ሽን አን​ሥ​ተሽ እነ​ዚ​ህን ከሰ​ሜን የሚ​መ​ጡ​ትን ተመ​ል​ከቺ፤ ለአ​ንቺ የሰ​ጠ​ሁሽ መንጋ፤ የክ​ብር በጎ​ችሽ ወዴት አሉ?


ሳም​ኬት። መን​ገድ ዐላ​ፊ​ዎች ሁሉ እጃ​ቸ​ውን ያጨ​በ​ጭ​ቡ​ብ​ሻል፦ “በውኑ የም​ድር ሁሉ ደስታ፥ አክ​ሊ​ልና ክብር የሚ​ሉ​አት ከተማ ይህች ናትን?” እያሉ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሴት ልጅ ላይ ያፍ​ዋ​ጫሉ፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም ይነ​ቀ​ን​ቃሉ።


ወርቀ ዘቦም አለ​በ​ስ​ሁሽ፤ ጥቁር ጫማም አደ​ረ​ግ​ሁ​ልሽ፤ በጥሩ በፍታ አስ​ታ​ጠ​ቅ​ሁሽ፤ በሐ​ርም ከደ​ን​ሁሽ።


ከሰ​ጠ​ሁ​ሽም ከወ​ር​ቄና ከብሬ የተ​ሠ​ራ​ውን የክ​ብ​ር​ሽን ዕቃ ወስ​ደሽ የወ​ንድ ምስ​ሎ​ችን ለራ​ስሽ አድ​ር​ገ​ሻል፤ አመ​ን​ዝ​ረ​ሽ​ባ​ቸ​ው​ማል።


የሰ​ጠ​ሁ​ሽ​ንም እን​ጀ​ራ​ዬን፥ ያበ​ላ​ሁ​ሽ​ንም ዱቄ​ትና ዘይ​ቱን፥ ማሩ​ንም ጣፋጭ ሽታ አድ​ር​ገሽ በፊ​ታ​ቸው አኖ​ርሽ፤ እን​ዲ​ህም ሆኖ​አል፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ከሩቅ ሀገ​ርም ወደ​መጡ ሰዎች መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላኩ፤ እነ​ር​ሱም በደ​ረሱ ጊዜ ይታ​ጠ​ባሉ፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይኳ​ላሉ፤ ያጌ​ጣ​ሉም።


የሶ​ር​ያም ሰዎች ከገ​ን​ዘ​ብሽ ብዛት የተ​ነሣ ነጋ​ዴ​ዎ​ችሽ ነበሩ፥ ከአ​ን​ቺም ጋር አንድ ከሆኑ ከብዙ ሰዎች ጋር ትነ​ግጂ ነበር፤ ነጭ ሐር​ንና ዕን​ቍን፥ ቀይ ሐር​ንና ወርቀ ዘቦን ከር​ከ​ዴን የሚ​ባል ዕን​ቍ​ንና ልባ​ን​ጃም የሚ​ባል ሽቱን ከተ​ር​ሴስ ያመ​ጡ​ልሽ ነበር፤ ገበ​ያ​ሽ​ንም ረዓ​ሙ​ትና ቆር​ኮር መሉት።


እና​ታ​ቸው አመ​ን​ዝ​ራ​ለ​ችና፤ የወ​ለ​ደ​ቻ​ቸ​ውም፥ “እን​ጀ​ራ​ዬ​ንና ውኃ​ዬን፥ ቀሚ​ሴ​ንና መደ​ረ​ቢ​ያ​ዬን፥ ዘይ​ቴ​ንና የሚ​ገ​ባ​ኝን ሁሉ የሚ​ሰ​ጡኝ ወዳ​ጆ​ችን እከ​ተ​ላ​ቸው ዘንድ እሄ​ዳ​ለሁ” ብላ​ለ​ችና አሳ​ፈ​ረ​ቻ​ቸው።


ስንዴ፥ ገብ​ስም፥ ወይ​ንም፥ በለ​ስም፥ ሮማ​ንም ወደ ሞሉ​ባት፥ ወይ​ራም፥ ቅቤም፥ ማርም ወደ ሞሉ​ባት ምድር፥


ሳሙ​ኤ​ልም የዘ​ይ​ቱን ቀንድ ወስዶ በራሱ ላይ አፈ​ሰ​ሰው፤ ሳመ​ውም፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “በሕ​ዝቡ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ትነ​ግሥ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀብ​ቶ​ሃል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሕዝብ ትገ​ዛ​ለህ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ካሉ ጠላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ ታድ​ና​ቸ​ዋ​ለህ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በር​ስቱ ላይ ትነ​ግሥ ዘንድ እንደ ቀባህ ምል​ክቱ ይህ ነው።


የአ​ሞ​ንም ልጆች ንጉሥ ናዖስ እንደ መጣ​ባ​ችሁ ባያ​ችሁ ጊዜ፥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ንጉ​ሣ​ችሁ ሳለ፦ እን​ዲህ አይ​ሁን፤ ነገር ግን ንጉሥ አን​ግ​ሥ​ልን አላ​ች​ሁኝ።


跟着我们:

广告


广告