ሕዝቅኤል 14:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 እነዚህ ሦስት ሰዎች በመካከልዋ ቢኖሩ፥ እኔ ሕያው ነኝ! እነርሱ ብቻቸውን ይድናሉ እንጂ ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻቸውን አያድኑም፤ ምድሪቱም ባድማ ትሆናለች፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም16 ‘በሕያውነቴ እምላለሁ!’ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ እነዚህ ሦስቱ ሰዎች ቢኖሩባት እንኳ፣ ወንዶች ወይም ሴቶች ልጆቻቸውን ማዳን አይችሉም፤ እነርሱ ብቻ ይድናሉ፤ ምድሪቱ ግን ባድማ ትሆናለች። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 እነዚህ ሦስት ሰዎች በውስጧ ቢኖሩ፥ እኔ ሕያው ነኝና ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ እነርሱ ብቻቸውን ይድናሉ እንጂ ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻቸውን አያድኑም፥ ምድሪቱም ባድማ ትሆናለች። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 እኔ እግዚአብሔር ሕያው አምላክ እንደ መሆኔ እነዚያ ሦስት ሰዎች እንኳ በዚያ ቢኖሩ ከራሳቸው ሕይወት በቀር የገዛ ልጆቻቸውን እንኳ ማዳን አይችሉም፤ ምድሪቱም ወደ ምድረ በዳነት ትለወጣለች። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 እነዚህ ሦስት ሰዎች ቢኖሩባት፥ እኔ ሕያው ነኝና እነርሱ ብቻቸውን ይድናሉ እንጂ ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻቸውን አያድኑም፥ ምድሪቱም ባድማ ትሆናለች፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 参见章节 |