Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 14:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ስለ​ዚህ ንገ​ራ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፥ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ከእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ጣዖ​ቶ​ቹን በልቡ የሚ​ያ​ኖር፥ የበ​ደ​ሉ​ንም መቅ​ሠ​ፍት በፊቱ የሚ​ያ​ቆም ሰው ሁሉ ወደ ነቢዩ ቢመጣ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ጣዖ​ታቱ ብዛት እመ​ል​ስ​ለ​ታ​ለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ስለዚህ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ማንኛውም እስራኤላዊ ጣዖትን በልቡ አኑሮ፣ ክፋቱንም የማሰናከያ ድንጋይ አድርጎ በፊቱ በማስቀመጥ ወደ ነቢይ ቢመጣ፣ እኔ እግዚአብሔር እንደ ጣዖቱ ብዛት እመልስለታለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ስለዚህ ተናገራቸው፥ እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ማንም ሰው ከእስራኤል ቤት ጣዖቶቹን በልቡ የሚያኖር፥ የበደሉንም የማሰናከያ ድንጋይ በፊቱ የሚያቆም፥ ወደ ነቢዩም የሚመጣ፥ እኔ ጌታ እንደ ጣዖታቱ ብዛት እመልስለታለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ንገራቸው፦ “ከእስራኤል ሕዝብ መካከል ልባቸውን ለጣዖቶች የሰጡና የጣዖት አምልኮአቸው በፊታቸው ዕንቅፋት እንዲሆንባቸው ያደረጉ አሉ፤ እነዚህ ሰዎች ወደ ነቢዩ የሚመጡ ከሆነ እኔ እግዚአብሔር እንደ ጣዖቶች ብዛት ተገቢ መልስ እሰጣቸዋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4-5 ስለዚህ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሁሉም በጣዖቶቻቸው ከእኔ ተለይተዋልና የእስራኤልን ቤት በልባቸው እይዝ ዘንድ ከእስራኤል ቤት ጣዖቶቹን በልቡ የሚያኖር፥ የበደሉንም መቅሠፍት በፊቱ የሚያቆም ሰው ሁሉ ወደ ነቢዩ በመጣ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ጣዖታቱ ብዛት እመልስለታለሁ ብለህ ንገራቸው።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 14:4
12 交叉引用  

ኤል​ያ​ስም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የአ​ቃ​ሮ​ንን አም​ላክ ብዔ​ል​ዜ​ቡ​ልን ትጠ​ይቅ ዘንድ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ለምን ላክህ? በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አም​ላክ ስለ​ሌለ ነውን? እን​ደ​ዚህ አይ​ደ​ለም፤ ትሞ​ታ​ለህ እንጂ ከወ​ጣ​ህ​በት አልጋ አት​ወ​ር​ድም” አለው።


እንደ እጁ ሥራ ፍዳው ይደ​ረ​ግ​በ​ታ​ልና ለበ​ደ​ለኛ ወዮ! ክፉም ይደ​ር​ስ​በ​ታል።


እኔ ግን አዋ​ር​ዳ​ቸው ዘንድ፥ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም እበ​ቀ​ላ​ቸው ዘንድ እፈ​ቅ​ዳ​ለሁ፤ እኔ በጠ​ራሁ ጊዜ አል​መ​ለ​ሱ​ል​ኝ​ምና፥ በተ​ና​ገ​ር​ሁም ጊዜ አል​ሰ​ሙ​ኝም፤ በፊ​ቴም ክፉ ነገ​ርን አደ​ረጉ፤ ያል​ወ​ደ​ድ​ሁ​ት​ንም መረጡ።”


“የሰው ልጅ ሆይ! እነ​ዚህ ሰዎች በል​ባ​ቸው ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አኑ​ረ​ዋል፤ የበ​ደ​ላ​ቸ​ው​ንም መቅ​ሠ​ፍት በፊ​ታ​ቸው አቁ​መ​ዋል፤ እኔስ ለእ​ነ​ርሱ መልስ ልመ​ል​ስ​ላ​ቸ​ውን?


ስለ​ዚህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት እን​ዲህ በል፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ንስሓ ግቡ፤ ከበ​ደ​ላ​ች​ሁም ተመ​ለሱ፤ ፊታ​ች​ሁ​ንም ከኀ​ጢ​አ​ታ​ችሁ ሁሉ መልሱ።


ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ከሚ​ቀ​መጡ መጻ​ተ​ኞች የሚ​ሆን፥ ከእኔ ተለ​ይቶ ጣዖ​ቶ​ቹን በልቡ የሚ​ያ​ኖር፥ የበ​ደ​ሉ​ንም መቅ​ሠ​ፍት በፊቱ የሚ​ያ​ቆም ሰው ሁሉ ስለ እኔ ይጠ​ይቅ ዘንድ ወደ ነቢዩ በመጣ ጊዜ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በራሴ እመ​ል​ስ​ለ​ታ​ለሁ።


እነ​ርሱ ዐመ​ፀኛ ቤት ስለ​ሆኑ ቢሰሙ ወይም ቢደ​ነ​ግጡ ቃሌን ትነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ።


እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ተነ​ሥ​ተህ ወደ እስ​ራ​ኤል ቤት ሂድና ግባ፥ ቃሌ​ንም ንገ​ራ​ቸው።


በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ፊት አገ​ል​ግ​ለ​ዋ​ቸው ነበ​ሩና፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት የኀ​ጢ​አት እን​ቅ​ፋት ሆነ​ዋ​ልና ስለ​ዚህ እጄን በላ​ያ​ቸው አን​ሥ​ቻ​ለሁ፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ይሸ​ከ​ማሉ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፣ የሰማይን ወፎችና የባሕርን ዓሣዎች ማሰናከያንም ከኃጢአተኞች ጋር አጠፋለሁ፣ ሰውንም ከምድር ፊት እቈርጣለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።


跟着我们:

广告


广告