Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 14:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ከሚ​ቀ​መጡ መጻ​ተ​ኞች የሚ​ሆን፥ ከእኔ ተለ​ይቶ ጣዖ​ቶ​ቹን በልቡ የሚ​ያ​ኖር፥ የበ​ደ​ሉ​ንም መቅ​ሠ​ፍት በፊቱ የሚ​ያ​ቆም ሰው ሁሉ ስለ እኔ ይጠ​ይቅ ዘንድ ወደ ነቢዩ በመጣ ጊዜ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በራሴ እመ​ል​ስ​ለ​ታ​ለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “ ‘ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በእስራኤል የሚኖር ማንኛውም መጻተኛ ራሱን ከእኔ በመለየት ጣዖቶችን በልቡ አኑሮ፣ ክፋቱንም የማሰናከያ ድንጋይ በማድረግ በፊቱ አስቀምጦ ከእኔ ለመጠየቅ ወደ ነቢይ ቢመጣ፣ እኔ ራሴ እግዚአብሔር እመልስለታለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ማንም ከእስራኤልም ቤት፥ በእስራኤልም የሚቀመጥ መጻተኛ፥ ራሱን ከእኔ የሚለይ፥ ጣዖቶቹን በልቡ የሚያኖር፥ የበደሉንም የማሰናከያ ድንጋይ በፊቱ የሚያቆም፥ ስለ እኔም ለመጠየቅ ወደ ነቢዩ የሚመጣ፥ እኔ ጌታ ራሴ እመልስለታለሁ፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 “ከእስራኤላውያን አንዱ ወይም በእነርሱ መካከል ከሚኖሩ ባዕዳን ሰዎች አንዱ ከእኔ ተለይቶ ጣዖቶችን በማምለክ ኃጢአት የሚሠራ ቢሆን፥ በደሉም በፊቱ ዕንቅፋት እንዲሆንበት ቢያደርግና እንደገና ደግሞ ምክር ለመጠየቅ ወደ ነቢያት የሚመጣ ከሆነ እኔ እግዚአብሔር ራሴ መልስ እሰጠዋለሁ!

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ከእስራኤልም ቤት፥ በእስራኤልም ዘንድ ከሚቀመጡ መጻተኞች የሚሆን፥ ከእኔ ተለይቶ ጣዖቶቹን በልቡ የሚያኖር፥ የበደሉንም መቅሠፍት በፊቱ የሚያቆም ሰው ሁሉ፥ ስለ እኔ ይጠይቅ ዘንድ ወደ ነቢዩ በመጣ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር በራሴ እመልስለታለሁ፥

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 14:7
24 交叉引用  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፋሲካ ያደ​ርግ ዘንድ ወደ እና​ንተ የመጣ መጻ​ተኛ ቢኖር ወን​ዱን ሁሉ ትገ​ር​ዛ​ለህ፤ ያን ጊዜም ፋሲካ ያደ​ርግ ዘንድ ይገ​ባል፤ እንደ ሀገር ልጅም ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል፤ ያል​ተ​ገ​ረዘ ሁሉ ግን ከእ​ርሱ አይ​ብላ።


ሰባ​ተ​ኛዋ ቀን ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ም​ላ​ክህ ሰን​በት ናት፤ አንተ፥ ወንድ ልጅ​ህም፥ ሴት ልጅ​ህም፥ ሎሌ​ህም፥ ገረ​ድ​ህም፥ አህ​ያ​ህም፥ ከብ​ት​ህም፥ በደ​ጆ​ች​ህም ውስጥ ያለ እን​ግዳ በእ​ር​ስዋ ምንም ሥራ አት​ሥሩ፤


አቤቱ፥ ከመ​ን​ገ​ድህ ለምን አሳ​ት​ኸን? እን​ዳ​ን​ፈ​ራ​ህም ልባ​ች​ንን ለምን አጸ​ና​ህ​ብን? ስለ ባሪ​ያ​ዎ​ችህ ስለ ርስ​ትህ ነገ​ዶች ተመ​ለስ፤


ንጉ​ሡም ሴዴ​ቅ​ያስ ልኮ አስ​መ​ጣው፥ ንጉ​ሡም በቤቱ፥ “በውኑ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የሆነ ቃል አለን?” ብሎ በቈ​ይታ ጠየ​ቀው። ኤር​ም​ያ​ስም፥ “አዎን አለ፤ ደግ​ሞም በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ እጅ አል​ፈህ ትሰ​ጣ​ለህ” አለው።


ደግሞ ጻድቁ ከጽ​ድቁ ተመ​ልሶ ኀጢ​አት በሠራ ጊዜ እኔ በፊቱ ዕን​ቅ​ፋት ባደ​ርግ፥ እርሱ ይሞ​ታል፤ አን​ተም አል​ነ​ገ​ር​ኸ​ው​ምና በኀ​ጢ​አቱ ይሞ​ታል፤ ያደ​ረ​ጋ​ትም የጽ​ድቅ ነገር አት​ታ​ሰ​ብ​ለ​ትም፤ ደሙን ግን ከእ​ጅህ እፈ​ል​ጋ​ለሁ።


ወን​ዶ​ችም ደግሞ ከአ​መ​ን​ዝ​ሮች ጋር ይጫ​ወ​ታ​ሉና፥ ከጋ​ለ​ሞ​ቶ​ችም ጋር ይሠ​ዋ​ሉና ሴቶች ልጆ​ቻ​ችሁ በሰ​ሰኑ ጊዜ፥ ሙሽ​ሮ​ቻ​ች​ሁም በአ​መ​ነ​ዘሩ ጊዜ አል​ቀ​ጣ​ኋ​ቸ​ውም፤ የማ​ያ​ስ​ተ​ው​ልም ሕዝብ ከአ​መ​ን​ዝራ ጋር ይቀ​ላ​ቀ​ላል።


በቀ​ንም ትደ​ክ​ማ​ለህ፤ ነቢ​ዩም ከአ​ንተ ጋር ይደ​ክ​ማል፤ እና​ታ​ች​ሁም ሌሊ​ትን ትመ​ስ​ላ​ለች።


እስ​ራ​ኤ​ልን በም​ድረ በዳ እንደ አለ ወይን ሆኖ አገ​ኘ​ሁት፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያዋ ዓመት እንደ በለስ በኵ​ራት ሆነው አየ​ኋ​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን ወደ ብዔ​ል​ፌ​ጎር መጡ፤ ለነ​ው​ርም ተለዩ፤ እንደ ወደ​ዱ​ትም ርኩስ ሆኑ።


“ይህም የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሁ​ን​ላ​ችሁ።


“ደግሞ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እን​ዲህ በላ​ቸው፦ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወይም በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ከሚ​ቀ​መጡ እን​ግ​ዶች ማና​ቸ​ውም ሰው ዘሩን ለሞ​ሎክ አገ​ል​ግ​ሎት ቢሰጥ ፈጽሞ ይገ​ደል፤ የሀ​ገሩ ሕዝብ በድ​ን​ጋይ ይው​ገ​ሩት።


እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና ለመ​ጻ​ተ​ኛና ለሀ​ገር ልጅ አንድ ዐይ​ነት ሕግ ይሁ​ን​ላ​ችሁ።”


ለእ​ና​ንተ፥ በእ​ና​ን​ተም መካ​ከል ለሚ​ኖሩ መጻ​ተ​ኞች አንድ ሥር​ዐት ይሆ​ናል፤ ለልጅ ልጃ​ች​ሁም የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሆ​ናል፤ እና​ንተ እንደ ሆና​ችሁ እን​ዲሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መጻ​ተኛ ይሆ​ናል።


ትው​ልዱ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ቢሆን፥ ወይም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው የሚ​ኖር መጻ​ተኛ ቢሆን፥ ሳያ​ውቅ ኀጢ​አ​ትን ለሚ​ሠራ ሁሉ ሕጉ አንድ ይሆ​ን​ለ​ታል።


“የዚ​ህ​ንም ርግ​ማን ቃሎች በሰ​ማ​ችሁ ጊዜ በልቡ ‘ይህን በልቤ ስን​ፍና በማ​ድ​ረግ ሄጃ​ለ​ሁና ይቅር ይለ​ኛል’ የሚል ቢኖር የበ​ደ​ለኛ ፍዳ ካል​በ​ደለ ጋር እን​ዳ​ይ​ተ​ካ​ከል፥


እነዚህ የሚያለያዩ ሥጋውያንም የሆኑ መንፈስም የሌላቸው ሰዎች ናቸው።


跟着我们:

广告


广告