Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 13:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 እኔም ያል​መ​ለ​ስ​ሁ​ትን የጻ​ድ​ቁን ልብ ወደ ዐመፃ መል​ሳ​ች​ኋ​ልና፥ በሕ​ይ​ወ​ትም ይኖር ዘንድ ከክፉ መን​ገድ እን​ዳ​ይ​መ​ለስ የኀ​ጢ​አ​ተ​ኛ​ውን እጅ አበ​ር​ት​ታ​ች​ኋ​ልና፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 እኔ ያላሳዘንሁትን ጻድቅ በውሸት ስላሳዘናችሁ፣ ኀጢአተኛም ከክፉ መንገዱ ተመልሶ ሕይወቱን እንዳያድን በኀጢአቱ ስላበረታታችሁት፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ምክንያቱም እኔ ያላሳዘንሁትን የጻድቁን ልብ በውሸት አሳዝናችኋልና፥ ከክፉ መንገዱ ተመልሶ በሕይወትም እንዳይኖር የኃጢአተኛውን እጅ አበርትታችኋልና፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 “እኔ ተስፋ ያላስቈረጥኳቸውን ጻድቃንን ሐሰት በመናገር ተስፋ አስቈርጣችኋል፤ ክፉዎች ሕይወታቸውን ለማዳን ከኃጢአታቸው እንዳይመለሱ አደፋፍራችኋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እኔም ያላሳዘንሁትን የጻድቁን ልብ በውሸት አሳዝናችኋልና፥ በሕይወትም ይኖር ዘንድ ከክፉ መንገድ እንዳይመለስ የኃጢአተኛውን እጅ አበርትታችኋልና

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 13:22
23 交叉引用  

እና​ን​ተም “ከሲ​ኦል ጋር ተማ​ም​ለ​ናል፤ ከሞ​ትም ጋር ቃል ኪዳን አድ​ር​ገ​ናል፤ ሐሰ​ት​ንም መሸ​ሸ​ጊ​ያን አድ​ር​ገ​ና​ልና፥ በሐ​ሰ​ትም ተሰ​ው​ረ​ና​ልና፥ ዐውሎ ነፋ​ስም ባለፈ ጊዜ አይ​ደ​ር​ስ​ብ​ንም” ትላ​ላ​ች​ሁና፥


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ነቢ​ያት ላይ የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግ​ጥን ነገር አይ​ቻ​ለሁ፤ ያመ​ነ​ዝ​ራሉ፤ በሐ​ሰ​ትም ይሄ​ዳሉ፤ ማንም ከክ​ፋቱ እን​ዳ​ይ​መ​ለስ የክፉ አድ​ራ​ጊ​ዎ​ችን እጅ ያበ​ረ​ታሉ፤ ሁሉም እንደ ሰዶም፥ የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ትም እንደ ገሞራ ሆኑ​ብኝ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ለሚ​ያ​ቃ​ልሉ ሰላም ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል፥ በፍ​ላ​ጎ​ታ​ቸ​ውና በል​ቡ​ና​ቸው ክፋት ለሚ​ሄ​ዱም ሁሉ፦ ክፉ ነገር አያ​ገ​ኛ​ች​ሁም” ይላሉ።


ስለ ነቢ​ያት ልቤ በው​ስጤ ተሰ​ብ​ሮ​አል፤ አጥ​ን​ቶ​ችም ሁሉ ታው​ከ​ዋል፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የተ​ነሣ፤ ከጌ​ት​ነ​ቱም ክብር የተ​ነሣ እኔም በመ​ከራ እንደ ተቀ​ጠ​ቀጠ ሰው፥ የወ​ይን ጠጅ እን​ዳ​ሸ​ነ​ፈ​ውም እንደ ሰካ​ራም ሰው ሆኛ​ለሁ።


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ከገጸ ምድር አስ​ወ​ግ​ድ​ሃ​ለሁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ዐመ​ፅን ተና​ግ​ረ​ሃ​ልና በዚህ ዓመት ትሞ​ታ​ለህ” አለው።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ አሔ​ል​ማ​ዊው ስለ ሸማያ እን​ዲህ ይላል ብለህ ወደ ምር​ኮ​ኞች ሁሉ ላክ፦ እኔ ሳል​ል​ከው ሸማያ ትን​ቢት ተና​ግ​ሮ​ላ​ች​ኋ​ልና፥ በሐ​ሰ​ትም እን​ድ​ት​ታ​መኑ አድ​ር​ጓ​ች​ኋ​ልና።


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ አሔ​ል​ማ​ዊ​ውን ሸማ​ያ​ንና ዘሩን እቀ​ጣ​ለሁ፤ እኔም ለሕ​ዝቤ የማ​ደ​ር​ገ​ውን መል​ካ​ሙን ነገር የሚ​ያይ ሰው በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ አይ​ኖ​ር​ላ​ቸ​ውም፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ዐመ​ፃን ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።”


ነገር ግን ተመ​ል​ሳ​ችሁ ስሜን አስ​ነ​ቀ​ፋ​ችሁ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ች​ሁም በፈ​ቃ​ዳ​ቸው እን​ዲ​ሄዱ አር​ነት ያወ​ጣ​ች​ኋ​ቸ​ውን ወን​ድና ሴት ባሪ​ያ​ዎ​ቻ​ች​ሁን፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ባሪ​ያ​ዎች እን​ዲ​ሆ​ኑ​ላ​ችሁ መለ​ሳ​ች​ኋ​ቸው።”


እነሆ እኔ አዝ​ዛ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ወደ​ዚ​ህ​ችም ሀገር እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እር​ስ​ዋ​ንም ይወ​ጋሉ፤ ይይ​ዙ​አ​ት​ማል፤ በእ​ሳ​ትም ያቃ​ጥ​ሉ​አ​ታል፤ የይ​ሁ​ዳ​ንም ከተ​ሞች ሰው የሌ​ለ​በት ባድማ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ።”


እኔም፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ ወዮ! አንተ ሰይፍ እስከ ሰው​ነ​ታ​ቸው ድረስ እስ​ክ​ት​ደ​ርስ ሰላም ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል” ብለህ ይህን ሕዝ​ብና ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን እጅግ አታ​ለ​ልህ አልሁ።


የሕ​ዝ​ቤ​ንም ስብ​ራት በጥ​ቂቱ ይፈ​ው​ሳሉ፤ ሰላም ሳይ​ሆን፦ ሰላም ሰላም ይላሉ።


የሕ​ዝ​ቤ​ንም ሴት ልጅ ስብ​ራት በማ​ቃ​ለል ይፈ​ው​ሳሉ፤ ሰላም ሳይ​ሆን፦ ሰላም ሰላም ይላሉ።


እነ​ር​ሱም ስለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ትን​ቢት የሚ​ና​ገሩ፥ የሰ​ላ​ም​ንም ራእይ የሚ​ያ​ዩ​ላት የእ​ስ​ራ​ኤል ነቢ​ያት ናቸው፤ ሰላ​ምም የለም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውም ከአ​ደ​ረ​ጋት ኀጢ​አት ሁሉ ቢመ​ለስ፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ሁሉ ቢጠ​ብቅ፥ ፍር​ድ​ንና ቅን ነገ​ር​ንም ቢያ​ደ​ርግ ፈጽሞ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል እንጂ አይ​ሞ​ትም።


ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውም ከሠ​ራው ኀጢ​አት ቢመ​ለስ፥ ፍር​ድ​ንና ቅን ነገ​ር​ንም ቢያ​ደ​ርግ ነፍ​ሱን ይጠ​ብ​ቃል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “በከ​ተ​ማ​ዪቱ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መካ​ከል እለፍ፥ በመ​ካ​ከ​ል​ዋም ስለ ተሠ​ራው ኀጢ​አት ሁሉ በሚ​ያ​ለ​ቅ​ሱና በሚ​ተ​ክዙ ሰዎች ግን​ባር ላይ ምል​ክት ጻፍ አለው።


ጻድ​ቁን የም​ታ​ስ​ጨ​ንቁ፥ ጉቦ​ንም የም​ት​ቀ​በሉ፥ በበ​ሩም የች​ግ​ረ​ኛ​ውን ፍርድ የም​ታ​ጣ​ምሙ እና​ንተ ሆይ! በደ​ላ​ችሁ እን​ዴት እንደ በዛ፥ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁም እን​ዴት እንደ ጸና እኔ ዐው​ቃ​ለ​ሁና።


跟着我们:

广告


广告